የሸገር ልጅ (ነዋሪ) ሆይ: አሁንም አትሸወድ! ባይሆን እያየህ (እያወክ) ግባበት! 

የሸገር ልጅ (ነዋሪ) ሆይ: አሁንም አትሸወድ! ባይሆን እያየህ (እያወክ) ግባበት! 

የሸገር ልጅ/ነዋሪ ሆይ: አሁንም አትሸወድ! ባይሆን እያየህ/እያወክ ግባበት! 
———————————-
በ ግርማ ጉተማ ( Abbaacabsaa)

“የባልደራስ ባላደራ ምክር ቤት” በሚል ራሱን የሾመው የነስክንድር ነጋ ቡድን እንደሚለው ሸገር የኦሮሞ ሃገር አይደለም ወይም የኦሮሚያ አካል አይደለም። ስለዚህ “ከኦሮሚያ ተነጥሎ በራሱ መቆም አለበት” የሚለው የትግሉ አላማ ሊሳካ የሚችለው ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ብቻ ነው፥

1) ደርግ በ66ቱ ሃዝባዊ አብዮት የነፍጠኛውን ስርዓት አስወግዶ የተዛባው የህዝቦች ታሪክ በተወሰነ ደራጃም ቢሆን እንዲስተካከል እድል ከመፍጠሩ በፊት የነበረውና ቀደም ብሎ ባጼዎቹ ዘመን በደብተራዎች የፈጠራ ትርክት ላይ ተመስርቶ፣ “…ኦሮሞ ነባር ህዝብ ሳይሆን ኢትዮጵያን ከጥቂት መቶ አመታት በፊት በወረራ የያዘ፣ ልክ እንደ ደራሽ ጎርፍ ኢትዮጵያን በማጥለቅለቅ ስልጣኔዋንም ያጠፋ ህዝብ ስለሆነ ሸገርን ጨምሮ የዛሬዋ ኦሮሚያ የኦሮሞ ሃገር አይደለም” የሚለው ያጼዎቹ ዘመን ድርሰት ዛሬ ላይ ዳግም ነፍስ ዘርቶ ተቀባይነት ማግኘት የሚችል ከሆነና፣ ይሄንኑም “የባልደራሱ ባላደራ ምክር ቤት” በጉልበትም ሆነ በሌላ በማንኛውም መንገድ በተለይም የኦሮሞ ህዝብ ላይ ለመጫን በቂ ሃይል ያለው እንደሆነ፤

2) ከላይ በቁጥር 1 ስር በተጠቀሰው ሁናቴ፣ ዛሬ ላይ ፊንፊኔ የቱለማ ኦሮሞ መሬት አለማሆኗንና አሁን ላይ ኦሮሞ የሃገሩ ባለቤትነት ጥያቄ ማንሳት እንዳይችል፣ ካነሳም በጉልበትም ሆነ በሌላ መንገድ መከልከል የሚያስችል ሁኔታና አቅም መፍጠር የተቻለ እንደሆነ፤ በዚሁ ምክኒያት የኦሮሞ ህዝብ ልክ እንደ ሬድ ኢንዲያንስ ባሜሪካና እንዳቦሪጂንስ ባውስትሬሊያ ተሸንፎንና የራሱን ሃገር ባለቤትነት መብት ማስከበር ከማይችልበት ደረጃ ደርሶ፣ ዱቄት ሆኖ ተሰብሮ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ማድረግ የሚቻል እንደሆነ፤

አለበለዚያ ደግሞ፥

3) የኦሮሞ ህዝብ ሸገር ላይ የሃገር ባለቤትነት ጉዳይ አንዳች ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ፣ ኦሮሞ ለራሴም ሆነ ለሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ይጠቅማል ብሎ አምኖ በኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች አስተባባሪነት በሚደረግ ህዝበ ውሳኔ መሰረት፣ ሸገር የቆመችበት የቱለማ ኦሮሞዎች መሬት የፌዴራል መንግስቱ በስጦታ መልክ እንዲወስደውና የራሱ ግዛት እንዲያደርገው፣ ወይም ደግሞ ሸገር የከተማ መንግስት (City State) ሆና ተዋቅራ የፌዴሬሽኑ አዲስ አባል መንግስት መሆን ትችል ዘንድ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ ድምጽ የሚወስን ከሆነ ነው።

——

በቁጥር 1 እና 2 ስር የተጠቀሱትና “የባልደራሱ ምክር ቤት” የሚሄድበት ያለው መንገድ ከሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎችና ከወጡበት አርባ ሚሊዮን ህዝብ ጋር ግጭት ፈጥሮ ከግጭቱም ባሸናፊነት መውጣትንና አላማን ማሳካትን የምጠይቅ ከባድ (ግን ደግሞ ኢፍትሃዊ የሆነ) ትግል ነው።

ስለሆነም፣ የሸገር ልጅ/ነዋሪ ሆይ:

“የባልደራሱን ባላደራ ምክር ቤት” በተመለከተ አትሸወድ—ባይሆን እያወክ ግባበት!! ጉዳዩ የሸገር ነዋሪዎችን መብት ወይም ጥቅም ስለማስጠበቅ አይደለም ምክኒያቱ የከተማው አስተዳደር ለኦሮሚያ ስቴት ተጠያቂ መሆኑ የነዋሪውን መብቶችና ጥቅሞች ይበልጥ ያሰፋ እንደሆነ እንጂ ሊያጠብ አይችልም። ይልቅ “የባልደራሱ ምክር ቤት” ጉዳይ የኦሮሞን ያገር ባለቤትነት ከመቃወም እንጂ ለሸገር ነዋሪዎች መብት ወይም ጥቅም ከመቆም ጋር ከቶ አይያያዝምና ቆም ብለህ አስብ የሸገር ልጅ/ነዋሪ ከሆንክ።

የምትገባበት ከሆነም እያየህ/እያወክ ግባበት

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.