የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ

የሲዳማ ሕዝብ ለዘመናት ሲጠይቀው የነበረ የራስ አስተዳደር የክልል ጥያቄ የሕዝብ ውሳኔ የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል። በሂደቱ አዎንታዊ ሚና የነበራቸውን ሁሉንም አካላት የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር ማመስገኑም ይታወሳል። ሆኖም የሕዝቡን ውሳኔ ተከትሎ መሰራት ያለባቸው የሽግግር ስራዎች በመንግስት ባለመከናወናቸው ህዝቡ ውስጥ እያደር ሌላ ጥርጣሬ ፈጥሯል።  በሀገራችን ሕዝቦች እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በፍጹም ሠላማዊነቱ እና ሁሉን አካታች በሆነ መልኩ መከናወኑ የተመሰከረለት ህዝበ ውሳኔ ቢደረግም ሽግግሩን አስመልክቶ መቼ እና እንዴት ይከናወናል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ግልጽ መግለጫ ለሕዝቡ አለመሰጠቱ አግባብነት የሌለው መሆኑን ማህበራችን ያምናል። ከዚህም ባሻገር በሲዳማ ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍ እና በደል አሁንም መቀጠሉን የሚያመላክቱ በርካታ ማስረጃዎች በማህበሩ እጅ እንደገቡ፣ በእነዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ እና አባላት በ 12/ 29/2019 ዓ. ም ባካሄዱት አስቸኳይ የምክክር ስብሰባ የሚከተለውን ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

1ኛ. የሲዳማ ሕዝብ እጅግ ውድ መስዋዕትነት ከፍሎ ያገኘውን ድል በልመና እንዲፈጸም ለማድረግ የሚደረግ አሻጥር በፍጥነት እንድቆም እና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ለአዲሱ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈላጊውን የርክክብ ስነ ስርዓት የሚፈጽምበትን የጊዜ ገደብ እንዲያስቀምጥ እንጠይቃለን፤  አተገባበሩም ቶሎ እንዲገባደድ እናሳስባለን።

2ኛ. ሕዝባችን ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ክልላዊ አስተዳደር እንዲመሰረት በመጠየቃቸው እና ሕዝቡን በማስተባበራቸው ብቻ በህገወጥ መንግስታዊ ድርጊት ያለወንጀላቸው ለወራት በእስር ላይ የሚንገላቱ የሚዲያ ሰወች፣ ምሁራኖች፣ የኤጄቶ እንቅስቃሴ አባላትና የሲዳማ ተወላጂ ዜጎች በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አጥብቀን እንጠይቃለን።

3ኛ. የሲዳማ ህዝብ የጠየቀውና ያገኘው መብት ህገ መንግስታዊ ነው። በሂደቱ ድጋፍ ያደረጉ እና ጥያቄው እንዲመለስ በሀሳብ ሙግት እንዲሁም ሕዝቡን በማስተባበር ፊት ለፊት የወጡ የመንግስት የስራ ሀላፈዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘው በደል  ዛሬም ድረስ መቀጠሉ የፌዴራሉ መንግስ ላይ ሕዝባችን እምነት እንዳይኖረው አድርጓል፤ እያደረገም ይገኛል። ከጥያቄው ጋር በተያያዘ ከሕዝቡ ጎን በመሰለፋቸው የዞን አስተዳዳሪዎች፣ የከተማ ከንቲቦች፣ የፌዴራል ስራ አስፈጻሚዎች እና የክልል ፕረዚዴንት ሳይቀር ሕዝባቸውን እና የኢትዮጵያን ሕዝብ በልምድ እና በፖለቲካ አቅማቸው ለማገልገል በተሰማሩበት ስፍራ እንዳይሰሩ ሲደረግ ቆይቷል፤  አሁንም እየተደረገ ይገኛል። ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ስልጣን የመስጠት እና የመንፈግ ሀይል በእጁ ቢሆንም አመራሩ ከህዝቡ ጎን በመሰለፉ ምክንያት የሚወሰደው እርሚጃ ፍጹም የተሳሳተ እና ጸረ-ህዝባዊ መሆኑን ማህበሩ ያምናል። በመሆኑም በደም ሲዳማ በመሆናቸ እና ከህዝባዊ ፍላጎት ጋር በመደመራቸው ምክንያት በሀላፍነታቸው ከተቀመጡ በወራት ውስጥ ሰበብ እየተፈለገ ከየቦታው ተለቃቅመው ከስራ ገበታቸው እንዲነሱ የሚደረገው መንግስታዊ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።

4ኛ. የሲዳማ አመራሮች ወደ ህዝቡ ይዛችሁ የምትወርዷቸውን የፖለቲካ አጀንዳወች ገታ አድርጋችሁ ህዝቡ በትግሉ ያገኘውን ክልል ባፋጣኝ በማደራጀት ክልላዊ ተቋማት እና አቅም ለመፍጠር ቅድምያ እንድትሰጡ ማህበራችን ይጠይቃል። ሕዝቡ የሚመራውን የፖለቲካ ድርጅት የሚመርጠው በምርጫ ወቅት መሆኑን አውቃችሁ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው ለሚገባቸው  የሽግግር ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲታደርጉ አጥብቀን እናሳስባለን።

5ኛ. የሲዳማ ሕዝብ ያገኘውን ክልላዊ አስተዳደር አጠናክሮ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር የሚያስችለውን ሕብረብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ለመደገፍ እና  ጥብቅና ለመቆም ሕዝባችን እጅ ለእጅ ተያይዞ የሚያደርገውን ጥረት ማህበራችን መደገፉን እንደሚቀጥል ልናረጋግጥ እንወዳለን።

6ኛ. ከህዝብ ጋር እልህ በመጋባት የሚፈታ ችግር እንደማይኖር እናምናለን። ዛቻ እና አሸማቃቂ የሚመስሉ እርሚጃወች ስለተወሰዱም የሚንበረከክ ህዝብ አይኖርም። የትኛውንም ህዝብ ያገለለ የፖለቲካ ስርዓት እድሜው አጭር እንጅ ረጅም እንደማይሆን ታሪክ ምስክር ነው። በመሆኑም ብሄርን መሰረት ያደረገ የግለሰቦች ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን።

ጥር 02 2020 ዓ. ም

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር

1 Comment

  1. To Sidama:
    -Wait for your turn .
    For all we know so far, at the elections in allover the country Sidama might be the only one voted for with all others across the whole country getting boycotted not getting a single vote at the next national elections , if this happens every body in federal government and in all regional gvernments have to relinquishh all government to Sidama .

    Then Sidama will have to administer the whole not only Sidama so for now we advise you to wait for your turn in the meantime spend the time wisely by getting prepared for the scenario I just told you now in the next half a year just in case it happens, so you can confidently be able to do the work transitioning into such a huge responsibility .

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.