በኦሮቶዶክስ ሃይማኖት ተቋማት ሥር የተደበቀ ነፍጠኝነት በሁሉም አቅጣጫ እየተጋለጠ ነው

በኦሮቶዶክስ ሃይማኖት ተቋማት ሥር የተደበቀ ነፍጠኝነት በሁሉም አቅጣጫ እየተጋለጠ ነው።
ተቋማቱ ለተወሰኑ ቡድኖችና ግለሰቦች የንግድ ማዕከል እንደሆነች በግልጽ እያየን ነው።


ከኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኦሮሚያ ቤተክሀነት ፅ/ቤት እንዲቋቋም በመጠየቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክተርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስን በመጠየቅ የሰጠው መግለጫ ጥፋት ነው በማለት የኮሚቴው አባላት ይቅርታ እንዲጠይቁ ብፁሃን አባቶች ለማስገደድ ብሞክሩም የኮሚቴው አባላት ያጠፋነው ነገር የለም በማለት ይቅርታ መጠየቅ አይገባንም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ምክኒያቱም መግለጫ የተሰጠው፡-

1ኛ. የቤተ ክርስትያኗን ቀናኢ ልጆችን ብሶትና ፍላጎትን ለመግለፅ ነው

2ኛ. ላለፉት 27 አመታትና ከዚያ በፊት ባሉ ጊዜያት ለህዝቡ በተለይም ለኦሮሞ ህዝብ ተደራሽ ያልሆነ መዋቅርና የአገልግሎት አሰጣጠት ችግር ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ

3ኛ. ቋሚ ሲኖዶሱ መግለጫ እንዳይሰጥ ከልክሏል ብለን ስለማናምን

4ኛ. ህዝቡ መግለጫውን በከፍተኛ ተነሳሽነት የሚጠብቅ ስለሆነ መግለጫው በመቅረቱ ምክኒያት የሀገሪቱ ሰላም እንዳይደፈርስ

5ኛ. እንዲያውም ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ከሆነ መጠየቅ ያለባቸው ላለፉት አመታት ስር የሰደደውን የቤተ ክርስትያኗን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ ቤተ ክርስትያኗን የፖሊትካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶቻቸው ሎሌ ያደረጉ ብፁሃን አባቶች በመሆናቸው ህዝቡን ይቅርታ በይፋ ጠይቀው ህዝቡን እንዲክሱ በትህትና በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን::

በአጠቃላይ በእነዚህና አያሌ አሳማኝ ምክኒያቶች ያለጥፋታችን ይቅርታ ጠይቁ የተባልነውን አስገዳጅ ኣካሄድ አልተቀበልንም፡፡

የኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ
ጳጉሜ 2፣ 2011 ዓ.ምKMN:- September 08/2019
በእስራኤል ሀገር የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ገዳማት አስተዳደር ከ 10 በላይ ጳጳሳትን የብሄር ተኮር ጥቃት አደረስችባቸዉ::
———————————————–

በሀይማኖቱ አስተምህሮ ውግዝ የሆነዉን የሰዉን ልጅ በብሄር በመለያየት ; የትግራይ,የኦሮሞ እና የጉራጌ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አባቶችን ከገዳሙ እንዲወጡ ብሎም ደሞዛቸዉ እንዲቋርጥ እንዲሁም ቪዛቸዉ እንዳይታደስ በማድርግ በገዳማቱ አስተዳደር እና በአንድ ብሄር በተደራጁ የገዳማቱ አስተዳደር አባላት ይህ ነዉ የማይባል በደል ተፈፅሞባቸዋል::

ይህ ሲሆን በደላቸዉን ለህገሪቱ ጠቅላይ ሲንዶስ እና ለጠቅላይ ፓትሪያኩ ባስገቡት የአቤቱታ ደብዳቤ ከታች ያለዉ ደብዳቤ ከፓትሪያርኩ ለገዳማቱ እስተዳዳሪዎች የተከ ሲሆን የገዳማቱ አስተዳዳሪዎች ግን ሊቀበሉት አልፍቀዱም::

በዚህ ድርጊታቸዉ ስንዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ጠርቶ ወደ እስራኤል የሚሄዱ ጳጳሳትንመርጦ ለእርቅ የላከ ሲሆን የገዳማቱ አስተዳዳሪዎች ለሽምግልና ከኢትዮጵያ የተላኩትንም ጳጳሳት ሊሰሙ አልፈቀዱም:: በዚህም ከገዳማት የታገዱት አባቶች አሁንም ችግር ላይ እንዳሉ ለ KMN ገልጸዋል::

መርጃዉን የላኩልንን አባቶች KMN አንጋግራ ሙሉዉን መረጃ ለህዝብ የምናደርስ መሆኑን ከዉወዲሁ እንገልፃለን::

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.