ነፍጠኞች ለምንድነው የኦሮሞ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብተው ዘመቻ የምከፍቱብን?

ነፍጠኞች ለምንድነው የኦሮሞ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብተው ዘመቻ የምከፍቱብን? 

ብርሃኑ ሁንዴ, Adooleessa 17, 2019

The Ethiopian army, with the order of Colonel Abiy Ahmed, on Sunday morning (January 13, 2019) started an aerial operation targeting areas in western Oromia believed to be he held by Oromo Liberation Army, OLA. (Africa News)

ከጥቂት ቀናት በፊት“የነፍጠኞች በኦሮሞ ማንነት ላይ ያላቸው ጥላቻ አሁንስ ከወሰን አላለፈም?” በሚል ጥያቄያዊ ርዕስ አንድ አጭር ፅሁፍ አቅርቤ ነበር። በዚያ ፅሁፍ ውስጥ ለነዚህ ሰዎች ትዕብትና ንቀት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ኦሮሞም የራሱን ሚና እንደተጫወተ በመጥቀስ፣ ይህንን ጉዳይ ግን በሰፊው እንደምመለስበት ጠቅሼ ነበር። በዚህኛው በዛሬው ፅሁፍ ውስጥ ይህንን ጉዳይ በሰፊው ለማቅረብ እሞክራለሁ። ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት ግን በቅድሚያ ለአንባቢዎች ግልፅ እንዲሆን የምፈልገው፣ እኔ ስለ ነፍጠኞች ሳነሳ እነዚህ ቡድኖች ወይም ኃይሎች መሰረታቸውና አመጣጣቸው ከአማራ ገዢ መደብ ቢሆንም፣ እነዚህ ባጠፉት ጥፋት ወይንም በምያደርጉት መጥፎ ድርጊት ሰፊው የአማራ ሕዝብ መጠየቅ እንደሌለበት ነው።

የኦሮሞ ጥላቻ (Oromo Phobia) ለምን እየጨመረ መጣ?

በመሰረቱ የኦሮሞ ጥላቻ የተጀመረው ዛሬ ሳይሆን ይህቺ እምፓየር ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ እንደሆነ ለታሪክ የሚተውለት ነው። እምፓየሯ የተመሰረተቸው የኦሮሞን ማንነት ለማጥፋት በሚል ዓላማ በመሆኑ፣ ዛሬ የእምፓየሯ መስራች ከሆነው መደብ የመነጩ የነፍጠኛ ልጆችና የልጅ ልጆች የአባቶቻቸውንና አያቶቻቸውን ድርጊት ብደግሙ የሚደንቅ አይደለም። የኦሮሞን ማንነት የሚያንፀባርቁትን ሁሉ ለማጥፋትና ኦሮሞን አንገት ለማስደፋት ለዘመናት ሲደረግ የነበረ ዘመቻ በኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) መቆም ቢችልም፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግን ይብዛ ይነስ እንጂ ተመሳሳይ ዘመቻ መደረጉ የቆመበት ጊዜ የለም። የኦሮሞ ትግል ፍሬ እያፈራና የተለያዩ ድሎች እየተመዘገቡ በሄዱ ቁጥር የኦሮሞ በተለይም የኦነት ጠላቶች እንቅልፍ ያጣሉ። በመሆኑም በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቅስቃሴና በተለይ ደገሞ በቄሮ መራራ ትግል እየታየ ያለው ለውጥ የኦሮሞን ጉዳይ ለዓለም በማሳየቱ፣ ነፍጠኞች በዚህ ደስተኞች አይደሉም። መሆንም አይችሉም። ስለዚህ በቅናት የተነሳም ይሁን በፍራቻ ጥላቻ መጨመሩ የሚታወቅ ነው።

ይህ ድፍረታቸው ከየት መጣ? ምክንያቱ ምንድነው?

ይህ ጥያቄ ወደ ፅሁፉ ዋናው ርዕስ ስለሚወስደን፣ የተለያዩ ጉዳዮችን እንደ ምክንያት ለማየት እሞክራለሁ። የመጀመሪያው የሚዲያ ጉዳይ ነው። የነፍጠኛ ልጆችና የልጅ ልጆች በድሮ ስርዓት ስር ገደብ የለሽ የትምህርት ዕድል በማግኘታቸው፤ በኢኮኖሚ በኩልም ከስርዓቱ ባገኙት ልዩ ጥቅምና ዘረፋም ጭምር ፋይናንሻሊ (financially) ጠንካራ በመሆናቸው፣ ቁጥር የለሽ ሚዲያዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር መገንባት ችለዋል።  እነዚህ ሚዲያዎችን ደግሞ እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዘመቻ በመክፈት ሌት ተቀን እየሰሩ እንደሆነ በግልፅ እየታየ ነው። ይህ ሞራላቸውን እጅግ ጨምሯል። ወኔም ሰጥቷቸዋል። ለሌሎች ያላቸው ንቀትም የሚመነጨው ከዚህ ነው ብዬ አስባለሁ። በዚህ ሚዲያዎቻቸው ጠቅላላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የምያሳምኑና ለመሰሪ ዓላማቸው ከጎናቸው ማሰለፍ እንደምችሉ አድርገው ነው የምያስቡት። ሚዲያ የሚጫወተው ሚና እጅግ ቁልፍ በመሆኑ፣ ይህ መሰሪ ድርጊታቸው በተወሰነ መልክና መጠን የሰራ ይመስላል። ይህ ደግሞ ወደ ሌለኛው ምክንያት ይወስደናል።

እንደሚታወቀው የኦሮሞ ሚዲያዎች ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ነው። ብዛታቸው ከኦሮሞ ሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ጭራሽ የማይመጥን ነው። በመሆኑም ልክ በጦር ሜዳ ተመጣጣኝ የጦር መሳሪያ ከሌለ፣ ሁለት በሚዋጉ ጠላቶች መካከል እኩል ድል መኖር እንደማይችል፣ በሚዲያውም ዓለም ሀበሾች የበላይ እጅ (upper hand) ስለምኖራቸው፣ በዚህ የተነሳ ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎችን ከጎናቸው ለማሰለፍ ጥሩ ዕድል ይኖራቸዋል። በተወሰነ መልኩ በዚህ በኩል የተሳካላቸው ይመስላል። ኦሮሞዎችም የራሳቸውን ነገር ከመውደድና ከማሳደግ ይልቅ የሀበሾችን ሚዲያ በመከታተል፣ አንደኛ  የነሱ ሚዲያዎች በይበልጥ እንዲያድጉ አስተዋኦ ስያበረክት፣ ሁለተኛ  በሀበሾች ሚዲያ አእምሮአቸው እንዲደነቁር ዕድል ይከፍታል። ይህ ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለትግላችንም እንቅፋት ይፈጥራል። እዚህ ላይ የማይደበቅ ሀቅ የሀበሾች ሚዲያዎችና የፊልም ኢንዱስትሪ ምን ያህል እያደገ እንደሆነ የማይታበል ነው። ይህ ደግም የሀበሾች በተለይም የነፍጠኞች የበላይነት መኖሩን ስለሚያሳይ፣ ሌሎችን እንዲንቁና አልፈውም በግልፅ እንዲሳደቡ ወኔ ሰጣቸው።

ሌላው መረሳት የሌለበት ጉዳይ የእምነት (ሃይማኖት) ጉዳይ ነው። እዚህ ላይ አንባቢዎች እንዲረዱ የምፈልገው፥ ማንኛውም እምነት በእኩልነት መከበር አለበት። ነገር ግን ከሌሎች በተለይም ከፖለቲካ ነፃ ካልሆነና በዚህ ጣልቃ ከገባ ችግር ነው የሚሆነው። የሀበሻን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ካየን፣ ይህ ሃይማኖት ከፖለቲካ ውጭ የሆነበት ጊዜ የለም ቢባል ሀሰት አይሆንም። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይህ ሃይማኖት ዛሬም እንደ ትላንቱ በኢትዮጵያ አንድነት ስም የተደበቀ ያንድ ብሔር የበላይነት እንዲታይ እየሰራ መሆኑ ይስተወላል። “ሰው ውሎውን ይመስላል” እንደሚባለው፣ በዚህ ሃይማኖት ምክንያት ከሀበሾች ጋር ትስስር ያላቸው አንዳንድ ኦሮሞዎች ማንነታቸውን እንኳን ጥያቄ ውስጥ ያሚያስገቡበት ሁኔታ ይታያል። በተለይም ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ያላቸው አመለካከት ጥሩ አይደለም። ይህም ነፍጠኞች ለኦሮሞ ላላቸው ንቀትና ጥላቻ የተወሰነ አስተዋፅኦ ያበረክታል። በማህበራዊ ኑሮ በኩልም ሲታይ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚታየው። ሰው ውሎውን ይመስላል የሚባለው እዚህም በደነብ ይሰራል ማለት ነው። “Bakka oolte natti himi, eenyu akka taate sittin hima” የሚለውም የኦሮሞ ተርት እዚህ ላይ ይሰራል።

በስተመጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ሌላው ምክንያት የፖለቲካ አመለካከትና የአይዶሎጂ ጉዳይ ነው። እጅግ የሚገርመው ኦሮሞም ሆነው የኦሮሞ ነፃነት ትግልን ዓላማ ያላወቁ ወይንም መረዳትም የማይፈልጉ በመኖራቸው፣ የዚህ የነፃነት ትግል ዓላማ ልክ አገርን ለማፈራረስ እንደሆነ ስለሚያቀርቡ፣ በዚህ በኩል ለጠላቶቻችን አጋር ይሆናሉ። ይህም ለነፍጠኞች ወርቃማ አጋጣሚ ነው። ለዚህ ብዙ ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠትና የተለያዩ ምሳሌዎችን ማቅረብ ቢቻልም፣ ይህንን ጉዳይ በሌላ ርዕስ ለማቅረብ እሞክራለሁ። እንግዲህ የዛሬውን ፅሁፍ ለማጠቃለል፣ ለነፍጠኞች ትዕብትና ንቀት የኦሮሞም አስተዋፅኦ እንደሚኖር ከላይ ከተጠቀሱት አንዳንድ ጉዳዮች መረደት ይቻላል ብዬ አምናለሁ።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት።

1 Comment

  1. Amara and Oromo is made to quarrell each other by TPLF.TPLF doesn’t want to get attention directed to the common enemy of Amara and Oromo the TPLF.
    Just a decade ago there were only 66 billions of Birrs worth cash that were printed By EPRDF, now a decade later there are said to be 789 billions of birrs that are printed by EPRDF.

    The cash printed by EPRDF got 11 folds higher in just a decade .
    Diasporas dollar is the only thing that will finish the GERD DAM CONSTRUCTION.

    https://addisfortune.news/two-overseas-firms-seal-deal-to-print-banknotes/

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.