By | May 6, 2019


የኦዴፓ፣ አዴፓ እና አብን የተደበቀ ውስጣዊ ትስስርና የፖለቲካ አሻጥሮች

ብርሃኑ ሁንዴ, Caamsaa 5, 2019

አብዛኛውን ጊዜ ከተለያዩ ሚዲያዎች እንደምናየውና እንደምንሰማው ኦዴፓ(ODP)፣ አዴፓ(ADP)ና አብን(NaMa) ስናገሩ አንድ የጋራ ነገር እንዳላቸው ነው። ይኸውም ሁሉም ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ማውራት ነው። ነገር ግን ሌላ የራሳቸው የሆነ አመለካከትና አገላለፅ ካልያዙ በስተቀር የኢትዮጵያ አንድነት ምን እንደሆነና እንዴትስ ሊጠበቅ እንደሚችል በደንብ ያሰቡበት አይመስልም። የአንድ አገር አንድነት የሚጠበቀው በውስጧ ያሉት ሕዝቦች ማንነታቸው ሲከበርና እንደዚሁም ሰላምና ደህንነታቸው ሲጠበቅ ነው። ይህ ከሌላ ስለ አገር አንድነት ማውራት ትርጉም የለውም። በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ጉዳይና እውነታ የአገሪቷን አንድነት የሚያስጠብቅ ሳይሆን አገሪቷን ወደ መፈራረስ (disintegration) ሊወስድ የሚችል ሁኔታ ነው።

የአማራ ዴሞራቲክ ፓርቲ (አዴፓ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አብረው እየሰሩ አንደሆነ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ። ለብሔራቸው ጉዳይ ቅድሚያ ከመስጠትም አልፈው የዚህን ብሔር የበላይነት ለማረጋገጥ በሚደረገው አካሄድ ላይ ሁለቱም ድርጅቶች የጋራ አቋም አንዳላቸው ለመረዳት አያዳገትም። በሌላ በኩል ደግሞ የአገሪቷን አንድነት ማስጠበቅ በሚለው ስምና ሽፋን የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና አዴፓ እጅና ጔንት ሆነው እየሰሩ እንደሆነ የማይካድ ነው። በዚህ የጋራ አሰራር ውስጥ ደግሞ ኦዴፓ ከአዴፓ ከሚያገኘው እርዳታና ትብብር ይልቅ በተቃራኒው አዴፓ ከኦዴፓ የሚያገኘው ይበልጣል ቢባል ሀሰት አይሆንም። የድሮው ኦሕዴድ (OPDO) ያሁኑ ኦዴፓ (ODP) ለሕወሃት (TPLF) አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየው አሁን ደግሞ ተመሳሳይ አገልግሎት ለአዴፓ እየሰጠ ያለ ይመስላል።

ምንም እንኳን ኦዴፓና አብን ቀጥተኛ ትስስር አላቸው ለማለት ቢቸግርም፣ ነገር ግን ኦዴፓ ከአዴፓ ጋር በቅርበት አብሮ እየሰራ ስለሆነ፣ በተዘዋዋሪ የአብን ዓላማ እንዲሳካ ይረዳል ማለት ነው። ምክንያቱም የአዴፓና አብን የፖለቲካ ዓላማ ከሞላ ጎደል አንድ ነውና። በነገራችን ላይ የአማራ ድርጀቶች ለአማራ ብሔር ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት አበረው እንደሚሰሩ፣ ኦዴፓ ግን ምንም እንኳን የኦሮሞን ስም ቢይዝም፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት ከኦሮሞ ድርጅቶች ጋር ለመስራት ፍለጎትም ሆነ ዓላማ ያለው አይመስልም። ከአማራ ድርጅቶች ጋር ለመስራት ግን ጥሪም የሚጠብቅ አይመስልም። ነገሩ እንዲያውም አንዳንዴ ሳይጠሩ አቤት ሳይላኩ ወዴት እንደሚባለው ተረት ዓይነት ይመስላል።

ወደ ዋናው ርዕስ ለመመለስ፣ ሶስቱ ድርጅቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የውስጥ ትስስር (internal link) እንዳላቸውና የፖለቲካ አሻጥር እየተሰራ እንደሆነ በቅርብ በጉሙዝ ሕዝብ ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ጦርነት ማስረጃ ሊሆን ይችላል። እንዴት?  በመጀመሪያ የአማራን ድንበር ለማስፋት በሚደረገው አካሄድ ውስጥ ከዚህ ጦርነት በስተጀርባ አብን እንደሚኖር የተላያዩ ማስረጃዎች አሉ። ይህ አስከፊ ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ የክልሉ (የአማራ ክልል) መንግስትና እያስተዳደረ ያለው ድርጅት አዴፓ ዝምታ መምረጣቸው በተዘዋዋሪ እጃቸው እንዳለበት ያሳያል። በፌዴራል በኩልም ኦዴፓና አዴፓ ቁልፍ ድርጅቶች ሆነው እያስተዳደሩ በሚገኙበት መንግስት ተመሳሳይ ሁኔታ መታየቱ የሶስቱ ድርጅቶች ውስጣዊ የፖለቲካ አሻጥር እንዳለ ያሳያል። ወይንስ እንደሚወራው የፌዴራል መንግስት መዳከሙናን በአገሪቷ ላይ ምንም ቁጥጥር አንደሌላቸው ያሳያል??

ያም ሆነ ይህ፣ የአገው ሸንጎ መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አላምረው ይርጋው በ OMN ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የተናገሩት አንድ ነገር አንጀት የሚበላ እውነታ ነው። https://www.youtube.com/watch?v=IPocb0LwsJc  አቶ አላምረው ይርጋው  የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ቅን አመለካካት ያላቸው መሪ ቢሆኑም፣  ነገር ግን ለአገሪቷ አንድነት ከመጨነቅ ውጭ የሰው ሕይወት ሲጠፋ ምንም ዓይነት ስሜት እንደሌላቸው ተናግረው ነበር። እኔም በግሌ ይህንን እውነታ እጋራለሁ። ምክንያቱም ዶ/ር አብይ ሌላው ቀርቶ ከአብራኩ የወጡት የኦሮሞ ሕዝብ ሲገደል፣ ሲፈናቀል፣ ሲሰቃይ፣ ሴቶቻችን ሲደፈሩና የተለያዩ አስከፊ ነገሮች በሕዝባችን ላይ ሲፈፀሙ ዝምታ መምረጣቸው የማይካድ ሀቅ ነውና። እስቲ ይታየን አንድ የአማራ ተወላጅ የዶ/ር አብይን ቦታ ቢይዝ ሁኔታዎች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ መገመት ኣያስቸግርም።

ባጠቃላዩ ሁኔታዎች ሲገመገሙና በጥልቀት ሲታዩ  ምን ዓይነት የፖለቲካ አሻጥሮች እየተሰሩ እንደሆነና የፖለቲካ ቁማር አየተጫወተ እንደሆነ ለመገንዘብ አስቸጋሪ የሚሆን አይመስለኝም። ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለና መፍትሄ ካልተገኘለት አገሪቷ ወደ መፍረስም (disintegration) ሊታመራ እንደምትችል ጥርጥር የለውም። የሕዝቦች ደም በየቦታው መፍስስና ሕይወት መጥፋት መጨረሻው ወዴት ሊያመራ እንደሚችል መቸም የማይገምት ይኖራል ብዬ አላምንምና።

One thought on “የኦዴፓ፣ አዴፓ እና አብን የተደበቀ ውስጣዊ ትስስርና የፖለቲካ አሻጥሮች

  1. Abaltii Gillo

    Wantii nutti beekuu qabnnu wari harra jeequmssaa kassaannii sababa ittiin Heera biyyiitti issa ammaa jiru, mirga saboota beeku kana ittiin digaan barabadaa jiru. Uffii jakanni kanni balallefachaa, saba sodachiisuun caassa fi heera ammaa jiru diguuf, demokraatoota uffii fakeesuun halkannii guyyaa hojeechaa jiru. Kana beekun warrii Bilisumma fi demokraassi barbaduun hummnna ta’un, nagaan bu’ee akkaa sabn jiru fi jireenya issaa Bilisumma fi demokrassiin qindeefachuu danda’uu gochuun akeekka keenyaa ammaa ta’uu qabaa.
    Bilisumman saboota fi demokrassiin haa laliissaan

    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.