ከጭቆና ስር መዉጣት የሚቻለዉ ጨቋኝን ኣንበርክኮ እንጂ ለጨቋኝ ተንበርክኮ ኣይደለም!

ከጭቆና ስር መዉጣት የሚቻለዉ ጨቋኝን ኣንበርክኮ እንጂ ለጨቋኝ ተንበርክኮ ኣይደለም!

በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ኣጭር መልዕክት ለኦሮሞ ህዝብ

ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ ጥር 27, 2020

Duula Gurguddaa Walloo siyaasaa adda Lafa Ajjeechaan Qeerroo uummataበታሪካችን ዉስጥ እጅግ በጣም ዘግናኝ እና ኣስቀያሚ የነበሩ ጭቆናዎችና በደሎች ደርሰዉብን እኛም ስንቃወማቸዉ የነበረበት ሁኔታ ኣሁንም በዘመናችን በሕይወት እያለን በኣዲስ መልክ እየተመለሱብን ነዉ። በሚኒሊክ ዘመን በሌሎች የኦሮሞን ህዝብ ለማስገበር በሚፈልጉ ኣካላት የኦሮሞ ህዝብ እርስ በራሱ ከተከፋፈለ በዃላ ኣንድ በኣንድ በጠላት በመመታት በመጨርሻ ሙሉ በሙሉ በነጮች በሚደገፈዉ የኣቢሲኒያ የቅኝ ግዛት ስር ለመዉደቅ መገደዱ የሚታወስ ነዉ። ያለፈዉ ችግር እንደ ዛሬ እንደ ታሪክ የሚናወራዉ ጉዳይ ብ ቻ መሆኑይ ቀርቶ ዛሬም እንደ ኣዲስ ተመልሶ ሲመጣብን ማየት እጅግ ኣሳፋሪ ጉዳይ ነዉ። ዛሬ የሚንኖርባትን ሃገራችንን ኣባቶቻችን ለመናገር እንኳን የሚከብድ ታሪክ ዉስጥ ኣልፈዉ ነዉ ያስረከቡን። በዚህ ሰኣት ግን ከኣባቶቻን በኣደራ የተረከብናትን ሀገር ኣደራችንን ጠብቀን ለመጪዉ ትዉልድ ማስተላለፍ ቀርቶ መጪዉ ትዉልድ የሚጠብቅብንን ኦሮሚያን እስከእነ ክብሯ ሳይሆን ቅኝ ገዚዎቻችን እንደሚፈልጉት ተከፋፍለን ለታሪካዊ ዉርደት እየተዘጋጀን ነዉ። በዚህ ወቅት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ጭቆና እና መከራ መግለጽ እንኳን ይከብዳል።

በተለይ በተለይ ከሚኒሊክ ዘመን ወዲህ ኦሮሞን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ታቅዶ በሰፊዉ ወደ ስራ የተገባበት ዘመን ይህኛዉ ዘመን ነዉ ብንል ማጋነን ኣይሆንም። ይህንን እቅድ ለማሳከት ጥንት ሚኒሊክ የኦሮሞን ህዝብ በተንኮል ከፋፍሎ በማዳከም ቀስ በቀስ እጅ ሲያሰጥ እንደነበረዉ ሁሉ ዛሬም ብልጽግና ብሎ ራሱህን የሰየመዉ መንግስት ነኝ ባይ የሽፍታ ቡድን በምእራብ ኦሮሚያ በተለይም በኣራቱ የወለጋ ዞኖች እና በደቡብ ኦሮሚያ በሁለቱ የጉጂ ዞኖች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል።

ይህ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ላይ ክትትል ማድረግ በሚል ሰበብ እየተደረገ ያለዉ ኦሮሞን የመስበር ዘመቻ ሁለት ኣመታትን ኣስቆጥሯል። እነዚህ ሁለት ኣካባቢዎች ከሌላዉ የኦሮሚያ ኣካል ለብቻቸዉ በመነጣል በወታደራዊ ኣገዛዝ ስር እየተገዙ መሆናቸዉ ሃገሪቱን እንኳን እያስተዳደርንብት ነዉ ከሚሉት የህገ መንግስት ጋር ራሱ የሚጣረስ ነዉ።

ታሪክ ራሱን ደገመ። ሚኒሊክ የኦሮሞን ህዝብ እየጨፈጨፈ በነበረበት ወቅትም ለሚኒሊክ ኣቅምና ጉልበት ሆነዉ የነበሩት ከሚኒሊክ የባሪነት ቀምበር ሰር መዉጣት ባማይፈልጉ የኦሮሞ ከሃዲ ልጆች ሲሆን በዛሬም ጊዘ ይኸዉ የኦሮሞ ህዝብ እያለቀ ባለበት ሁኔታ ዉስጥ የኦሮሞን ህዝብ ድምጽ በማፈን ለጨፍጫፊዉ መንግስት እዉቅና እየሰጡ ይገኛሉ። የመንግስትን ከፋፍለህ ግዛ ክፉ እቅድን ለማሳካት የፖለቲካ ወጥመድ ዘርግተዉ ህዝባችን ኣንዱ ለኣንድ ደራሽ እንዳይሆን ላማድረግ የተንኮል ሴራቸዉን እየሸረቡ ይገኛሉ። በሚኒሊክ ዘመን ኣንዱ የኦሮሞ ክፍል በጠላት ሲወጋ ሌላዉ ደግሞ የራሱን የግሉን ጉዳይ ሲያካሄድ በዃላ ሁሉም ኣንድ በኣንድ በየተራ ሲበላ ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ ኣሁንም በምእራብ እና በደቡብ ኦሮሚያ ጠላት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት ከፍቶ እያለ በሌላዉ በኩል ደግሞ በሌላዉ የኦሮሞ ኣከባቢዎች ምንም እዉነተኛነትና ህጋዊ መሰረት ለሌላዉ ምርጫ ምረጡኝ በማለት የህዝቡን ትኩረት የሚበትኑ የፖለቲካ ቡድኖች ሚና ይኸዉ የኦሮሞን ህዝብ ከፋፍሎ የማስመታት ዘመቻ ኣካል እንደሆነ እያየን ነዉ። ህዝቡም ትኩረቱ በዚህ በመጠመዱ በምእራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ እየተጨፈጨፈ ላለዉ ህዝቡ መድረስ ኣቅቶታል።

ሌላዉ ቢቀር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኦሮሞ ተማሪዎች እንኳን ተለይተዉ የዬት ኣካባቢ እንደሆኑ እየተለዩ እየተባረሩ ያሉበት ሁኔታ እያለ ብዙዉ ህዝብ በዝምታ እየተመለከተ መሆኑ ኣስደናግጭ ነዉ።

ዛሬ ወለጋ እና ጉጂ ዉስጥ የኦሮሞን ህዝብን እየፈጀ ያለዉ ጠላት ነገም ለሌላዉም ኦሮሞ የሚምለስ እንደማይሆን መታወቅ ይኖርበታል። በዚህ ኣስቸጋሪ ወቅት በኣንድ ቀን ስለተገደሉት 89 የኦሮሞ ልጆች ትንፍሽ ሳይሉ ስለሌላ ጉዳይ የሚቀባጥሩ በኦሮሞ ህዝብ ስም የቆሙ ሚዲያዎችም የዚህ ታሪካዊ ዉድቅት ኣካል መሆናቸዉ መዘንጋት የለበትም። የፖለቲካ ቡድኖች ግለሰቦች እና ቡድኖች የህዝባችንን ሞትና ሲቃይ በቸልታ የሚመለከቱ ከሆነ የቆሙት ለማን እና ለምን ኣላማ እንደሆነ ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባቸዉ መሆኑን ተረድተዉ ለህዝባችን ድምጽ ከመሆን ኣልፈዉ በተጨባጭ ከህዝባችን ጎን ቆመዉ ይህንን ክፉ ጠላት እንዲጋፈጡ ጥሪ እናቀርባለን።

እየደረሰብን ያለዉንም ጭቆና እና በደል ጣላትን በመለማመጥ ሳይሆን ጠላትን ተጋፍጦ ታግሎ በመጣል መሆኑን ሁላችንም ተረድተን በጋራ ሊያጠፋን የተነሳዉን ጠላት ለማጥፋት እንዲንነሳ ጥሪያችንን እናቀባለን።

በዚህም መሰረት የጠላት መጠቀሚያ ሆነዉ ህዝባንን ለማጥፋት እየዋሉ የሚገኙትን ማንኛዉም ሃብታችንንም ሆነ የኣገልግሎት ተቋማት ከጠላት መጠቀሚያ ነጻ ለማድረግም እንደምንቀሳቀስ መታወቅ ይኖርበታል። ይህንንም ለማድረግ ከመላዉ ኦሮሚያ የህዝባችንን ምርት ጭነዉ ወደ ትላልቅ ከተሞች የሚጓዙ ተሸከራካሪዎች ፍንፍኔን ጨምሮ ኣቅርቦት ማቅረብ እንዳይችሉ እስከማገድ ደረስ የተለያዩ እርምጃዎችን ለመዉሰድ መዘጋጀት ይኖርብናል። ስለዚህ በመላዉ ኦሮሚያ የሚገኘዉ ህዝባችን በቁጨት ህዝባንን እየገደለ ያለዉን ጥላት ለማን በርከክ በምናደርገዉ እልህ ኣስጨራሽ ትግል ላይ ከጎናችን በመሆን ትግሉን እንዲያፋፍም ጥሪ እናቀባለን።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ
ከቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ
ጥር 27, 2020
ፊንፍኔ; ኦሮሚያ

1 Comment

  1. Yaa qerroobiliisuummaa Esa jirtu?
    Yaa warra Dina jilbeefachiise,hardha,gurmuunkesan kaleesaa,Esa dhaqe?Fulakenya durattii inniikaleesaa,hardhas yeroo nuttii debi’u attam tana.Warrii kaleesaa falmmee asiin gahe.Ammas garbbummaa,dhaloota dhaalchiisuuf tessu?Enyuun egdu,maaliis abdattulaata.Barabaraan immimmaan cuphsuun,rorriifamuun,yoom nugaha laata.Jagamaa kelloos ummata Baaleerratti kanuma raawatee.Gobana Daacees,akkasuuma. Numakesaa baheetu dina nuttii ta’e.Kanaaf yeroo meqa gowoomnu?Hamayoomiittiis haaboonyu? Fala barbaada.Gurmmukeesan debiisa.Diinaaf gahiinjeedhiina.Xumuura Diddaa Garbbuumma isadhugaa,Isa dubattii hindeebiine, rorroofi garbbuummaa dhabamsiisee,walabummaaf walqiixuumaa labsu,kan gantuufii xawalwaalee balleesu,Oroomof Oroomiiyaa biliisa baasu karoorsaa,xumuuras ittiigodha. Horaa Bulaa!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.