የሌላውን ማንነት ከማያከብሩት ጋር እንዴት የጋራ አገር መስርተው አብሮ መኖር ይቻላል?

የሌላውን ማንነት ከማያከብሩት ጋር እንዴት የጋራ አገር መስርተው አብሮ መኖር ይቻላል?

ከብርሃኑ ሁንዴ, ሚያዝያ  9, 2019

ESAT anti-Oromo daily propagandists and fake news producers

በኦሮሞና በሀበሾች መካከል ምን ያህል ልዩነቶች እንዳሉ ለማሳየት ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ኢትዮጵያ በሚትባል አገር ውስጥ የነበሩትንና ያሉትን የፖለቲካ አካሄድ ካየን፣ ኦሮሞ እየተሰደበ፣ እየተናቀ፣ እየታሰረና እየተገደለ በሚገኝበት ሁኔታ ውስጥ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን ለዚህች አገር መስዋዕትነትን ሲከፍሉ ቆይተዋል፣ ዛሬም አንደዚያው ስንከራተቱ ይታያሉ። በተቃራኒው ግን ሀበሾች በተለይም የነፍጠኛ ዘሮች ስራቸው ሁሉ በተንኮልና ደባ የተሞላ በመሆኑ፣ ኦሮሞ ምንም ያህል ብተባበራቸውና ብሰራላቸው እንኳን ለኦሮሞ ያላቸው ንቀት፣ ጥላቻና ፍራቻ እንደድሮው ነው። ምንም የተቀየረ ነገር የለም። እንዲያውም ባሰበት ቢባል ሀሰት አይሆንም። አንዳንድ ጊዜ ሳሰብ እውነትም ኦሮሞ የዋህ ነው የሚባለው እውነት ይሁን እንዴ ብዬ ራሴን እጠይቃለህ። የሚገርመው ግን ኦሮሞ ለምን ከታሪክ መማር እንደሚያዳግተው ነው።

ለአንድነት የሚሰጠው ትርጉም ወይም አመለካካት ብለያይም፣ በመሰረቱ በአፍም ቢሆን ከነፍጠኞች በላይ ስለዚህች አገር አንድነት የሚያወራ የለም። ኦሮሞ ግን ለአገሪቷ አንድነት ስጨነቅ ምስጋና ከማግኘት ይልቅ ሌላ ነገር ተለጥፎበት ይረገማል፣ ይሰደባል፣ ይወቀሳል፣ ይኮነናል። እንደዚህም ሆነው ለዚህች አገር ህልውና እንደ ኦሮሞ የሚንከራተት የለም ቢባል ነገር ማጋነን አይሆንም። በየጦር ሜዳው፣ በዱርና ገደል እንዲሁም በድንበር ላይ ለዚህች አገር ብለው የሞቱትን ቁጥር የለሽ የኦሮሞ ልጆች እንኳን ትተን አንዳንድ እጅግ የታወቁና በችሎታቸው የሚደነቁትን የኦሮሞ ልጆች እንደነ ዶ/ር ሀይሌ ፊዳን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ ይህቺን አገር ለመቀየር ብለው ሲንከራተቱ ቆይተው መጨረሻ ላይ መጥፎ አሟሟት እንደሞቱ ታሪክ የሚያሳየው ጉዳይ ነው። ግን ለምን?

ሊጣላ የሚመጣ ሰበብ አያጣም እንድሚባለው፣ ኦሮሞን ለማሰርና ለመግደል ሲፈለግ የሆነ ስያሜን በመስጠት በዚህ የተነሳ እንደ ቀንደኛ ጠላት እንዲታይ ይደረጋል። በደርግ ዘመን ሰርጎ ገብና ከሃዲ የሚል ሲያሜ እየሰጡ የኦሮሞን ልጆች ሕይወት ስያጠፉና ደም ሲያፈሱ ነበር። በወያኔ አገዛዝ ዘመን የኦነግ አባልና ደጋፊ ከሚለው ባሻገር ጠባብ ብሔርተኛ የሚለውን ሰያሜ እየሰጡ ኦሮሞን ሲገድሉ፣ ስያስሩና ከአገሩ እንዲሰደድ ስያደርጉ ነበር። ዛሬም ኦሮሞ አገሪቷን እያስተዳደር ነው በሚባልበት ጊዜ ኦሮሞን ለማጥቃት ሲፈለግ፣ ፅንፈኛ ወይም ገንጣይ የሚል ስያሜ ይሰጠዋል። መቸ ነው እንግዲህ ኦሮሞ ከኢላማ ውጭ የሚሆነው? የሀበሾችን ፍላጎትና ዓላማ ለማሳከት ብሰሩ እንኳን ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ አይታመኑም። ለምሳሌ የድሮውን ኦሕዴድ/ያሁኑን ኦዴፓ ብንውስድ፣ ይህ ድርጅት ለኢትዮጵያ አንድነት እንሰራለን ከሚሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ ስለዚህ ድርጅት ብዙ እንደሚባል የሚታወስ ነው። መለስ ዜናዊ ኦሕዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው ሲል ነበር። ዛሬ ደግሞ በኦነግ የተጠለፈና በድብቅ የኦነግን ዓላማ ለማሳካት የሚሰራ ድርጅት ነው እየተባለ ይወቀሳል።

እውነት እንናገር ከተባለ እጅግ የላቀ ችሎታ ያላቸው የኦሮሞ ልጆች የኦሮሞን ማንነት ለማታከብር ኢትዮጵያ ከመንከራተት ይልቅ ለኦሮሞ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጠው ቢሰሩ፣ ይሄኔ የኦሮሞ ጥያቄ መልስ አግኝቶ ነበር። እስቲ ሌላው ይቅርና የኦሮሞ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሲደርግ በነበረበት ወቅት የኦሮሞ ቄሮዎች አንግበው የተነሱትን የኦሮሞ ጥያቄዎችን አንዳንዱን ብናስታውስ፣ ከነዚህ ውስጥ አንዱ አፋን ኦሮሞ (Afaan Oromoo) የፌዴራል የስራ ቋንቋ ይሁን የሚል ነበር። ይህ በጣም ቀላሉና ቶሎ መልስ ማግኘት የሚችል ነበር። የሕዝቡ እንቅስቃሴ ወደ ፊት ያወጣቸው የኦሕዴድ አዲስ መሪዎች ይህ ጥያቄ እንዲመለስ ማድረግ ስችሉ ግን እስከ ዛሬም ይህ ስራ ላይ አለመዋሉ የሚያሳዝን ነው። ጥሩ አጋጠም ነበራቸው። ይሁን እንጂ ጌታችን ሕዝባችን ነው ሲባል የነበርው ንግግር ሁሉ ከንቱ ሆኖ ቀረ። ይህ ሊሆን ለምን ቻለ? የዚህ ጥያቄ መልስ አንድና አጭር ነው። እሱም ሀበሾችን ማስኮረፍና ማስቆጣት ስላልፈለጉ ነው። ሀበሾች ግን ይህን አይነት ዕድልና አጋጣሚ ብያገኙ ጉዳያቸውን ለማስፈፀም ውለውም ኣያድሩም ነበር።

የኦሮሞ ጥያቄዎች እኮ ከአገሪቷ ሕገ መንግስት ጋር የሚፃረሩ አይደሉም። ሀበሾች በተለይም የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች ይሀው ማንም ውክልና ሳይሰጣቸው “ባለ አደራ” ብለው ከሕገ መንግስቱ ጋር የማይሄደውን እየሰሩ አይደሉም እንዴ? እንሱ እኮ እንደ እኛዎቹ ሁኔታው ብመችላቸው ይሄኔ ያሰቡትን ብዙ ሰርተው ነበር። የኛዎቹ ግን ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው እያሉ፣ እውነትም በዚህ ሱስ ሰክረው፣ የውስጣቸውን የኦሮሚያን ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ለማይመስገኑት ለኢትዮጵያ አንድነት ሲንከራተቱ ይታያሉ። የኦሮሞን ተፈጥሮአዊ ማንነትን ከማያከብሩት ኃይሎች ጋር የጋራ አገር ለመመስረት ይጥራሉ። ቢሰደቡም፣ በረገሙም፣ ቢኮነኑም አይሰማቸውም። ይህ ጉድ ነው። ዛሬ ኦሮሚያ ውስጥ የኦሮሞ ደም እንደ ወንዝ ውሃ እየፈሰሰ፣ የዜጎች ሕይወት በየቀኑ እንደ ቅጠል እየረገፈ ሕዝባችን ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው እየተሰቃዩ በሚገኙበት ጊዜ፣ የራስን የቤት ስራ ከመስራት ይልቅ ለኢትዮጵያ አንድነት አልፎም ለአፍሪካ አንድነት መንከራተት ትርጉሙ ምንድነው? ጉዳዩ “የምለበስ የላት መከናነብ አማራት” እንደሚባለው ተረት ይመስላል። ኦሮሚያ እየታመሰች ስለ ኢትዮጵያ አልፎም ስለ አፍሪካ አንድነት ማውራት ትርጉም ይለውም።

ይህ ራዕይ መብታቸው ነውና እስቲ ይሁን። በፍቅር፣ በሰላምና በእኩልነት የሚኖርባት የጋራ አገርን መግንባት የሚጠላም የለም። ነገር ግን መነሳት ያለበት ጥያቄ እንዴትና ከማን ጋር የሚለው ነው። ሌላው ቀርቶ ማንነትን እንኳን ከማያከብሩት ኃይሎች ጋር አንዴት የጋራ አገር ይመሰረታል? አንድ ሕዝብ እየተናቀ፣ እየተሰደበ፣ እየተዋረደ፣ የገዛ መሬቱ ያንተ እይደለም እየተባለ እንዴት የጋራ አገር ተመስርታ በሰላም አብሮ መኖር ይቻላል? ለኦሮሞ መብት እታገላለሁ የሚትለው ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ወይም ድርጅት ያለንበትን ሁኔታ አስተውል። ለዚህ ለሰላም ፈላጊ የኦሮሞ ሕዝብ የምትቆረቆርና ለመብቱ እታገላለሁ የምትል ሁሉ ለኦሮሞ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተህ የማትሰረ ከሆነና ይህ ወርቃማ አጋጣሚ ካመለጠህ አንተም ከጉዳቱ አታመልጥም። ከታሪክ ተጠያቂነትም አትድንም።

1 Comment

  1. These anti-Oromo lunatic fringes are insignificant in the process of building a new Ethiopia which will acknowledge all her peoples, and recognize the greatness of the Oromo people. We must reclaim our country from pseudo Ethiopians (hatemongers anti-Oromo lunatic fringes). In fact, because we have been too modest in claiming Ethiopia, our country, whose survival has depended on our existence (the Oromo being the corner stone of everything Ethiopia has rested on), emboldened ungrateful parasites such as the so called Ermias Legesse to insult the great people, who shared their daily bread with them. If I have to go down to his level and point out clearly who this anti-Oromo individual might be, he claimed (in an interview he gave when he accomplished his assignment of spying on the Oromo at home for the TPLF and posted overseas to continue his low level gossips) that he was born to a Gurage family who lived near Finfinne and spoke Affaan Oromo. Mind you, hyenas live in the jungles side by side with Lions and survive on leftovers from the kill of the lion. Hynas being hynas, they dare to attack the lion when they get opportunities. This Ermias Legesse, with a body of fatten pig and hyna’s face fills the televission screen with his ever expanding belly, and spits hatred against the Oromo people ( in Amharic language). The anti-Oromo lunatic fringes who insult the great Oromo people in Amharic language are trying to hide behind the Amhara while they are harming both communities. It is up to the Amhara intelligentsia to take on these anti-Oromo individuals and media outlets and educate their people what is in the best interest of future Ethiopia. The Gurage people whom this anti-Oromo individual, Ermias Legesse, claims to belong to also have responsibility to show wisdom and stand up to his destructive propagandas. This individual is posing danger to their future relationship with the Oromo people who have kept them under their wings for ages and helped their businesses to thrive.

    Equally, the Amhara people must stand up to extremist gangsters and ultra nationalists who are poised to endanger their coexistence with their Oromo neighbours and other Ethiopians. Irresponsible propagandas and hateful speeches intended to incite violence must be countered by genuine and peace loving Amharas before it gets out of hands. Amhara intelligentsia, beware; you have added responsibility to stand up to anti-Oromo lunatic fringes, and guard the coexistence of these two people, the great Oromo people and the great Amhara people. Irresponsible Amhara activists with 19th century mindset and deceptive politics as well as anti-Oromo non-Amhara individuals who hide their ethnic backgrounds in order to inflict harms to both communities must not be tolerated by all Ethiopians. Hatred propagandas will not hold in future Ethiopia, where we all live together and thrive.

    Above all, qeerroo and qaree you understand more than I do that your country and your future is in your hands. You have matured in your political outlooks, unwavering unity and focused on the big picture, greater freedom. Those who seek your friendship and protection are fully protected and will enjoy the greater freedom you will bring to your people. Nevertheless, small enemies (lunatic fringes) barking hatred will have no place in Oromia in particular and new Ethiopia in general. They will not have chance to endanger the coexistence of the Ethiopian peoples anymore. This is a new era; something great is happening to Oromia and Ethiopia by the special people of that country, you: qeerroo, qaree, ejeto, and other enlighten Ethiopian youth. You have no time for crying hyenas, anti-Oromo lunatic fringes. Listen to each other; read each other; protect your people and the peaceful others who live among you. No force will stop you from achieving the inalienable greater freedom to the great Oromo people and all Ethiopians alike!

    May truth and justice prevail in the country of Ethiopia!

    OA

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.