ሦስት አማራጮች አሉን፡- ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወይም አሃዳዊነት ወይም መገንጠል?

ሦስት አማራጮች አሉን፡- ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ወይም አሃዳዊነት ወይም መገንጠል?

ክፍል—3 (ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ, Ph.D.)

የመደመር ‹‹ፍልስፍና›› እንደ ገዳፊነት     !

(Ethiopiansism_as_Reductionism)

ሀብታሙ አለባቸውታላቁ ተቃርኖበተሰኘ መጽሀፉ ውስጥ (ገጽ. 197) እንዲህ ሲል በትክክል ይሞግታል፡2009 . ታትሞ ገበያ ላይ የዋለው የፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣውእነሆ መንገድ…› የሚል መጽሐፍየኢትዮጵያን ልማት አንቀው የያዙ ችግሮችን፣ የችግሮቹን ምንጭና አውድ ሳይነግረን፣ መፍትሄውን በምክር መልክ በማዥጎድጎድ ይለግሰናል። ለአገሩ ያለውን ጥሩ ምኞት ብጋራውም ዳንኤል በምሁርነቱ ያበረከተው እስተዋጽኦ ግን እምብዛም እንደሆነ ተሰምቶኛል። የእሱን የመሰሉየአብረን ተፋቅረን እንኑርተምኔታዊ ስብከት የሞላቸው የቡራኬ መጻሕፍት በርካታ ናቸው።

    ለምሳሌ፡– ‹‹የመደመርፍልስፍና› ›› ጽንሰሐሳብ ‹‹አብረን ተፋቅረን እንኑር፣ አብረን እንደግ፤ ነፃነት፣ እኩልነት እና ወንድማማችነት የሰፈነባት ጠንካራ ኢትዮጵያን አብረን እንገንባ፤ ከመከፋፈል ፈንታ አንድነትን አጥብቀን እንፈልግ፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በተባበረ ክንድ እንገንባ፤ ጠንካራ አንድነት ሊኖረን የሚችለው በመከፋፈል ሳይሆን በመደመር ነው፤ መደመር ደግሞ ባለፈው ታሪክ ውስጥ ተደብቆ መኖር ሳይሆን ከታሪክ ተምሮ በተለይም ከቂም፣ ከበቀል፣ ከጥላቻና ከዘረኝነት ተላቆ በእውነተኛ መንፈስ አንድ መሆን ነው፤ ስለዚህ መደመር ማለት ከዘሮ ድምር ጫወታ ወጥተን በግልና በቡድን የያዝነውን ሀብት (እውቀት፣ ጥበብ፣ የባህል እሴቶችን፣ ታሪካዊና ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦችን…) በአንድ ላይ ደምረን/አዋህደን ጠንካራና ሁሉም አቃፊ የሆነችና ለሁላችን የሚትበቃ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን አንድ ላይ እንገንባ፣….›› ወዘተ የሚል ነው››

   እውነት ነው አንድነት ወይም መደመር ቅዱስ ሐሳብ ነው፤ እጅግም መልካም ነው፣ ግና እንደ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ሥራ ሁሉ የመደመርፍልስፍና ጋሪውን ከፈረሱ አስቀድመዋል፤ መቅደም ያለበትን ነገር አላስቀደመም አልያም ለጥያቄዎቻችን ደረጃ አላበጀላቸውም። ስለዚህ፣ የጋራ ግብ አልያም የዓላማ አንድነት ሳይኖር የመደመር ‹ፍልስፍና› ሊሳካ አይችልም። የጋራ ግብ እንዲኖረን ከተፈለገ ደግሞ የአንድን ሀገር ችግር ቁልፍ ምንጭ (the root causes the problem) ማወቁ ፊቱን መድሃኒት ነው። የአንድን ችግር ቁልፍ ምንጭ ሳያውቁ መፍትሔ ማፈላለግ ውጤቱ ታጥቦ ጭቃ ነው የሚሆነው። በየጊዜው የሸረሪቱን ድር ከማጽዳት ይልቅ ሸረሪቱን ራሱን መግደልና ማስወገድ ያስፈልጋል።

    ስለዚህ፣ በአንድ ሀገር ውስጥ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ የሚቻለው የጋራ ግንዛቤ ሲኖር ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በሚትባል ሀገር ውስጥ ደግሞ ይህ የጋራ ግንዛቤ ሊፈጠር የሚችለው “የኢትዮጵያ ታሪክ”ን የሚንረዳበት እና የሚንተነትንበት መንገድ ወይም ዘዴ እንደገና በጥልቀት ሲንፈትሽ ብቻ ይሆናል። ከምዕራቡ ዓለም የተቀዳ የአስተሳሰብ ቅሬ ግን ኢትዮጵያ ታሪክአረዳድ ላይ ሥነዕውቀታዊ ጥቃት (epistemological violence) እያስከተለ ይገኛል። ዛሬ ከምንም ጊዜውም በላይ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ከመፍጠር ይልቅ  አሃዳዊነት አልያም መገንጠልን የሚያቀነቅኑ ሰዎች የዚህ የምዕራቡ ዓለም ሥነዕውቀታዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው በተለይ፣ ከእኛ የታሪክ አረዳድ በተቃራኒ የተሰለፉና በኩረጃ ፍልስፍና የተካኑ የምዕራባዊያን የአስተሳሰብ ዘይቤ ተከትለው የአውሮፓዊነት መንፈስ (ዘረኛ አስተሳሰብ) የተላበሱ ኢትዮሮፒያንስ (Westernized Ethiopians) ህብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዳይፈጠር ትልቅ እንቅፋት ሆነዋል

  ኢትዮሮፒያንስ የአንድን ግለሰብ ወይም የአንድ ሕዝብ ታሪክ አንድም ፍጹም እርኩስ፣ አልያም ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ያቀርባሉ። ይሁን እንጂ የማንኛውም ግለሰብም ሆነ ሕዝብ ታሪክ ምልካምና መጥፎ ገጽታ ስላለው፣ አንድም ፍጹም እርኩስ፣ አልያም ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ተቀባይነት የለሌውና የቅኝገዥዎች የታሪክ አረዳድና አጻጻፍ ዘይቤን የተከተለ ነው ስለዚህ፣ ሀብታሙ በትክክል እንዳስቀመጠውየአብረን ተፋቅረን እንኑርተምኔታዊ ስብከት የሞላቸው የቡራኬ መጻሕፍት በርካታ ቢሆኑም፣ የአንድን ሀገር ችግር ቁልፍ ምንጭ ሳያውቁፍቅር ያሸንፋልብለው ቀንና ማታ መስበክ እንኳን ሞያሌ ሀገር ለሚኖር ሰው እዚህ ሸገር ብብት ሥር ላሌችው ሱሉልታ ውስጥ ለሚኖር አንድ ግለሰብ ምንም ዓይነት ስሜት ላይሰጠው ይችላል።

በመጀመሪያ ደረጃ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተስፈንጣሪ/ጽንፈኛ ፖለቲከኞች አያስፈልጉንም። የኢትዮጵያ ሕዝቡ አበሳውን ስቆጥር የኖረው በጽንፈኛ የፖለቲካ አስተሳሰብ እና አፈጻጸም ነው። ፖለቲካዊ ጽንፈኝነት ቁርበት ነክ መሆኑን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፍልስፍና ታሪክ ውስጥ በተጨባጭ አይተናል። ለምሳሌ፡- ዶ/ር መረራ ጉዲና በትክክል እንደታዘበው የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖለቲካ፣ ብዙም ያለተንቀሳቀሰና ‹‹በዋናነት በሁለት ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጓተት ወደ መሃል መጥቶ የጋራ ዴሞክራትክ አጀንዳ መቅረጽ›› እንዳላስቻላቸው ያሰምርበታል። (መረራ ጉዲና፣ የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች፤የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖሊቲካ፣2008፣ ገጽ 11) የሁለቱን ልሂቃን ፖለቲካዊ ውይይት አንዱ ሌላውን የማይሰማ ‹‹የዶንቆሮዎች ውይይት (dialogue of the deafs)›› ሲል አካሄዳቸውን አጣጥሏል። (ገጽ 11፣12)

  ስለዚህ፣ ለወደፊቱ በስፋት እንደምንመለከተው ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመፍጠር ከተፈለገ ከአሃዳዊነት እና ከመገንጠል ባሻገር ያለውን የዶ/ር መረራ ጉዲና ፖለቲካዊ ፍልስፍና መከተል ያስፈልጋል። አለበለዚያ ኢትዮጵያ የመበታተን አደጋ እንደምገጥማት ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። በተለይ በመደመር ‹ፍልስፍና› ስም አሃዳዊነትን ለማስፈን የሚደረገው እንቅስቃሴ ስበዛ አደገኛ ነው። ይህንን ሀገራዊ አደጋ ለማስቀረት የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል። ምክንያቱም፣ የጋራ ግንዛቤ በሌለበት ሀገር/አህጉር ውስጥ እውነተኛ የኢኮኖሚና የፖሊቲካ ነፃነት መጎናጸፍ ዘበት ነው። ከሁሉም በላይ፣ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ የሚቻለው የጋራ ግንዛቤ ሲኖር ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ፣ ባለመስማማት መስማማት (agreeing to disagree) የሚቻለው አሁንም የጋራ ግንዛቤ ሲኖር ብቻ ነው።

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በኢትዮጵያ ውስጥ የጋራ ግንዛቤ እንዳይፈጠር ትልቅ እንቅፋት እየሆኑ ያሉት ኢትዮሮፒያንስ (Westernized Ethiopians) ናቸው። ኢትዮሮፒያንስ በኩረጃ ፍልስፍና የተካኑና የምዕራባዊያን የአስተሳሰብ ዘይቤ ተከትለው ማንነታቸውን የሰለቡ ግለሰቦች ናቸው። በተለይ ምዕራቡ ዓለም ባስታጠቃቸው ርዕዮተ-ዓለም ወይም ጽንሰ-ሐሳብ ላይ ተመስርተው፣ በፍፁም የበታችነት ስሜት የራሳቸውን ማንነት (ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ) አብዝቶ የሚጸየፉ ሲሆን፣ በተቃራንው የነጮችን ባህልና ማንነት በለየለት ሁኔታ ያመልካሉ። ኢትዮሮፒያንስ ዘመናዊነትን እንደ ወረደ በመቅዳት፣ ተጨባጩን የሀገሪቱን ሁኔታ ያላገናዘበና የምዕራቡን ዓለም ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ የሚያስጠብቅ ፖሊስዎችን በመተግበር፣ ሀገራችንን ለእጅ-አዙር ቅኝ-ግዛት ዳርጓታል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በትክክል እንደታዘበው “ላለፉት መቶ ሃምሣ ዓመታት ነፃ ሀገር ናት በምትባለዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያ መሪዎች ሥልጣን ላይ ለመውጣት ወይም ሥልጣን ላይ ከወጡ ቦኋላ ተደላድሎ ለመቆየት እንድችሉ የውጭ ኋይሎች ጉልህ ሚና ሲጫወቱ እንደነበር ነው…በሀገራችን ፖሊቲካ ውስጥ የውጭ ጣልቃ ገብነት ቋም ክስተት እየሆነ መምጣቱን በውል መንገዘብ ጠቃም ይመስለኛል።” (ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች፤የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖሊቲካ፣ 2008፣ ገጽ 16፣17)

በተለይ፣ ኢትዮሮፒያንስ ከአውሮፓዊያን ጠበብት በኮረጁት የታሪክ አጻጻፍ ስልት፣ የአንድን ሕዝብ ታሪክ ሙሉ በሙሉ አዋርደው፣ ውሸትን አውነት በማስመሰል ጽፈው ያስተምራሉ። ይህ ከቅኝ-ገዥዎች የተቀዳ የታሪክ ትንተናና አረዳድ እኛእነሱ የሚል የሁለታዊነት (dualism) ጽንሰ-ሓሳብ (‹ብሔር-ሀገር› ‹ሴሜን-ደቡብ›፣ ‹ክርስቲያን-አረመኔ›፣ ‹ባንዳ-ኢትዮጵያዊ›፣ ‹እስላም-ክርስተያን›፣ ‹ሴማዊ-ሻንቅላ› ወዘተ) በመፍጠሩ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ በአንድነት ኋይሎችና (ultra-right) በብሔርተኞች (ultra-left) መካከል ‹ያላባራ ጦርነት› አስከትለዋል። በአብዮቱ ጊዜ በብዙ ሊሂቃን ዘንድ የነበረው አንዱ ችግር ‹የኢትዮጵያ ታሪክ›ን የሚተረጉሙበት መንገድ ነበር። በቅርጽና ይዘት የተለያየ ቢሆንም፣ ይህ የታሪክ አረዳድና ልዩነት የመደብና የብሔር ጥያቄን ይዞ ብቅ ብሏል። ስለዚህ፣ የብሔር ጥያቄ የቅርብ ጊዜ ክስተት አይደለም። አንድ መጠንቀቅ ያለብን ነገር ቢኖር የመደብም ሆነ የብሔር ጥያቄ በነበረበት ኢትዮጵያ ‹ሁለቱም አልነበሩም› ወይም ‹አንዱ ብቻ ነበር› ብሎ መፈላስፍ በተዘዋዋር ‹በግድ እኛን ሁኑ› የሚል አንደምታ አለው። ‹በግድ እኛን ሁኑ› የሚለውና ከምዕራቡ ‹ዓለም› የተቀዳ አስተሳሰብ በኢትዮጵያ ምድርም እንደማይሰራ ነው።

የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ በ1960ዎቹ የነበረው ትውልድ (‹ያ ትውልድ›)፣ የሀገራችን ባህልና ኅይማኖት ወይም የሕዝቡን ሥነ-ልቡናአቀራረጽ ግምት ውስጥ ሳያስገባ፣ ዘመናዊነትን ከእነ አሰስ ገሰሱ በመቅዳት በጊዜው አብቦ የነበረውን የኢትዮጵያ አብዮት አስጠልፏል። ‹ያ ትውልድ› ለውጥ ፈላግ የሆነ ማኅበረሰብ መሆኑ ቢገባንም ቅሉ፣ ለዚህ ታሪካዊ ስህተትና የመጠፋፋት ፖሊቲካ ኋላፍነቱን መውሰድ ይኖርበታል። ይህ ግን የብሔር እኩልነትም ሆነ የሀገር እንድነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በሰከነ መንፈስ ሁላችንንም በእኩልነት የሚታስተናግድ ‹ድሞክራሲያዊት› ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቃላት ሊገለጽ የማይችል ተጋድሎ ያደረጉትን ጥቅት ቆራጥ ግለሰቦችን አይመለከትም። በተቃራኒው፣ በሕዝብ ብሶትና እንባ ለማትረፍ ሲሉ፣ አንድም በኢትዮጵያ አንድነት ስም፣ አልያም በብሔር ፖሊቲካ ስም ተነስተው የምዕራባዊያንን የኢኮኖሚ አጀንዳ በስውር በማስፈጸም  ሀገራችንን ለእጅ-አዙር ቅኝ-ግዛት የዳረጓትን አድርባይና ወሮ-በላ ኢትዮሮፕያን ፖሊትከኞችንና ምሁራንን ይመለከታል። ለምሳሌ፡- ኢትዮሮፕያንስ የአብጎዳጅነት ስሜት በመላበስ፣ በሀገራችን ውስጥ ለሚፈጠረው ማንኛውም ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የውጭውን ዓለም መፍትሔ ይሻሉ። የኢትዮጵያዊያን ችግር በኢትዮጵያዊያን ‹ብቻ› መፈታት ሲገባ፣ የሦስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ይሻሉ። በዚህም ምክንያት፣ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በመደማመጥ፣ በመነጋገርና በመግባባት መፍታት አይፈልጉም። የምዕራቡ ‹ዓለም› ርዮተ-ዓለም ለህልና ባርነት ስለዳረጋቸው፣ የተወሳሰበ ታሪክና የማንነት ስብጥር ላላት ሀገራቸው ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አመለካከት ብቻ የሚያሰርጽ አካሄድ ይተገብራሉ።

በአንድ በኩል፣ የተለያየ ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ያላቸውን ሕዝቦች በጉልበት ጨፍልቀው እንድ በማድረግ ‹በግድ እኛን ሁኑ› የሚል ጽንፈኛ አመለካከት ነው። ‹በግድ እኛን ሁኑ› ማለት ሌላ ሳይሆን፣ የራሳችሁን ቋንቋ፣ ባህልና ማንነት ትታቸው የእኛን ማንነት በኋይልና በጉልበት ተቀበሉ ማለት ነው። “ብሔራዊ ስምምነት ላይ መድረስ የሚንችለው አንድ ወጥ አመለካከት/ማንነት ስኖር ብቻ ነው” የሚል ፍልስፍናዊ አመለካከት ስበዛ ግልብ አስተሳሰብ ነው። አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሀገር፣ አንድ ኅይማኖት ያላት ሶማሊያ እንኳ ለዚህ አልታደለችም!

በሌላ በኩል፣ ያለ ጽንፈኝነት የብሔር ጭቆናንን ማዕከል ያደረገ ፖሊቲካዊ አመለካከት ሲሆን፣ “ምንም ዓይነት የጋራ ታሪክ አልነበረንም” የሚል ተረታ-ተረት ነው። ለምሳሌ፡- ከ19ኛው ከ/ዘመን መጨረሻ ወዲህ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ከሌላው ጊዜ የበለጠ ያስተሳሰራቸውና ያቀራረባቸው ብዙ የታሪክ አጋጣሚዎች ነበሩ፤ አሉምም። በአንድ ‹ግዛት› ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ይቅርና፣ ግለሰቦች ሰው በመሆናቸው ብቻ የሚጋሩ ብዙ እሰቶች አሏቸው። ‹የታሪክ ሒሳብ ካልተወራረድን ሞተን እንገኛልን› የሚል ጽንፈኛ አመለካከት ካልተከተልን በስተቀር፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አሁንም አንድ ላይ ሆኖ ይህንን ሀገር የማይገነቡበት ምንም ምክንያት አይታየኝም። ሌላው ቀርቶ የእኛ ስምምነትና አንድነት ከምስራቅ አfeሪካም አልፎ፣ ለአህጉራችን አስፈላጊና በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው።

ዛሬም አንዱ ወገን ሌላውን ከመውቀስ ውጭ የጋራ አጀንዳ ቀርጸን፣ ለሀገራችን ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዘላቅ መፍትሔ ማመንጨት ‹አልቻልንም›። ዝለዚህ አንድ ላይ ‹ማልቀስ› እን አንድ ላይ መስራት አልተቻለም! የኢትዮጵያ ‹ታሪክ› እስከገባኝ ድረስ፣ የሥነ-ልቦና ጥቅም ካልሆነ እንጂ፣ ባለፉት ሥርዓቶች ሆነ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖም ረገድ አንድ ወገን ብቻ ተጠቃም ነበር ብሎ መፈላሰፍ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ክልሆነ በስተቀር ከተጨባጩ የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተገናኘ አይደለም። ኢትዮሮያንስ ግን በአጉል ተመጻዳቅነት ‹ኢትዮጵያዊነት-ብሔርተኝነት› ‹ወዝ-አደር-ላብ-አደር› ‹ሀገር-ሕዝብ› ‹እናሸንፋለን-እነቸንፋለን› ‹ግለሰብ-ቡድን› ‹ግደታ-ነፃነት› ወዘተ የሚሉ ጽንሰ-ሐሳቦችን አንዱ የሌላው ተቃራን አድርጎ ለማቅረብ ሞክሯል። ይህ የፀጉር ስንጠቃ ክርክር ዛሬም ለእኛ ትውልድ ተርፎ የማንነት ግራ መጋባት ውስጥ ከቶናል። ‹ኢትዮጵያዊነት-ብሔርተኝነት› ‹ሀገርና-ሕዝብ› ወይም ‹ግለሰብና-ቡድን›  ወይም ‹ግደታና-ነፃነት›  የአንድ ሣንትም ሁለት ገጽታ መሆኑ እየታወቀ፣ ‹ከአንበሳውና ጐፈረው የትኛው ይቀድማል› ብሎ መፈላሰፍ ለተራበው ዜጋችን ዳቦ ይሆናል ብዬ አላስብም። ስለዚህ፣ የውሃ ቀጠነ ክርክር ትተን የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘቤ ዘላቂ የፖሊቲካ መፍትሔ ማፈላለግ ይኖርብናል። ሕዝብን በሃይመኖትና በብሔር እያከፋፈልን ማፋጀት፣ የምዕራቡን ‹ዓለም› ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ውጭ ለብዙኅኑ ኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስገኘው ጥቅም ፈጽሞ እንደሌለ መታወቅ ይኖርበታል። በአጠቃላይ በእሳት የመጫወት አባዜ ለሁላችን የሚበጅ አይመስለኝም።

ዞረም ቀረ ለዚህም ሦስት አማራጮች አሉን (1) ህብረብሔራዊ አንድነት (2) አሃዳዊነት (3) መገንጠል ከአሃዳዊነት (ከመደመር) እና መገንጠል ባሻገር ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚበጃት ህብረብሔራዊ አንድነት መሆኑን በክፍል 4 በስፋት እንመለከታለን!

ክፍል-4 ይቀጥላል!

ቸር እንሰንብት!

Yoseph Mulugeta Baba is a qubbee generation born in Eastern Wollega, Konchi/Nekemte, Ethiopia. He holds a B.A, M.A, and Ph.D. degrees in Philosophy from The Catholic University of Eastern Africa (CUEA), Nairobi-Kenya. He also holds a B.D, in Sacred Theology (Magna Cum Laude Probatus) from Pontifical Urbaniana University, Rome. His research interests involve: Metaphilosophy, Oromo Philosophy, Continental Philosophy, Post-colonial African Philosophy, Sage Philosophy, and Post-modernism. His publications include, Metaphilosophy or Methodological Imperialism? (2015); Philosophical Essays (2016); The Oromo Concept of reality: Epistemological Approach (2016); የኢትዮሮፒያንስ የአስተሳሰብ ቅሬ፤ ‹አበበ በሶ በላ› vs ‹ጫላ ጩቤ ጨበጠ› (2017); KANA DUBBIIN (2017); Negritude As The Recovery of Indigenous African Political Leadership The Case of Gadaa Oromo Political Philosophy (2017); Remembering Great African Thinkers (2018). His book titled, African Philosophical Hermeneutics, is forthcoming. Currently he teaches African philosophy at CFIPT. He can be reached at:  kankokunmalimaali@gmail.com

2 Comments

  1. EPRDF A.K.A. Prosperity Party should have distributed power to other political parties outside EPRDF starting from Tamrat Layne’s administration time until now , instead EPRDF hugged all the power to itself as much as it can, still fighting tooth and nail to cling to power. EPRDF is currently a little infant baby in a giant’s body ,too clumsy it is squashing somebody or something every move EPRDF AKA Prosperity makes. It is time to stay clear by keeping a safe distance from EPRDF AKA Prosperity because once this infant baby slips, it is bound fall hard , as long as the infant baby doesn’t land on the people it is ok, that is why especially from now on everyone should keep a safe distance from this infant baby in a giant’s body known as EPRDF AKA Prosperity.

  2. Liviing amongst the nephtegnas timkihitignas eventually will lead to serious psychological problems, not to mention the anger along with the physical problems such as gastritis or high blood pressure it causes.
    Nephtegnas Amharas are showing their true nature’s lately, how backward barbarians they are . I sensed Amaras can not talk in a civilised manner even amongst themselves. They always shout at each other with a tone of anger and hate which they think is normal. I went to their huge Thanksgiving party in San Francisco California few days ago. I couldn’t sit amongst them for 20 minutes because of the way they talk , me and my boyfriend apologized and left right away. We promised never to associate with Amaras anymore.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.