ትልቁ ቁምነገር የውሾቹ አሳዳጊ ጌቶቻቸውን መንከስ እና መብላት አይደለም

ትልቁ ቁምነገር የውሾቹ አሳዳጊ ጌቶቻቸውን መንከስ እና መብላት አይደለም

Dannaboo Dhaqqabaa | January 19, 2021
ብዙ ተንታኞች ህወሓት እራሳቸው ፈጥረው፣ መስርተው እና ባሳደጉት OPDO/ODP መበላትን የተመለከተ የተለያዩ ትንታኔ በመስጠት ተጠምደዋል። ገምሱ ድርጊቱን ባሳደጉት ውሻ ከመነከስ ጋር ስያስመስሉ፣ ሌሎች ደግሞ ኢትዮጵያ ከምትታወቅበት ተንኮል እና የሎሌ ጌታውን መገልበጥ ድርጊት አድርገው ይተነትናሉ። የኢሕደግን ፓለትካዊ ቀመርን በቅርበት የምያዉቁት ደግሞ የግዜ ጉዳይ እንጂ እነ አብይ አህመድ ፣ ደመቀ መኮንን ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ለማ መገርሳ፣ ሙክታር ከዲር፣ ግርማ ብሩ፣ ሽመልስ አብዲሳ ወዘተረፈ እጣ ፈፈንታም ከአለቆች/አሳዳግዎቻቸው የተለየ አይሆንም በማለት ይከራከራሉ። ነገርግን ከኢትዮጵያ አፈጣጠር፣ ነባራዊ ሁኔታ እና ካለችበት የgeopolitical ውጥንቅጥ አንፃር እነዝህ ሁሉ ዋናውን በሽታ ትተው ጥቃቅን ምልክቶች ላይ ያተኮሩ ይመስላል ።
በእርግጥ  እነ ስዮም መስፍን እራሳቸው ባሳደጉት ውሻ ነዉ የተነከሱት ።ዋናው ቀምነገር ግን የህወሓቶች እራሳቸው ባሳደጉት ውሻ መነከስ እና መበላት አይደለም ። በእርግጥ ውሻ አሳዳጊውን ከነከሰ ሌላ ማንንም አይምርም! የመገንዘብ ዓይኖቹን ከፍቶ መመልከት ለምችል ሰው ግልጥ ብሎ ምታየው ሃቅ ኢትዮጵያ እራሷን በራሷ እያጠፋች መሆኑ ነው። የውሾቹ አሳዳጊ ባለቤቶቻቸውን መንከስ እና መብላት ዋናው ጉዳይ ሳይሆን ከጉዳዩ መለያ ምልክቶች አንዱ ብቻ ነው። ትልቁ ቁምነገር  በወንጀል ተጸንሳ፣ በወንጀሎች ተወልዳ እና በወንጀሎች ተጠብቃ የቆየችው ኢምፓየር አሁን የመሞቻ ግዜዋ መድረሱ ነው።
ኢምፓየር ኢትዮጵያ ልክ እንደ ዪጎዝላቭያ  ከዓለም ካርታ ለይ  የምትጠፋበት ግዜ መቃረቡን የምያመላክቱ ብዙ ከስተቶች እየተከሰቱ ነዉ- ማየት ለምችሉት።  የሴሜኑ የነፍጠኛ Hardcore ቡድን እንኳን እድሜ ለአሳምነው ፅጌ እርስ በራሱ ተባልቶ ሳስቷል። በተጨማሪም  ጎንደር እና ጎጃምን ሱዳኖች በጋድቃባ  እየተረከቡ ነዉ፣ ይመቻቸው። በንሻንጉል ጉምዝ ደግሞ ነፃ አገር ነበረች ነፃነቷን አስመልሳ ነፃ  ሆና መቆም ትችላለች። የገምቤላው ደግሞ ቀላል ነው፣ 85% በላይ የምሆኑት የጋምቤላ ነዋሪዎች የSouth Sudan ዜጎች ናቸው ። ስጀመር ጋምቤላ ከጥቂት ዐስርተ-ዓመታት በፊት ነበር ከሱዳን ተነጥቃ ለኢምፓየር ኢትዮጵያ የተሰጠው እናም መመለስ አለባት- ትግራይ ነፃነቷን ስትቀዳጅ Kassalaን ማስመለስ ትችላለች ። ጂቡቲ አፋርን በሰላም ለመረከብ ቀብድ መስጠት ጀምራለች ፣ እናም እሱ ብዙ ውጣ ወረድ አይኖረውም ። የኦሮምያም እንደዛው። Declaration of Independence of Oromiaን ተከትሎ ነገሮች ዓለምአቀፍ አሰራርን መሠረት በማድረግ የድንበር ማስመር ስራ ይሰራል። የኦሮሚያ ድንበርን ማካለል ስራ ስጠናቀቅ የቆዳ ስፋቷ ብያንስ ከthe Scramble of Africa ቤፊት ወደነበረበት 600000km2 ይመለሳል። ሌሎችም እንደዝያው። ወወላይታ፣ ካፋ፣ ስዳማ፣ ወዘተረፈ እያንዳንዳቸው በሉዓላዊነት የቆሙ ነፃ አገራት ነበሩ፣ እናም ወደ ነፃነታቸው ይመለሳሉ። በዝህ መልኩ የኢትዮጵያ ሥርአተ ቀብር በፀጥታ ይፈፀማል።
በእርግጥ ኢትዮጵያ እራሷን በራሷ ከዓለም ካርታ ለይ በርትታ እየሰራች ነው። ያለፋት የEthio- Eritreaው ጦርነት፣ የEthio-Somaliaው ጦርነት ወዘተረፈ፣ እና አሁን እየተካሄዱ ያሉት የ Ethio-Tigrai፣ Ethio-Oromia፣ Ethio-Sudan፣  ወዘተረፈ ጦረነቶች እና ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ሶማልያ ጋር የገባችበት ውጥረት መነሻ አንድ እና ግልፅ ነው። ሁላም ሰው  የክስተቶቹን ገፅታ በተመለከተ የየራሱን ትርጉም እና ትንታኔ ምሰጥበት ብሆንም የችግሮቹን ምንጭ ኢትዮጰያ በ the Scramble for Africa ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን ከ አውሮፓውያኑ ቅኝ ገዢዎች ጋር በመተባበር ፈርማ የተገበረቻቸው ስምሚነቶች፣ ውሎች እና ሕግጋት ነቸው። በተለይም ድምበሮችን እና ድንበር ተሻጋር ተፈጥሯዊ መብቶችን በተመለከተ የኢትይጵያ ከአውሮፓውያኑ ቅኝ ገዢዎች ጋር የፈፀመቻቸው ስምምነቶች ንና ውሎች ናቸው። ለምሳሌ ፣ ግብፅ ግድቡን በተመለከተ ከኢቶጵያ ጋር ለመጨቃጨቅ መሰረታዊ መነሻዋ ዓፄ ሚኒልክ ተቀብሎ በመፈረም የተፈፀመው The Anglo-Ethiopian Treaty of 1902 የተባለው ስምምነት ነዉ። ስምምነቱም መሰረት የአባይ ወንዝ ውሃ ሙሉ ባለቤትነት ለግብፅ (ያኔ የብሪታንያ ቅኝ ተገዢ) የተሰጠ ነበር። አሁን ሱዳንን ወደ ኢትዮጵያ እንድትዘምት የደረገው  የሱዳን (ያኔ የብሪታንያ ቅኝ ተገዢ) እና እትዮጵያ ድንበር ጉዳይም በዝሁ ስምምነት ውስጥ የተካተተ ነበር።
ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ ቅኝ ገዢዎች ጋር ተፈራርማ በተገበረቻቸው የአፍሪካ አዋራጅ ስምምነቶች ክፋኛ የተጎዱት ኦሮምያ፣ ወላይታ፣ ስዳማ፣ አፋር፣ ኦጋደን ወዘተረፈ ብቻ ሳይሆን እነ ኬንያ፣ ሱዳን እና ኤሪትራም ናቸው። በተለይም በ The Hewett Treaty አንቀፅ III መሰረት ኢትዮጵያ ፈረንጆቹን በማገዝ ሱዳንን መውጋቷ እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው። ኢትዮጵያ በፈፀመችው አስነዋሪ  ድርጊትምክንያት ሱዳን የደረሰሰባትን በደል መቸም አትረሳም። ሱዳን በየThe Hewett Treaty አንቀፅ III ምክንያት የደረሰሰባትን በደል መካስ ትፈልጋለች፣ መብቷም ነው-የወጋ ብረሳ የተወጋ አይረሳም። በርግጥ ያኔ ሱዳኖቹ የንጉሱን አንገት ቆርጠው ወስደዋል፣ አሁን ግን አንገት ብቻ ሳይሆን አንጀትም ምያስቀሩ አይመስለኝም ።
የኢትዮጵያ አባቶች ይህን ሁሉ ክህደት ወንጀል በገዛ ወንድም እህት አፍሪካዊያን ላይ በፈፀሙት የፈረንጆቹን ነፍጥ ለመግዛት እና ከእነሱ ጋር ለመወዳጀት ነበር። ያንን ተጠቅመው ነበር የሚኒልክ ሃይል ኦሮምያ፣ ወላይታ፣ ካፋ፣ ስዳማ፣ አፋር ወዘተረፈ የወረሩት እና ከፈረንጆቹ ጋር በመተባበር የተቀራመቱት። በዝህ አይነት ወንጀሎች እና ክህደት ነው እትዮጵያ የተመሰረተች። ይህ ሳያንስ የእትዮጵያ ነገሥታት በአፍሪካዊ ማንነታቸው እጅግ አብረው እና ተሸማቀው አፍሪካዊነታቸውን በመካድ በግልፅ አወጁ፣ (1931 Ethiopian Constitution & 1955 Revised Constitution)ን አንብቡ።
ለዝህም ነው በ1900ዎቹ ከተመሰረተች ግዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለአንድም አስርተ ዓመት ሠላም፣ መረጋጋት እና እድገት ሳታይ ዛሬ ሞትን እየተጋፈጠች ነው ።
እና ይህ ሁሉ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጠንቅ መሆኗን አያሳይም???? በእርግጥም እምፓየርቷ ለሱዳንን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካም ጠንቅ ሆና ኖራለች።  በነገራችን ላይ ሰነዶቹን በሙሉ በአማርኛ ማግኘት ትችላላቹ።

ስለሆነም፣ ኦሮምያ፣ ትግራይ፣ ስዳማ፣ አፋር ወዘተረፈም ሆነ ከንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን በሎODP ላው ምሥራቅ  አፍሪካ ሰላም  እንድያገኝ ከተፈለገ ይህ ጠንቅ መወገድ ይኖርበታል።

2 Comments

  1. የመንግስታቱ ድርጅትን ሽፋን በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ የነበሩ 30 ሺህ ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር እና ጌጣጌጦች ስለተያዙ ዶላር በጥቁር ገበያና በመደበኛው ገበያ መካከል ያለው ልዩነት አስራ ስድስት ብር ገደማ መሆኑ ስጋት ሆኖ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች ገደብ እንዲንሳቀሱ ካልተፈቀደ የበጀት ድጎማ እንደማይለቀቅ የአውሮፓ ኅብረት አቋም በመሆኑ የአርብቶ አደር ፖሊሲዎች ሲዘጋጁ ኅብረተሰቡ ለራሱ ያውቃል ከሚለው መነሳት አስፈላጊ ሆኖ ሳለ በመቀሌ ከተማ በመሣሪያ የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች ሲታደኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ80 በላይ ንፁኃን መገደላቸው ሕዝብን አስቆጥቶ የአባገዳዎች የመቀሌ ጉዞ ፖለቲካዊ ሲሆን የሰሜኑን ፖለቲካ እንዳይነሳ ለመግደል የጅንታ ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ ስለሚችሉ የክልል ልዩ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊት ወይም ከፖሊስ ኃይል ጋር እንዲቀላቀል ኢዜማ መንግሥትን መክሮ ደምወዝ ላላገኙት የትግራይ ክልል የመንግሥት ሰራተኞችም  በአዲስ አበባ ከተሰማሩ 500 ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውስጥ ሁለት መቶዎቹ ስራ አቁመው በትግራይ ክልል ተወላጅ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የትግራይ ክልል ህዝብ እንዲያገለግሉ ስምሪት አሰጥተዋቸው እድር በመቀሌ በድምፅ አልባ መሣሪያዎች የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች በየመንደሩ ዝርፊያ እየፈጸሙ ቢገኙም የተከታዩን ትውልድ አቅም ለማጠናከር ተመድ ትግራይ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታ ፣ የኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይ ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል ከሶማሊያ ወታደሮቹን የማስወጣት እንቅስቃሴ እና ሱዳን ኢትዮጵያ የድንበር ግጭቱን እያባባሰች ነው በማለት ከሳ በትግራይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሊሞቱ ስለሚችሉ ሸገር ዳቦ 6 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 70 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አጋጠመው ብሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መግለጫ ማሕበራዊ ሚዲያውን ሲወቅስ የአሜሪካ መንግስት ማስጠንቀቅያውን ለዜጎቹ (WWW.USEmbassy.gov › et › security-alert…Web results Security Alert: Recent Reports of Robberies in Popular Hiking Areas in Addis Ababa | U.S. Embassy in Ethiopia – USEmbassy.gov ) በማስተላለፍ በእንጦጦ ፓርክ ፣ በየካ ሚኒሊክ ሆስፒቲታል/እንግሊዝ አስስ ፓርክ እና ጉለሌ የእጸዋት ማዕከል በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋ እና ጥቃት እየተፈጸመ ነው – አሜሪካ አትሂዱ በማለት የአፍሪካ ህብረትን እና የተመድ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን እንጦጦ እና ጉለሌ ወረዳዎች ልክ እንደ በኮንሶ ዞን ውስጥ ሰዎች መገደላቸውንና ቤቶች መቃጠላቸው እየተገለፀ በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ወደ ጎረቤት ሀገሮች የሚሄዱ ስደተኞች በዚምቧቤ በኮሮናቫይረስ ለመከላከል ዚምቧቤ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ያላዳረጉ 10ሺህ ዜጎቿን እያሰረች ቢሆንም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ከፈለገች ወታደሮቿን ማስወጣት አለባት ስላሉ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለ2013 ዓ.ም ምርጫ ስኬት በሃላፊነት ስሜት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ኢዜማ ፓርቲ እያሳበበ ባልደራስም እንደ ስብሃት ነጋ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው ለማለት ዳድቶታል፡፡

  2. Hats off Dannaboo Dhaqqabaa! The falling apart of Abyssinia (Tegaru+Amara neftengas) brutal colonial empire from East Africa is long overdue. Can you, please, link the documents you mentioned above? Thank you!

    ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ የምትበልጥ እንጂ የማታንስ ትልቅ የምታኮራ አገር ነች። ኦሮሚያ በኢትዮጵያ በግፍ ቅኝ የምትገዛ አገር እንጂ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም። እኛ ኦሮሞዎች በፍጹም ኢትዮጵያዊያኖች ሆነን አናውቅም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.