By | March 10, 2018


የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

– ትላንት የነበሩት፣ ዛሬ ያሉትና ወደፊት የሚኖሩት ፈተናዎች –

Formerly, Qa’ee Tufaa Munaa (now the Arat Kilo Palace)

ብርሃኑ ሁንዴ, Bitootessa 9, 2018

ክፍል አንድ

የኦሮሞ ሕዝብ በሚኒሊክ ጦር ተወሮ፣ ሀገሩንና ነፃነቱን ካጣበት ጊዜ ጀምሮ ከመቶ ዓመታት በላይ ይነስ ይብዛ፣ ይጥበብ ይስፋ እንጂ በተናጠልም ሆነ በተደራጀ መልክ ያጣውን ነፃነቱንና ሀገሩን ለመመለስ ያልተቋረጠ ትግል ስያካሄድ እስከ ዛሬ ደርሷል። ስለዚህ የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት እንደ ተነሳ ወይንም እንዴት እንደጀመረ በሰፊው ማብራራት አስፈላጊ አይሆንም። ይህ ትግል የደረሰበት ደረጃና ዛሬ ምን ላይ እንደሚገኝም ለጠላትም ሆነ ለወዳጅ ግልፅ ስለሆነ፤ ይህንንም ጉዳይ በጥልቀት ማብራራት አስፈላጊ አይደለም።

ነገር ግን በጥልቀት መታየት ያለበትና እኔም በዚህ ላይ የራሴን ሀሳብ ለመግለፅ የምፈልገው ጉዳይ፣ ይህ ትግል ወዴት እየሄደ ነው? የሚለውን ጥያቄ ማየትና፤ እንደዚሁም በዚህ የነፃነት ትግል ውስጥ የነበሩት፣ አሁን ያሉትና ወደፊት ሊኖሩ የሚችሉት ፈተናዎችን በስፋት ማየት ነው። ይቆይ ይፍጠን፣ ይርዘም ይጠር እንጂ ይህ ትግል ወደ መጠናቀቂያው እንደተቃረበ ጥርጥር የለውም። ይሁን አንጂ ወዴት አንደሚያመራና የትኛውን ግብ እንደሚደርስ አሁን ማወቅ ያስቸግራል። ለምን ቢባል፣ ለዚህ ትግል ዓላማ የሚሰጠው ትርጉምና የትግሉ የመጨረሻ ግብ ምን መሆን እንዳለበት አከራካሪ ስለሆነ ነው። እዚህ ላይ ምን ማለት እንደፈለኩ እንደሚከተለው ለመግለፅ እሞክራለሁ።

እውነት እንናግር ከተበለ፣ ዛሬ በምንገኝበት ሁኔታ ውስጥ ቅድሚያ ማግኘት ያለበትና ቀዳሚው የትግሉ ዓላማ (primary objective) መሆን ያለበት ይህን ሰው በላ የወያኔ ስርዓት ገርስሶ፤ በሕዝባችን ላይ የተከፈተውን የዘር ማጥፋት ጦርነት ማብቃት ነው። አንድ ሰው እጅግ በጣም ከተራበ ያገኘውን ይበላል እንጂ፣ ይህ ወይንም ያ ይሻለኛል ብሎ አይመርጥም። የሕዝባችን ሁኔታም ይህንኑን ይመስላል። ሕዝባችን ዛሬ ሰላምና ነፃነት አጅግ ጥሞታል፣ እጅግ ርቦታል። ስለዚህ ቶሎ ይህንን ማግኘት አለበት። ከዚያ በኋላ ነው የረጅም ጊዜ ግቡን ለመድረስ ዕድልም ሆነ አጋጣሚ የሚኖረው።

ይህ ስለሆነ፣ የዚህ የነፃነት ትግል የመጨረሻው ግብ ምን መሆን አለበት ወይንም ደግሞ ምን መሆን ይችላል የሚለውን ጉዳይ አንስቶ ይህ ወይም ያ ነው ለማለት ባሁኑ ጊዜ አስፈላጊ አይመስለኝም። ይሁን እንጂ ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ የምፈልገውና ይህ ሕዝብ የምመኘውን የምወስነውም ሆነ ከግብ የሚያደርሰው የትግሉ ባለቤት የሆነው ይኸው ሕዝብ ብቻ ነው። የትኛውም ድርጅትም ሆነ ቡድን ይህንን ልወስንለት አይችልም። ባጭሩ የራሱን ዕድል መወሰን ያለበት ይህ ሰፊው ሕዝብ ብቻ ነው ማለት ነው። የትኛውም ኃይል ይህንን ልወስንለት አይችልም።  የግል ፍላጎትም ሆነ ምኞት የዚህ ታላቅ ሕዝብ ፍላጎትም ሆነ ምኞት ሊሆን አይችልም። ይህ እውነታ ግልፅ መሆን አለበት።

እንግዲህ የትግሉን የመጨረሻ ግብ በሚመለክት ይህን ያህል ካልኩኝ በኋላ፤ የትግሉን ፈተናዎች በሚመለክት ኣንዳንድ ነገሮችን ማንሳት እሞክራለሁ። የነፃነት ትግሉን ፈተናዎች በሶስት ቦታ ከፍለን ማየት እንችላለን። አነሱም ትላንት የነበሩት፣ ዛሬ ያሉት እና ነገ ሊታዩ የሚችሉ ፈተናዎች ናቸው። ትላንት የነበሩትን ፈተናዎች እዚህ በሰፊው ማንሳት አስፈላጊ ባይሆንም፣ ነገር ግን ካለፈው ለመማር ይረዳ ዘንድ እነዚህንም ትኩረት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ይሆናል።

የኦሮሞ የነፃነት ትግል የትላንትናዎቹ ፈተናዎች

የነፃነት ትግሉ ውስጥ የነበሩትን ፈተናዎች ሁሉ ማንሳትና ማብራራት ቀላል የማይሆን ጉዳይ ነው። ይህን ሰፊ ትንታኔ ለማድረግ የታሪክና የፖለቲካ ሙያም ይጠይቃል። ይሁን እንጂ የጉዳዩን ስፋትና ጥልቀት ለባለሙያዎቹ በመተው ያለኝን ሀሳብ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ለማብራራት እሞክራለሁ።

ከታሪክ መረዳት እንደሚቻለው፣ የመጫና ቱለማ የመረዳጃ ማህበር ምስረታ በፊት የነበረው ጊዜ በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የጨለማ ጊዜ እንደነበረ ነው። ለምን ቢባል በመጡትን ባለፉት የሀበሾች ገዥ መንግስታት ስር በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የማንነት ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድ ስለነበረ ነው። በዚህ የተነሳ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኦሮሞ ሕዝብ እንኳንስ መገናኘት ቀርቶ የጋራ ማንነታቸው ለመጥፋት መቃብር ጫፍ ላይ የደረሰበት ጊዜ ነበር። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የነበረው ትልቁ ፈተና የኦሮሞን ማንነት እና ይህንን ትልቅ ብሔር ከጥፋት ማዳን ነበር። በዚህ ምክንያት በዚያን ጊዜ የነበሩት የኦሮሞ ብሔርተኞች ይህንን ጥፋት ተረድተው መፍትሔ ለመፈለግ ብለው ልዩ በሆነ ስልት የመጫና ቱለማን ድርጅት አቋቋሙ።

እዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው አንድ ጉዳይ ከመጫና ቱለማ ምስረታ በፊት የነበሩት እንደ ወሎና ባሌ የመሳሰሉትን ንቅናቄዎች መርሳቴ ወይም መዘንጋቴ ኣለመሆኑን ነው። የመጫና ቱለማን ምስረታ እንደ መነሻ የወሰድኩት ይህ ትግል በተቀናጀ መልክ መቸ እንደ ተጀመረና ከዚህ ጋር ተያይዞ ሕዝብን ማንቃት የተጀመረው መቸ እንደሆነ ለመግለፅ ነው። ከዚያ በፊት የነበሩት ፈተናዎችም ከየትኛውም ፈተናዎች ያላነሱ እንደሆነ የታሪክ ሰዎች ማስረጃ ይሆናሉ። ይሁን እንጂ የመጫና ቱለማ መስራቾችና መሪዎች ያሳለፉት ፈተናዎች ታሪክ የማይረሳው ጉዳይ ነው። በዚያን ጊዜ የነበሩት ታጋዮች ያስመዘገቡት ድሎች ናቸው ለዛሬው ትግልና እንደ እሳት እየነደደ ላለው ሕዝባዊ ንቅናቄ መሰረት የጣለው።

ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ምስረታ ጀምሮ እስክ 1991 ድረስ ኦነግን ስፈታተኑት የነበሩት ፈተናዎች በሁለት መንገድ ነበሩ። እነዚህም ባንድ በኩል ከጥላት ጋር በጠመንጃ መፋለም ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝባችንን በይበልጥ ማስተማርና ማንቃት ነበር። በዚያን ወቅት በኦነግ ሲመራ የነበረው ትግል የተለያዩ ችግሮችንና ፈተናዎችን በማሻነፍ 1991 ትላልቅ ድሎችን ኣስመዝግቧል። ይህ ብቻ ሳይሆን በዚያን ጊዜ የተገኙት ድሎች ናቸው ለጠላት ያማይንበረከክና ጭቆናን መሸከም እንቢ ያለውን የቁቤ ትውልድን (Qubee Generation) የወለዱት።

ከ1991 በፊት ኦነግ ውስጥ የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከትና አይዶሎጂ ቢኖሩም፣ ይህ የነፃነት ትግል መሪ የሆነው ድርጅት አንድነት ያለውና ጠንካራ ግንባር ነበር። እንዲዚያ ባይሆን ኖሮ ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ የሚኮራባቸው ድሎች ባልተገኙ ነበር። በመሆኑም ኦነግ ዛሬ ተከፋፍሎ እቅሙም እንደ ያኔ ባይሆንም፣ አንግቦት የተነሳው ዓላማ በኦሮሞ ሕዝብ ልብና አእምሮ ውስጥ ነው ያለው ቢባል ሀሰት የሚሆን አይመስለኝም።  ኦነግ እንደ ድርጅት ቢዳከም እንኳን የተቋቋመለትና ይዞት የተነሳው ዓላማ ነው በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት እንዲያገኝ የሚያደርገው። ስለዚህ እንደ እኔ አመለካከት ይህ ድርጅት መሪዎቹ ስህተት ቢሰሩም፣ ድርጅቱ ሁለት ሶስት ቦታ ቢበታተንም፣ መሰደብ፣ መናቅ፣ መረገም የለበትም። ይህ ድርጅት ለኦሮሞ ያደረገውን መርሳት የለብንም ማለቴ ነው።

እስከ 1991 ድረስ በኦነግ የተመራው የነፃነት ትግል ታላላቅ ድሎችን ማስመስገብ ብቻ ሳይሆን የዚህ ትግል ግብ ምን መሆን እንዳለበትም ግልፅ አድርጎ ነበር። ከ1991 በኋላ የኦሮሞ ሕዝባዊ ንቅናቄ እስከ ጀመረበት እስከ 2015 ድረስ የኦሮሞ የነፃነት ጎራ (camp) መድከምና መቀዝቀዝ ብቻ ሳይሆን ስግብግብነት፣ ለስልጣን ሩጫ፣ ክህደት፣ የኦሮሞ ባሕልና ስርዓት ማጣት፣ መተቻቸት፣ መሳደብ፣ ትዕግስት ማጣት፣ በራስ መተማመን መጥፋት፣በጠላት ላይ የሚደረገውን ትግል ትተው እርሰ በርስ ላይ ጦርነት ማካሄድ ወዘተ በእጅጉ የታዩበት ወቅት ነበር። እነዚህ መጥፎ ልምዶች ዛሬም ቢሆን አልጠፉም። እነዚህ ደግሞ ለነፃነት ትግሉ ፈተናና እንቅፋት ከመሆንም ባሻገር፣ የትግሉንም ዓላማና ግብ ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ናቸው። ይህንን ጉዳይ “የኦሮሞ የነፃነት ትግል የዛሬዎቹ ፈተናዎች” በሚል ርዕስ በሚቀጥለው ክፍል ሁለት ፅሁፍ ውስጥ እናያለን።

ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ።

One thought on “የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

 1. Beka

  Obbo Birhanu,

  I like your peace and look forward for the next installment! My suggestion to you is not to equate the pretenders on the same level as those who gave their life to the national struggle and are still doing the work on the ground. The Oromo diaspora is becoming a cancer to the Oromo national struggle for freedom! To equate those who are in the pockets of our enemy in the likes of Lencoo Lata and his ODF or J/Mohammed and his side kicks with the Oromo Libaration Front that transformed the Oromo struggle from Organization to mass uprising and changed the landscape of Ethiopian politics does not do justice to those who are paying the sacrifice.

  Leencoo Lata and J/Mohammed are cancers on Oromo struggle. Driven by arrogance and personal ambition they are slowing the Oromo struggle by a mile or so /hour but cannot stop it or reverse it.

  The story of many of the so called “ABO” is laughable. A bunch of folks fall of from the OLF and call themselves we are the tru “ABA” and run around without doing nothing. Every winter trees loss branches and the fallen branches don’t call themselves we are the tree. For we all know the.

  I hope you analyze what did these generic “ABO” ‘s did.

  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.