በኦሮሚያ ላይ እያንዣበበ ያለው የአደጋ ደመና ካልጠራ የኦሮሞ ሕዝብ ህሊውና አሳሳቢ ነው

በኦሮሚያ ላይ እያንዣበበ ያለው የአደጋ ደመና ካልጠራ የኦሮሞ ሕዝብ ህሊውና አሳሳቢ ነው

በብርሃኑ ሁንዴ, Mudde 20, 2018

የኦሮሚያ ምድር የጦር ሜዳ እንዲሆን የሚመኝ ወይም የሚፈለግ የኦሮሞ ጠላት ብቻ ነው። ኦሮሞ ሆኖ ግን ይህንን የሚፈልግ ካለ ለግል ጥቅምና ለፖለቲካ ፍጆታ የሚሰራ ቡድን ወይም ድርጅት ነው። በኦሮሞ ድርጅቶች መካከል ችግሮችና ግጭቶች ሲፈጠሩ ቶሎ ብለው በተፈጠረው አጋጣሚ የሚጠቀሙት የኦሮሞ ጠላቶች ናቸው። የሚያሳዝነው ግን ኦሮሞ ይህንን አስጊ ጉዳይ ማየትና መረዳት አለመቻል ነው። ባሁኑ ወቅት በተላያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች እየተደረገ ያለው ጦርነት በማንም ይጀመር፣ በማንም ይቀናጅ፣ በማንም ይደራጅ በመሃል እየተሰቃየና እየተጎዳ ያለው ሰላማዊው የኦሮሞ ሕዝብ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ሲታሰር፣ ሲገደል፣ ሲፈናቀል፣ ከአገር ሲሰደድ የኖረው ኣንሶት ዛሬም ሰላም አጥቶ መኖሩ እጅግ ያሳዝናል። ይህ ሕዝብ ለችግርና ስቃይ ብቻ የተፈጠረ ይመስል ስቃዩ በዝምታ መታለፍ አለበት? እስከ መቸስ ይህ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ይቀጥላል?

ከተለያዩ ሚዲያዎች ማየትና መስማት እንደሚቻለው፣ ባሁኑ ጊዜ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና በመንግስት መካከል በተፈጠረው አለመስማማት በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች በተለይ ደግሞ በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ግጭቶችና ጦርነቶች እየተካሄዱ ናቸው። ችግሮችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ መፍታት ሲቻል፣ እልህ ውስጥ በመግባት እንደገና ጦርነት ውስጥ መግባት ለማን ትርፍ ሊያመጣ ይችላል ተበሎ ታስቦ ነው? በዚህ በተፈጠረው ጦርነት ዋናው ተጠቃሚ ፀረ ኦሮሞ ኃይሎች መሆናቸው እየታየ እንዴት የባሰ አደጋ ሊያመጣ ወደሚችል ሁኔታ ውስጥ ይገባል? በዚህ በተፈጠረው ሁኔታ ውስጥ እጅግ የሚገርመው ጉዳይ ከጣላቶች ጋር ተባብረዋል እየተባለ አንዱ ወገን ሌላውን ስወነጅል ነው። ለምሳሌ ያህል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚታየው ኦነግ ከወያኔ ጋር እየሰራ ነው ይባላል።

እስቲ ልብ እንበልና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ጉዳዩን በጥልቀት እንይ። “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” የሚባለው መርሆ እንኳ ቢከተልና ኦነግ ከወያኔ ጋር ሊሰራ ይችላል ተብሎ ቢታሰብ እንኳን፣ አንድ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ የወያኔ የበላይነት አይኑር እንጂ አገሪቷና እያስተዳደረ ያለው መንግስት በኢሕአደግ የሚመራና ወያኔ ደግሞ አሁንም የዚህ ድርጅት አባል እንደሆነች ግልፅ ነው። ታዲያ ከእውነታ አንፃር ሲታይ ሕወሃት የመንግስትም አካል ሆና እያለች በሌላ በኩል ግን ተቃዋሚ ድርጅትን ትደግፋለች ማለት አብሮ የማይሄድ ነው። የዚህች አገር የፖለቲካ ሁኔታ እጅግ የተወሳሰብ እንደሆነ ይገባኛል። ወያኔም ሁለት ሚና እየተጫወተች እንደሆነም ግልፅ ነው። ባንድ በኩል የመንግስት አካል በመሆን በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ ሚና በመጫወት ከሌሎች የመንግስት ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር መተባበር እንደምትፈልግ የማይታበል ሀቅ ነው።

በወያኔ በኩል እየተካሄደ ያለው የፖለቲካ ጨወታ ምንም ይሁን ምን ችግሩ ያለው ግን በኦነግና በኦዴፓ መካከል እየተደረግ ባለው የእልህ ጦርነት ኦሮሚያ በአደጋ ደመና መንዣበቧ ነው። ይህን አደጋ ለማስቀረት የጋራ መፍትሄ ካለተገኘ ኣንድ አካል ጥፍቶ ሌላው መቅረት ስለማይችል፣ የኦሮሞን ሕዝብ ሊያጠፋ የሚችል ጉዳይ መሆኑ ለሁሉም ግልፅ መሆን ይገባል። ይህንን አደጋ ማስቀረት የሚቻለው ደግሞ በጦርነት ሳይሆን ቁጭ ብለው በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው የጋራ መፍትሄ መፈለግ ነው። ይህ የሚደረገው ደግሞ ለድርጅቶች ጥቅም ሳይሆን ለሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ተብሎ ነው። ጌታችን ሕዝባችን ነው የሚባለው አሁን ስራ ላይ መዋል አለበት። የኦሮሞ ጠላቶች በተለይም ፀረ ኦሮሞ ነፃነት ኃይሎች ይህንን የተፈጠረውን ሁኔታ በደስታና በዝምታ አየተከታተሉት ናቸው። የሚፈጠረውን የፖለቲካ አጋጣሚም እየጠበቁ ነው። የኦሮሚያ ምድር የጦር ሜዳ መሆን የሚጠቅመው የኦሮሞ ጠላቶችን እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ ኪሳራ እንጂ ምንም የሚገኝ ትርፍ አይኖርም።

በፖለቲካ ፕሮግራማቸውና በትግል ግባቸው መካከል ያለው ልዩነት እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣ ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችና ኃይሎች ለኦሮሞ ሕዝብና ኦሮሚያ ህሊውና (ለራሳቸውም ህሊውና) ብለው ለአገር ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት በመካከላቸው ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፍታት ጊዜ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። አንዱ በሌላው ላይ ጣት መቀሰር፤ አንዱ ሌላውን ለማጥፋት መሞከር ለኦሮሞ ብሔር ውርደትና ውድቀት ነው። ለጠላቶቻችን ግን ወርቃማ አጋጣሚ ነው የሚሆነው። የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ ሊያገኝ ነው ተበሎ በሚጠበቅበት ወቅትና አጋጣሚ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የዚህን ሕዝብ የነፃነት ትግል ለመቅበር መሞከር ተመልሶ ሊገኝ የማይችል አጋጠሚን ማጥፋት ነው። በኦሮሚያ ላይ እያንዣበበ ያለውን የአደጋ ደመና ማጥራት የሚቻለው በኦሮሙማ ላይ በመመስረትና ለሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ብሔራዊ ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት ያሉትን ችግሮች በጋራ መፍታት ሲቻል ብቻ ነው።

በስተመጨረሻ አንድ ሁሉም መገንዘብ ያለባቸው ጉዳይ ይህ በኦሮሞ ልጆች ደምና አጥንት የተገኘው የለውጥ አየር እንዳይበከልና እየተሞከረ ያለውም ሽግግር እንዳይቀለበስ ሁሉም በጋራ መስራት ግዴታ ይሆናል ባይ ነኝ። ይህ እየታየ ያለው ለውጥ ከተቀለበሰና የኦሮሞ ጠላቶች ወደ ስልጣን ከመጡ፣ ከምን ጊዜውም የበለጠ ለኦሮሞ መጥፎ እንደሚሆን መገንዘብ አለበን።

1 Comment

 1. ODP/OPDO ወስጥ መሽገው ኦሮሞን የሚወጉት ስማቸውን ወደ ኦሮሞነት የቀየሩ የአማራ ልጆች ከፊል ዝርዝራቸው ተጋለጠ፡፡

  ለጊዜው የኦሮሚያ ገጠር አደረጃጀት ዘርፍ ላይ የሚሰራው እና አዲሱ አረጋ ቂጤሣ በሚል ስም ራሱን ደብቆ ያለ የነፍጠኛ ልጅን ነው የማስተዋውቀው፡፡ ይህ ሰው ትውልዱ ኢሉአባቦራ ውስጥ ሲሆን ቤተሰቦቹም በ1963 ዓ.ም. ከደብረ-ሲና የመጡ ና ኦሮሚያ (ኢሉአባቦራ) ውስጥ የሰፈሩ ከተስፋፊ የሚኒሊክ ተልዕኮ ፈጻሚዎች መካከል ናቸው፡፡ ለዚህ ሰው ትክክለኛ በቤተሰቡ ተሰጥቶት የነበረው ስሙም አዲሱ አረጋ ጌታሁን መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  ይህ ሰው ስም ቀይረው በODP/OPDO ውስጥ መሽገው ኦሮሞን ከሚወጉ የውስጥ አርበኞች የሀበሻ ልጆች አንዱ ብቻ ነው፡፡ እነ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ዶ/ር አብይን ጨምሮ በኦሮሞ ላይ የሚሰሩት የOPDO ሰዎች ሁሉ ዘር ከልጓም ይጎትታል እንደሚበለው ሆኖባቸው መሆኑን ብሔርተኛ ኦሮሞዎች ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  በተለይ ሀክ ኤቲኤም / hack ATM aka HAK ATM አባላትና በTeam Lemma ለማ ስም በODP/OPDO ውስጥ የተሰገሰጉት ኦሮሞን የሚቦረብሩ የውስጥ አርበኞች ሀበሾች ናቸው፡፡

  HAK ATM stands for Hailu Gonfa. Abebe Geresu, Kemal Galtu, Addisu Arega, Milkessa Midaksa

  This was posted on mereja.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.