በምስራቅ ወለጋ መንግስት ከተለያዩ የሰራዊት ክፍል አቀናጅቶ የላካቸዉ ወታደሮች ከ350 በላይ ንፁኃንን ሲገድሉ

በምስራቅ ወለጋ መንግስት ከተለያዩ የሰራዊት ክፍል አቀናጅቶ የላካቸዉ ወታደሮች ከ350 በላይ ንፁኃንን ሲገድሉ ከ500 በላይ ቤቶችን አቃጥለዋል።

KMN:- August 30/2021

በወለጋ አራቱም ዞኖች የመንግስት ወታደሮችን አሸንፎ ህዝባዊ መንግስት አቋቁሞ የነበረዉ የኦሮሞ ነፃነት ጦር (ኦነጦ) አሁን መንግስት ከአማራ ክልል ማሊሺያ,ከሀገር መከላከያ,ከአማራ ፋኖ እና ዉስን የኦሮማያ ልዩ ሀይል ያደራጃቸዉን ሸራዊት በአንድ እዝ ስር በተለያዩ ግንባሮች አሰልፎ የመጨረሻ ፊልሚያዉን እያደረገ ያለዉ ስረዓቱ ከባድ ሽንፈት እየገጠመዉ ሰራዊቱ የሳት’ራት እየሆኑ እንደሆነ የግንባሮቹ ምንጮች ገልፀዋል።
በዚህ ዉጊያ የተሸነፈዉ መግስት አቀናጅቶ ወደዚህ የላከዉ ሀይል በምስራቅ ወለጋ ሀሮ ሊሙ፣ ሀገምሳ፣ አርቁምቤ እና ኪረሙ ወረዳዎች ላይ ባለፉት ሶስት ቀን ብቻ ከ370 በላይ ንፁኃን ኦሮሞዎችን በጅምላ የገደለ ሲሆን ከ 500 በላይ የገበሬ መኖሪያ በረቶችን አቅጥለዋል። በዚህ ምክንያትም በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት “ይህንን ጭፍጨፋ ለአለም ማልበረሰብ እንዳናሳውቅ ከሀገር ቤት ኢንተርኔት ዘግቶ ከዉጫ በሳተላይት የሚተላለፉ ሚደመያዎችንም ጃም በማድረግ የንፁኃንን ለቅሶ አፍኗል” ሲሉ ስለ ጉዳዩ መረጃዉን ያደረሱን የአከባቢው ነዋሪ ገልፀዋል።
በተያያዘ ዜና በማዕከላዊ ዞን በትላንትናዉ እለት ከሰዓት ጀምሮ ከበባድ ውጊያዎች በኦሮሞ ነፃተንት እና በመንግስት ታጣቂዎች መኃል የተደረገ ሲሆን በጅባት፣በአቡነ ግንደበረትና ሚዳ ቃኚ የተባሉ አካባቢዎች በመንግስት ሰራዊት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸዉን እና ብዛት ያላቸዉ የነፍስ ወከፈ ማሳሪያዎችን መማረካቸዉን የአከባቢዉ ምንጫቻችን ገልፀዋል። በዚሁ አካባቢ እስረኞች ከተለያዩ ማጎራያዎች በነፃነት ታጋዮች መለቀቃቸዉም ተገልጿል።
በደቡብ መዓከላዊ ዞን ደግሞ በጃል ነዲ ገመዳ ስም የተሰየመው የ (ኦነጦ) በ አርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ እና አካባቢዉ ላይ ባደረገው መብረቃዊ ጥቃት ከ20 በላይ የመንግስት ጦርን ደመሰስኩ ያለ ሲሆን 13ቱ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ በ አሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ ሲል የማዕከላዊ ደቡብ እዝ መረጃ ምንጫችን አረጋግጧል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.