በኬሎ ሚድያ (Keelloo Media) ላይ የተለቀቀው የአብይ አህመድ ድምፅ አወዛጋቢነት

በኬሎ ሚድያ (Keelloo Media) ላይ የተለቀቀው የአብይ አህመድ ድምፅ አወዛጋቢነት

ብርሃኑ ሁንዴ, Waxabajjii 3, 2021

Kello Mediaበቅርብ በኬሎ ሚድያ (Keelloo Media) ላይ የተለቀቀው የአብይ አህመድ ድምፅን በሚመለከት አወዛጋቢ ጉዳዮች በማህበረ ሰብ ድህረ ገፆች ላይ እየታዩ ናቸው። በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ማጥፋቱ ተገቢ መስሎ ባይታየኝም፣ ነገር ግን አንድ እውነታን መገንዘብ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ በዚህች አጭር ፅሁፍ አስተያየቴን አቀርባለሁ። ሌባ እናት ልጇን አታምንም” እንደምባለው፣ PPዎች የራሳቸውን ስራና ተንኮል በሚገባ ስለምያውቁ፣ ሌሎችም እንደዚያው ያደርጋሉ በሚል አመለካከት ወይንም ደግሞ ይህንን ሚስጥራቸውን ለመደበቅ ስሉ ወዲያና ወዲህ ስሉ ይስተወላሉ። የPP ካድሬዎች ይህ በፎቶ ሾፕ የተሰራ፤ እንደዚሁም ከዚያና ከዚህ ተለቃቅመው የተሰሩ ድምፆች ናቸው እያሉ ስራቸውንና ሴራቸውን ለመደበቅና ሕዝብንም ለማወናበድ እንዳበደች ውሻ ይሯሯጣሉ።

ምናልባትም የጉዳዩ አወዛጋቢነት እዚህ ላይ መሆን ስለሚችል፣ እስቲ ወደ ዝርዝር ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት አንድ ጥያቄ ላንሳ፥ ማንም ይቅዳ ማንም ይህ ድምፅ PP የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ላይ እንዴት ሊቀዳ ቻለ? በሚስጢር ነው የተቀዳው እንዳይባል እንደሚመስለኝ ይህ ስብሰባ አንገብጋቢና ሚስጥራዊ እንደሆነ ነው የምገባኝ። በመሆኑ ደግሞ ጥብቅ የሆነ ፍተሻ ይደረጋል የሚል እምነት አለኝ። ጥብቅ ፍተሻ የሚደረግ ከሆነ ደግሞ፣ አንድም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ መግባት እንደማይችል ነው።  በሌላ በኩል ደግሞ እስቲ ፍተሻ አይኖርም፣ የኤለክትሮኒክስ ዕቃም ሳይከለከል ይገባል እንበል። ይህ ከሆነ ደግሞ ድምፁ የተቀዳው በሁለት መንገድ ሊሆን ይችላል። አንደኛ  አንድ የሰበስባው ተካፋይ ድምፁን ቀድቶ ለኬሎ ሚዲያ አስተላላፈ ማለት ነው። ሁለተኛው PP ራሱ ለተንኮልና የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ሆን ብሎ ያዘጋጀ ሴራ ሊሆንም ይችላል። ይህ ሁለተኛው መንገድ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ባሁኑ ጊዜ የPP መንግስት (እነዚህን የሽፍቶች ቡድን መንግስት እንበለውና?!) የዓለም ትኩረት ውስጥ ስለገባና በተለያዩ ችገሮች ስለተጠመደ፣ ይህን ለማዘናጋት የተደረገ ሴራ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ።

የሕዝብን ትኩረት አቅጣጫ የማስቀየሩ ጉዳይ በሁለት ስልቶች ነው። አንደኛ ራሱ ድምፁ እንዲቀዳና እንዲለቀቅ ካደርጉና ይህ ከተለቀቀ በኋላ ደግሞ ሰዎች በዚህ ላይ ጊዜአቸውን እንዲያባክኑ አጀንዳ መፍጠር ነው። ሁለተኛው ጩኸቶች ከተበራከቱ በኋላ ደግሞ በይበልጥ ነገሮችን ለማሟሟቅ ይህ የውሽት ድምፅ ነው እያሉ ከድሬዎቻቸውንና ለሎችንም busy ያደርጋሉ። ይህ ለነሱ ትንሽ እረፍትና የጊዜ መግዣም ስልት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንድሚባለው ውዥንብር ከፈጠሩ በኋላ ተመለሰው የኬሎ ሚዲያን ሰም ለማጠልሸት ዘመቻ ያደርጋሉ። ይህ ሚዲያ ገና ልጅ በመሆኑ፣ ስሙ እንዲጠፋና ተቀባይነቱ እንዲቀንስ ያደርጋሉ ማለት ነው። በዚህ በኩል የኦሮሞ ድምፅ ከሆኑት ሚዲያዎች ውስጥ አንዱን ለመምታት ተሳካላቸው ማለት ነው። ከኬሎ ሚዲያ ደግሞ ትልቅ ቂም እንዳላቸው መዘንጋት የለብንም። ይህን ቂም የምወጡበት ደግሞ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል። ይህን ባጭሩ ካሉክኝ በኋላ አስቲ አንድ እውነታን መገንዘብ አስፈላጊ ስለሆነ ነው ብዬ የፅሁፉ መግቢያ ላይ ወደ ጠቀስኩት ጉዳይ እመለሳለሁ።

ይህ ተቀዳ የተባለው የአብይ ንግግር የቀጥታ ስርጭትም ሆነ እነሱ እንደምሉት ከተላያዩ ንግግሮች ተሰብስቦ በፎቶ ሾፕ የተሰራ ቢሆንም፣ አንድ መታወቅ ያለብት ሀቅ አንደኛ የማይካድ የአብይ አህመድ ድምፅ መሆኑ ሲሆን፤ ሁለተኛ ዛሬም ሆነ ትላንት፣ ባለፈው ወርም ሆነ ዓመት አብይ የምናገራቸው ንግግሮች በተግባር እየታዩ መሆናቸውንና የሱ ዓላማ ሁሌም ደም እያፋሰሰ ስልጣን ላይ መቆየት በመሆኑ ይህ እንደ አዲስ ነገር መታየት የለብትም። ይህ ሰውየ ተናገረም አልተናገረ፣ ዛተም አልዛተ እሱ ወደ ስልጣን ከመጠባት ጊዜ አንስቶ የሰው ደም እየፈሰሰ፣ የዜጎች ሕይወት እንደቀጠፈ፣ ንብረት እየወደመ ወዘተ መሆኑ ከዕለት ወደ ዕለት እየታየና እየተባባሰ የመጣ ጉዳይ ነው። ግብረ ኃይል እያለ የምፎክርበትም በፊትም የነበረ፣ አሁንም ያለና ይህ ሰውየ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ወደፊትም የሚኖር ስለሚሆን ይህም እንደ አዲስ ነገር የሚታይ አይደለም።

አብይና ግብረ አበሮቹ ሰዎችን እያሰሩ፣ እየገደሉና እያሰቃዩ ስልጣን ላይ መቆየት ትልቁ ዓላማና ፍላጎታቸውም በመሆኑ ብዙም አይደንቅም። ከወሬ ማሟሟቅ የምያገኙት ትርፍ ቢኖር ግን ሕዝብን እያወናበዱ ለራሳቸውም ጊዜ መግዛትና ለሌሎች ደግሞ የጊዜ መግደያ የመነጋገሪያ አጀንዳ መፍጠር ነው። ስለዚህ ይህ ተቀዳ የተባለው ድምፅ አዲስም ሆነ አሮጌ፤ የእውነትም ሆነ የውሸት ይህ የኦሮሞን ሕዝብ ከትግሉ ማዘናጋት የለበትም። የኦሮሞ ሕዝብ ትልቁ ትኩረት ይህ ሰው-በላ የኒዎ ነፍጠኛ ስርዓት ከነስሩ ተነቅሎ፤ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ትግሉን ከምንጊዜውም በበለጠ ማጠናከር ብቻ ነው። በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (WBO) እጅግ ተጠናክሮ እነዚህን ተምቾች ከኦሮምያ እንዲያፀዳ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ነው። እውነታው ይህ ነው።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!!!

 

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.