የሕዝቦችን ጥያቄ በጠመንጃ ለማፈን መሞከር የዚህቺን እምፓየር ዕድሜ ያራዝም ይሆናል እንጂ ዘላቂ ሰላም አያመጣም

የሕዝቦችን ጥያቄ በጠመንጃ ለማፈን መሞከር የዚህቺን እምፓየር ዕድሜ ያራዝም ይሆናል እንጂ ዘላቂ ሰላም አያመጣም

ብርሃኑ ሁንዴ, Adoolessa 21, 2019

የሆነ ሆኖ፣ ህገመንግሥታዊ ጥያቄ ብሎ ቀንና ሌሊት በሠላማዊ መንገድ የጠየቀ፣ በሌላ በኩል መንግሥትንና ሥርዓቱን ደግፎ የተንቀሳቀሰ ህዝብ በጦር ሲዘመትበት መብቱን ወደጎን ትቶ ትግሉን ጥሎ ዝም ይላል ወይ? በሲዳማ ላይ የተጠመዱ በርካታ ችግሮች ህዝቡን እንደህዝብ የበለጠ እያጠከናሩት ጥያቄውን እንዲያሳካ ይረዱታል እንጂ ለደቂቃም አያሰናክሉትም። ሞት ለገዳዮች። ኤጄቶዎች ይፈቱ።

ታሪክ ይደገማል እንደሚባለው፣ የአብይ አህመድ አስተዳደርም ከሱ በፊት ከነበሩት አስተዳደሮችና ግዛቶች የተማረ አይመስልም። ምናልባትም የእምፓየሯ ባሕርይ በመሆኑ፣ ይህቺ እምፓየር አስካለች ድረስ ምንም ዓይነት ስርዓት ቢሞከር መረጋጋትና የመጨረሻ ሰላም መምጣት አይችልም ይሆናል። የአገሪቷ ሕገ መንግስትም በሚፈቅደው መሰረት አግባብ ያለውና ተፈጥሯዊ የሆነ የመብት ጥያቄ መጠየቅ ስህተቱ ምን ሆኖ ነው ይህን ለማፈን ሲባል በሚደረገው የኃይል እርምጃ የሰው ሕይወት የሚጠፋው? በመቶዎችና ሺዎች የሚቆጠር የዜጎች ሕይወት እየጠፋና ሌሎች በገፍ እየታሰሩ የመደመር ፍልስፍና ትርጉሙ ምንድነው? መደመር ማለት መጨፍለቅ ይሆን እንዴ? ወይንስ አሁን ካለው ከፌዴራላዊ ስርዓት ወደ ድሮው አሃዳዊ ስርዓት ለመመልስ ተብሎ የሚደርገገው አካሄድ ነው ከመደመር ፍልስፍና በስተጀርባ ያለው?

ይህንን ጉዳይ እንዳቀርብ ያደረገኝ የሲዳማ ሕዝብ የራሱን ክልል ለመመስረት ስያቀርብ የነበረውና ያለው ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ ፍፁም ሕገ መንግስታዊ ከመሆኑም ባሻገር እጅግ በትዕግስት የሞላ የመብት ጥያቄ ነው። መንግስት ይህንን ጥያቄ በአገሪቷ ሕግና ደንብ በጊዜ መመልስ ሲችል፣ አንደኛ  ከዓመት በላይ እንዲጓተት አድርጎ የሕዝብ ትዕግስት እንዲያልቅ ባማድረጉ፤ ሁለተኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝቦች ም/ቤት በሰጠው መግለጫ ውስጥ የዛቻ ንግግሮችን መጠቀሙ ነገሮች ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄዱ በማድረጉ ዛሬ ለምናየው የዜጎች እልቂት መንስዔ ሆኗል ማለት ነው። ስለዚህ ለዚህ ለተፈጠረው አስከፊ ድርጊት ተጠያቂው መንግስት ራሱ ነው ማለት ነው። ይህ የዛቻና በኃይል የመጠቀሙ ጉዳይ አንድ ነገር እንዳስታውስ አደረገኝ። ይኸውም መንግስቱ ኃ/ማሪያም አንድ ወቅት ስል የነበረ ነው። የሱማሌን ጦርነት ሲያሸንፍ እንዲህ ብሎ ነበር። “በምስራቅ የተገኘው ድል በሰሜን ይደገማል!” ይህ ማለቱ የኤርትራ ገንጣይ ወንበዴዎች ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቃቸዋል ማለቱ ይመስለኛል። ወንበዴ ወይም ከሃዲ ወይም ሰርጎ ገብ የሚሉት ቃለቶች ወይም ሀረጎች መንግስቱ ስጠቀምባቸው የነበሩት ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይም በሕዝቦች ም/ቤት የተናገርውም የዛቻ ንግግር ተመሳሳይነት አለው። እኛ በምንፈልገው መንገድ መልስ እስከምታገኙ ድረስ በትዕግስት ከልጠበቃችሁና ሌላ መንገድ የምትሞክሩ ከሆነ በሱማሌ የታየው በደቡብም ይታያል ማለቱ ከመንግስቱ አንጋገር ጋር ይመሳሰላል። ለዚህም ነው እንግዲህ ታሪክ ይደገማል ያልኩት። ይሁን እንጂ ካለፈው መማር ካልተቻለ ወደ ባሰ ችግር መግባት የማይቀር ይሆናል። ችግር ሌላ ችግር ይወልዳል እንጂ መፍትሄ አያመጣም። ኤርትራ እንዳትገነጠል ሌላ መፍትሄ ማግኘት ሲቻል፣ በኃይልና ጦርነት መጠቀሙ ኤርትራ ነፃነቷን እንድትጎናፀፍ አስቻላት እንጂ አላቆመም። አሁንም በእምፓየሯ አንድነት ስም የሕዝቦችን ጠፈጥሯዊ መብት መከልከልና ጥያቄአቸውን በጉልበት ለማፈን መሞከር አገሪቷ እንድትበታተን ያደርጋታል እንጂ ዘላቂ ሰላምና መራጋጋትን አያመጣም።

እኔ እንደሚመስለኝ የዶ/ር አብይ አካሄድ ምኞቱንና ፍላጎቱን (ምኞቱና ፍለጎቱ የእውነት ከሆኑ) የሚቃረን ነው። ለምን ቢባል፣ እንደ ለውጡ መሪና እንደ አንድ ፌዴራሊስት (ምን ያህል እውነተኛ ፌዴራሊስት እንደሆነ ማስረጃ ባይኖረኝም) በሀገሪቷ ሕገ መንግስት መሰረት የሕዝብን ጥያቄ ተገቢ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ሲገባው፤ አገሪቷን ወደ ተሻለ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ከማሻገር ይልቅ፣ ፀረ ፌዴራሊዝም የሆኑትንና አሃዳዊውን ስርዓት መልስው በሕዝቦች ላይ መጫን የሚፈልጉትን ኃይሎች በማቅረብ፣ ከዚህም አልፎ ከነዚህ ኃይሎች ውስጥ የተወሰኑትን በአማካሪነት ካሱ ጋር እንዲሰሩ ማድረጉ ጭራሽ አብረው የማይሄዱ ናቸው። በነገራችን ላይ የሕዝብን ጥያቄ በኃይል መፈን ነው ሰላም፣ ፍቅርና እርቅ የሚባለው? ይህ ነው የመደመር ፍልስፍና? ወይንስ የመደመር ፍልስፍና ትርጉሙ አሃዳዊ ስርዓት መሆኑ ይሆን? እንደዚህ ከሆነ ለዚህም ነዋ የድሮ ንጉሶችን ማድነቅ አስፈላጊ የሆነው??!! ለኦሮሞ ሕዝብ እውነተኛ ለውጥ ባያመጣም የኦሮሞ መንግስት ነው የሚባልለት ይህ መንግስት እንደ በፊቶቹ መንግስታት ኃይልን ተጠቅሞ ሕዝብን የሚጎዳ ከሆነ፣ የኦሮሞ ሕዝብም በዚህ መወቀሱ የማይቀር ይሆናልና ይህንን ድርጊት ባይፈፅም ጥሩ ይመስለኛል።

3 Comments

 1. The trouble is, the omni-shambolic Ethiopian Empire has never been short of dumb and shortsighted mediocre leaders, whose colourfull accomplishments have been spilling the blood of Ethiopians. Start with the present and count back to arrive at the number of lunatic butchers that the subjugated peoples in that country have had to shoulder since they fell into the hands of Abyssinian savages. Think the number of innocent citzens who had been massacred by government security forces, year in year out. The entire events attest to the fact that the Ethiopian polity cannot function without drinking the blood of innocent Ethiopians. When is the catastrophic political culture going to end? Will there be any civilized way of running government affairs in that country at all?

  What is more, it is crystal clear that there has never been a thing called “Oromo Government” since Oromia was overrun by Abyssinian invaders. The party which is running the country at the present is EPRDF, and the government is EPRDF government which is a coalition of four ethnic based parties. Tha fact that politically naive OPDO cadres are seen at the forefront does not make the Ethiopian government “Oromo Government”. It is, thus forth, not only wrong to label the current adminstration as “Oromo Government”, but also gravely misleading.

  RIP the Sidama martyrs! You have not sacrificed for nothing. Your blood in conjunction with the blood of other Ethiopians martyred for demanding justice, in Oromia and elsewhere, will free all the subjugated peoples who have been herded together in order to keep the cursed empire alive. Never be frightened by the massacre carried out by the irresponsible dictators; coordinate your struggle for justice with your Oromo brothers and sisters, and carry on so as to ascertain your greater freedom. Your martyrs’ blood must fuel your determination to achieve your freedom, and seek justice for your brothers and sisters who were gunned down cruelly.

  Justice to all the subjugated peoples in Empire Ethiopia; down with the lunatic Ethiopian dictator butchers!

  OA

 2. Oromo and Amara brought the great change adding others to join the great change, joining PM Abiy’s superb leadership team WHILE THE WHOLE WORLD witnessed the incredible results within just a little over a year’s time.

  Just to name few of the achievements we seen within
  the last year:
  1.All of Querro are added.
  2.All of Fano are added.
  3.Ethnic Gedeo are added.
  4.All of Hawassa residents are added.
  5.Ethnic Sidama are added.
  6.Addis Ababa residents are added.
  7.Tigray residents except TPLF are added.
  8.Diaspora except TPLF are added.
  9.Somali region Ogaden residents are all added.
  10.All of Afar are added.
  11.Gambella residents are all added.
  12.Benishangul Gumuz/Shinasha are all added.
  13.Eritreans are trying their best to be permitted to get added.
  14.Egypt is submitting to all of Ethiopia’s demands in regards to the Nile river.
  15.For the first time in decades Al-Shabab is scared shit less of Ethiopian military.
  16.Kenya is following Ethiopia’s order, to produce only green renewable energy.
  17.Both South Sudan and Sudan are one step away from making ethnic federalism constitutional declaration system, with both countries following PM Abiy’s instructions to follow ethnic federalism.
  18.In Ethiopia for the first time ever, Price of goods and services are finally seeing a decline after decades/centuries of continuous rises.
  19.In Ethiopia crime rate is at it’s lowest in decades.
  Ethiopia’s economy is booming.
  20.Foreign investors are pouring foreign currency into Ethiopia.
  21.Health Care system of Ethiopia is being rated one of the top 3 health care systems in Africa.
  AND MANY MANY MORE ACHIEVEMENTS WITH THE LIST BEING ENDLESS…

  All these in just a little over a year, that is the power of being added (MEDEMER) for sure.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.