ኦሮሞነት እና የኦሮሞ ብሔርተኝነት vs  የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት እና አማራነት

ኦሮሞነት እና የኦሮሞ ብሔርተኝነት vs  የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት እና አማራነት

ብርሃኑ ሁንዴ, Bitootessa 29, 2020

በርዕሱ ላይ በጥንድ ሁለት ቦታ የተቀመጡት እነዚህ ጉዳዮች ተቃራኒዎች እንደሆኑ ከመግለፅ በፊት እስቲ ፊቺአቸውን ባጭሩ እንይ። ኦሮሞነትም ሆነ አማራነት ሁለቱም ሶስት ምሰሶዎች (pillars) አላቸው። እነዚህ ምሰሶዎች ደግሞ ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ናቸው። እነዚህ ሶስቱ አንድ ላይ ከታዩ ደግሞ ማንነትን (Identity) ይገልፃሉ ማለት ነው። ባጭሩ ኦሮሞነትም ሆነ አማራነት ሁለቱም የብሔሩ መገለጫዎች ናቸው። የኦሮሞን ብሔርተኝነትና የኢትዮጵያን ብሔርተኝነት ካየን ግን የኦሮሞ ብሔርተኝነት እነዚያን ሶስት ምሰሶዎችን በደንብ ማወቅ፣ ማክበር፣ መውደድና ለነዚህ ደግሞ ቅድሚያ መስጠት ነው። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለበት ጉዳይ የራስን ነገር በድንብ ማወቅ፣ መውደድና ለዚህ ቅድሚያ መስጠት ማለት የሌላውን መጥላት እንደልሆነ ነው። ይህ በይበልጥ የኦሮሞን ብሔርተኝነትን ይመለከታል።

ይሁን እንጂ የኦሮሞን ብሔርተኝነትና የአማራን ብሔርተኝነት ወይንም የኢትዮጵያን ብሔርተኝነት ጎን ለጎን ይዝን ካየን፣ የአማራ ብሔርተኝነትና የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያንድን ብሔር ፍላጎት ከዚህም አልፈው ያንድን ብሔር የበላይነት እንደሚያንፀባርቁ ብዙ መስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ቢታመንም ባይታመንም፣ ቢወሰድም ቢተውም የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ሌላ ቀለም ለብሶ የሚቀርብ የአማራ ብሔርተኝነት ነው። ውስጣቸው አንድ ነው። ፍላጎታቸውም አንድ ነው። ስለዚህ የአማራን ብሔርተኝነትና የኢትዮጵያን ብሔርተኝነት ለይተው ማየት ኣለማስተዋል ነው። የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት የአማራ ብሔርተኝነትን ስራ ላይ እንዲውል የሚጠቀሙበት ስልት ነው። በኢትዮጵያ ስም የአማራን ማንነት በብሔሮችና ብሔረሰቦች ላይ መጫን የሚደረግ ሙከራ ነው።

አዚህ ላይ ይህንን ጉዳይ ለማይረዱት ለማብራራት ያህል፣ ኦሮሞነትንና የኦሮሞን ብሔርተኝነትን ጎን ለጎን ይዘን ካየን ደግሞ የኦሮሞን ብሔርተኝነትን እንደ ጠባብነት የምመለክቱት ስላሉ ይህ ፍፁም ስህተት ነው። የኦሮሞ ብሔርተኝነት የኦሮሞነት ከፍተኛው የእድገት ደረጃ ነው። የኦሮሞ ብሔርተኝነት ባጭሩ በኦሮሞነት መብሰል ነው። ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ኦሮሞነትን መውደድ፣ ማክበርና ለዚህም ቅድሚያ መስጠት ነው የኦሮሞን ብሔርተኝነት የሚያሳድገው። እንደተባለው የኦሮሞ ብሔርተኝነት የኦሮሞነት ከፍተኛው የእድገት ደረጃ ነው ቢባል ሀሰት አይሆንም። ኦሮሞ ሆኖ መወለድና ኦሮሞነትን ማወቅ ትልቅ ልዩነት ኣላቸው። ስለዚህ እገሌ የኦሮሞ ብሔርተኛ ነው ወይም ናት፤ እገሌ ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኛ አይደለም ወይም አይደለችም ይባላል እንጂ በተፈጥሮ የሚገኘውን ኦሮሞነትን ላንዱ መስጠት ወይንም ካንዱ መቀማት አይደለም።

በኦሮሞ ብሔርተኝነት ላይ የሚዘመትበት ዋናው ምክንያትም የኦሮሞ ብሔርተኝነት ኦሮሞነትን ስለሚወድና ለዚህም ቅድሚያ ስለሚሰጥ ነው እንጂ ፕሮፓጋንዳ እንደሚደረገው የኦሮሞ ብሔርተኝነት ለዚህች አገርም  ሆነ ለብሔር ብሔረሰቦች አደጋ ሆኖ አይደለም። የኦሮሞ ብሔርተኝነት የኦሮሞን ሕዝብና ብሔር ፍላጎት ለማሟላት ወሳኝ ቁልፍ ቢሆንም፣ የሌሎችን ፍላጎት ይፃረራል ማለት ትልቅ ስህተት ነው። ይህቺን አገር ያፈርሳታል የሚባለውም ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳና ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር ሀቅ አይደለም። የኦሮሞ ብሔርተኝነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዋያኔ የበላይነት አገዛዝ ያላቀቅ እንደሆነና የለውጥ አየር በዚህች አገር እንዲነፍስ አንዳደረገ እንዴት ይዘነጋል?? ይህ እኮ በመሬት ላይ ያለ እውነታና ዓለምም የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ኦሮሞዎች ለምን የኢትዮጵያን ብሔርተኝነትን እንደምያሞግሱና የኦሮሞን ብሔርተኝነትን እንደምኮንኑ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

ተመልሰን እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት።

2 Comments

  1. The EAL’s planes can be used to house the homeless and also other unused EAL’s warehouses can be used to house the homeless Ethiopians. The homeless should live inside the planes rather than letting the homeless stay outside spreading the virus within the society .

    Also the Airlines should soon consider renting out the airplanes to the highest bidders who wish to use the planes as their fully secured personal residences guaranteed to be immune from burglary , guaranteed to be immune from racism and guaranteed to be immune from xenophobia.

    All the planes need is a simple bath room and a simple kitchen put next to it, then many dollar billionaires will like to live in the planes for security reasons.

    EAL should not sell the planes or other assets of EAL, as rumors circling around the Federal Government and the EAL insiders are indicating about the intentions to sell the EAL’s assets including the EAL’s planes should be halted ASAP , renting the planes out to the dollar billionaires in Ethiopia can help the economy maintain a constant income afloat in the loop with the economic gain in long term cycles benefiting the organization rather than selling the planes at one time .

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.