አዲስ ድርጅት? ኦሮሞ ዳግም መታለል የለበትም

አዲስ ድርጅት? ኦሮሞ ዳግም መታለል የለበትም

ብርሃኑ ሁንዴ, Onkoloolessa 18, 2019

ኢትዮጵያ – Ethiopia from in side, via Elemo AbaNega AbaMecha

በዚህ ርዕስ ይህንን አጭር ፅሁፍ እንዳቀርብ ያነሳሳኝ ቅርብ ጊዜ በኦቦ ጀዋር መሃመድ በFace Book ላይ በኦሮምኛ የቀረበው ፅሁፍ ነው።

ያዚያ የጀዋር ፅሁፍ ርዕስ ADWUI: BAQSUU MOO DIMOKRAATESSUU WAYYA? የሚል ሲሆን፣ ይዘቱ ኢሕአዴግን (EPRDF)ን አፍርሶ ሌላ ድርጅት ስለ መመስረት ነው። በፅሁፉ ውስጥ ጀዋር ስለ ብዙ ነገር በስፋትና በጥልቀት አስቀምጧል። በዚህ አዲስ ድርጅት ማቋቋም ሂደት ውስጥ መሰረታዊ ችግሮች ምን ልሆኑ እንደምችሉ፤ ለኦሮሞ፣ ለኦዴፓ፣ ለኢሕአዴግ ራሱ፣ ለብሔሮችና ብሔረ ሰቦች እንደዚሁም ባጠቃላይ ለአገሪቷ ምን ዓይነት ችግሮች ልፈጠሩ እንደምችሉ፤ የነዚህ ችግሮች መፍትሄ ምን መሆን እንዳለበትም ጀዋር በደንብ ተንትኖ አቀርቧል። በዚህኛው የዛሬ ፅሁፌ ውስጥ ይህንኑን አዲስ ድርጅት መመስረትን በሚመለከት አስተያየቴን አቀርባለሁ።

ጀዋር ባሁኑ ጊዜ ስላለው ሁኔታና የኢሕአዴግን ውስጥ በሚገባ ስለሚያውቅ፣ ስለ ብዙ ነገር በጥሩ ሁኔታ ያብራራ ይመስለኛል። ስለወቅቱ ሁኔታ ከጀዋር የበለጠ የሚያውቅ ሌላ ሰው ይኖራል ብዬ ማሰብ ያስቸግረኛል። ስለዚህ ጀዋር የፃፈውን አምናለሁ። በፅሁፉ ውስጥ ጀዋር አንድ ነገር ጠቅሶ ነበር። ይኸውም ወደ አማርኛ ሲተረጎም፥ ጠ/ር አብይ ለኦሮሞ ፖለቲካ አዲስ ነው” የሚል ነበር። እኔ እንደማስበው ግን የኦሮሞ ፖለቲካ ለአብይ አዲስ ሆኖ ሳይሆን፣ ጠ/ር አብይ የኢትዮጵያዊነት አይዶሎጂ ስላለው፣ ለኦሮሞ ፖለቲካ ደንታ ያለው አይመስለኝም። በነገራችን ላይ ዶ/ር እታና ሀብቴ አንድ ወቅት የተናገረው ትዝ ይለኛል። እሱም፥ አብይ አህመድ እኛ ነን ኦሮሞ ነው የምንለው እንጂ እሱ እኔ ኦሮሞ ነኝ ማለት አይፈልግም”  የሚል ነበር። ይህ እውነት ይመስለኛል። ለምን ከተባለ፣ አብይ በኦሮሞነቱ የሚኮራ ቢሆን ኖሮ፤ ኦሮሙማ በደሙና አጥንቱ ውስጥ ቢኖር ኖሮ፣ የኦሮሞን ብሔርተኝነት አሳንሶ ባልተናገረ ነበር።

አሁን ጉዳዩ ያ አይደለም። አብይ የፈለገውን ያስብ፤ በሚፈልገው ነገር ይመን፤ የሚፈልገውንም  ይመኝ ወይንም ያድርግ፤ ነገር ግን ኢሕአዴግን አፍርሶ ሌላ አዲስ ድርጅት የማቋቋሙ ሀሳብ ከሱ የመነጨና በሱም የታቀደ ይመስላል። ይሁን እንጂ ጀዋር እንዳለው ኢሕአዴግን አፍርሶ unitary የሆነውን ድርጅት መመስረት ለብሔሮችና ብሔረ ሰቦች ችግር ሲፈጥር፣ በተለይ ደግሞ ለኦሮሞ በይበልጥ ትልቅ ችግር ይፈጥራል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ የፅሁፌ ርዕስ እንደሚገልፀው፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ኦሮሞ ዳግም መታለል የለበትም። ኦዴፓ(ODP) አብይን ፈርቶ ወይንም ደግሞ አብይን ለማስደሰት ብሎ ራሱን አፍርሶ አዲስ በሚመሰረተው ድርጅት ውስጥ መቅለጥ ከፈለገ፣ ይህ የራሱ ችግር ነው። ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኦሮሞ ሕዝብ መለየቱ ነው። በኦሮሞ ሕዝብ ሲጠላ እዚህ ከደረሰው ባሻገር ተተፍቶ ሊወረወር ነው ማለት ነው። ይህ የራሱ ጉዳይ ነው። ነገሩ እንደ ኦሮሞ ተረት ጨው ላራስህ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሃል” ሊሆን ነው።

አጫጭር መልዕክቶች ለሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ፣ ለቄሮና እንደዚሁም ነፃ ለሆኑት የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች

የኦሮሞ ሕዝብ ባጠቃላዩ ያለበትና በተለይ ደግሞ በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ ሕዝባችን ያለበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ እያለ፣ ሌላ አደጋ ሊመጣብን ስለሆነ፣ እኔ እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ ከዚህ በታች ያለውን መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።

ለሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ

ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ፥ በዚህ ፀረ ኦሮሙማ በሆነው ተንኮልና ደባ እንደዚሁም በጠ/ር አብይና ኦዴፓ ድርጊት አትታላል። ይህ አዲስ ሊመሰረት የታቀደው ድርጅት ከሚያመጣልህ ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን፣  ይህንን አትመን። አስከ ዛሬ ድረስ በልጆችህ ደምና አጥንት ያገኘሃቸው ድሎች ሊፈርሱብህ ነው። ይህ ፀረ ኦሮሞና ኦሮሙማ ስለሆነ፣ በንቃት ጉዳይህን ጠብቅ። ዳግም አትታለል። የአገር ባለቤትነትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ትግልህን አታቁም። የመጨረሻ ድል ያንተ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።

ለቄሮ ኦሮሞ

መራራ ትግል አካሄደህ፤ በሺዎች የሚቆጠሩትን ወንድሞችህንና እህቶችህን አጥተህበት፤ ወያኔዎችን አንበርክከህ ይኸው የለውጥ አየር እንዲመጣ አድርገሃል። ይሁን እንጂ አንተ ባስገኘኸው ድል ሌሎች ኃይሎች እየተጠቀሙበት ነው። አንተ አንግበህ የተነሳኸው የኦሮሞ ጥያቄ አንድም መልስ አላገኘም። ይህ ቀርቶ እንዲያውም የኦሮሞ ነፃነት ትግል (ኦነት) እስካሁን ያስመዘገባቸው ድሎችም እንዲፈርሱ ተንኮልና ደባ እየተሰራ ስለሆነ፣ በንቃት ተነስና ድሎችህን ጠብቅ፤ የቀረህንም ለማግኘት ትግልህን ቀጥልበት እንጂ በሌላ ነገር አትታለል።

ነፃ ለሆኑት የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች

በመካከላችሁ ከተፈጠሩት የአመለካከት ልዩነቶች የተነሳ ጥቃቂን አለመግባባቶችና ትንንሽ ችግሮች በመካከላችሁ ብኖሩም ለአንድ ዓላማ እንደምትቆሙ ተስፋ አደርጋለሁ። የኦሮሞን ብሔራዊ ፍላጎት (Oromo National Interest) ለመጠበቅና ለማስጠበቅ አንድ አቋም አንዳላችሁ ጥርጥር የለኝም። ተቀላቅላችሁ ባንድ አመራር ስር አንድ ድርጅት መሆን ብያዳግታችሁ እንኳን፣ ለጋራ የኦሮሞ ጉዳይ ተባብራችሁ በጋራ እንድትሰሩ፤ ኦነት እስካሁን ያስመዘገባቸውን ድሎች በጋራ እንድትጠብቁ፤ እየተቃጣብን ያለውን አደጋ በጋራ ለመቋቋም በህብረት እንድትሰሩ፤ ኦሮሞና ኦሮምያ አደጋ ውስጥ ኣንዳይገቡ ሕዝባችንን አንድታደራጁና የኦሮሞን ኃይል እንድታጠናክሩ ወንድማዊ መልዕክቴን ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ።

ድል ለኦሮሞና ለሌሎች ጭቁን ሕዝቦች!! የነፃነትና ፍትህ ትግል ይቆይ ይሆናል እንጂ ከግቡ ሳይደርስ አይቀርም።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት።

 

2 Comments

 1. Well articulated, Brehanu Hundee!

  This is a timely call of wakeup for the Oromo and other nation nationalities! I read your article and Jawar Mohammed’s well thought piece, in which he assesses the reality on the ground carefully, and warns the Oromo people in particular and other nation nationalities in general about the brewing disaster, wrapped in the proposed merging of EPRDF. Although, as I always confess, I am not in a position to fully assess what is really happening on the ground back at home, I share your concerns that the Oromo people and other historically subjugated nation nationalities will be the losers if the said merger is effected any soon. To start with, there is no level playing field in which historical wrongs are corrected and those who have been benefiting from a century and half old one-sided polity and those who have been on the periphery can play fairly. We must keep in mind that the neftegna and neo-neftegna , who are controlling the country’s resources, including media and federal government bureaucracy, instead of taking responsibility for their fathers crimes and trying to redress historical harms, are still braying to justify their crimes. There is no guarantee that they would not repeat their fathers crimes on the Oromo and other nation nationalities if they get the opportunity.

  Let me be clear that the sufferings EPRDF had subjected our people and other nation nationalities for three decades is unforgivable, and its demise is most welcome. Nevertheless, the neftegna and neo-neftegna are more guilty in creating the historical injustices the peoples of Ethiopia have been subjected to, and their coming back is more disastrous than the misery caused by the EPRDF. They conditioned TPLF leaders into carrying out neftegna wishes and worked behind the scenes to inflict more harms on the Oromo and others, using EPRDF long arms. That is, EPRDF’s crime cannot cleanse the crimes of the neftegna and bring them forward as angels. The proposed unholy merger with neftegna and neo-neftegna dominated entities may mean that the history of betrayal and deception is going to repeat itself, eroding the relative gains made by the subjugated peoples of Ethiopia and reincarnating the old system, or creating fertile grounds for the neo-neftegna to impose themselves on the Ethiopian peoples.

  George Orwell, in his book titled ‘Animal Farm’, depicts how on the road from revolution to tyranny, the would be victims silently follow the new masters into their own demise and end up in similar situations to what they experienced prior to their revolution . The story in the book goes: “the animals on Farmer Jones’s farm rise up and chase him away. They plan to run the farm themselves, for their own benefits. At first, the animals are able to work together and support each other. Gradually, however, the pigs begin making helpful suggestions about how the farm should be run. Before long, the pigs are at the top of the social ladder and the rest of the livestock are wondering what happened. …. As the pigs grow more powerful, they find a number of animals who seem willing ” to obey and follow even though they knew that it will have dire consequences for them and other animals. The story in the novel narrates human conditions, using animal characters and exposes how “comrades” might deceive their fellow revolutionaries and become tyrannies, often winning their victims over to follow them into their own disasters.

  ODP rank and file as well as other politicians who have the opportunity to avert the impending disastrous outcome for the Oromo, Somali, Sidama, Tigrawi, Affar, Agaw, Qimant, Gumuz, Hadiya, Walayita, Kambata, etc., must stop and think, listen to their conscience, put the interests of their constituents first and discharge the responsibilities they have on their shoulders. Particularly, the Oromo, qeerroo and qarree must read between the lines. The matter at hand may have more serious consequences than the past untold sufferings our people had been subjected to. Since going into merger before righting historical wrongs and creating even playing platform means justifying the genocides and ethnic cleansing carried out by neftegna, the marriage may equate to licensing the neo-neftegna to use the resources they have looted for a century and half as well as the upper hand they have gained, employing unjustifiable means.

  Therefore, the ODP must firstly discharge their obligations by answering Oromo fundamental questions and serving the interests of their constituents. ODP officials and members must avoid being gullible and echo chambering their possibly misguided superiors, and stand for their people and use their conscience to judge every steps of their political moves. They must be guided by the interests of their people. Above all, qeerroo and qarree must stay united and ascertain the objectives for which your bright comrades sacrificed for. No unconditional support be given to any political party or group; you are the bosses who can dictate the future of your people. Organize yourselves and promote leaders among yourselves and continue to shape the direction that country must take. Similarly, the great Oromo people and other nation nationalities, must beware of any manipulation and deception to bring back the neftegna to power through the back door. Any rhetoric of unity or merger must be preceded by the neftegna and neo-neftegna coming out and apologizing to the Ethiopian peoples for the crimes of their fathers and their own roles in subjugating others. They must acknowledge the genocides and ethnic cleansing carried out in the name of the country and sincerely reassure nation nationalities that cruelty is not going to be repeated in that country.

  No more deception! “In politics, being deceived is no excuse”!

  OA

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.