የብልጽግና ኅልዉና ከ”ማሸነፍ” ጋር የተሳሰረ ነዉ፡፡

የብልጽግና ኅልዉና ከማሸነፍጋር የተሳሰረ ነዉ፡፡

ፍዳ ቱምሳ, Guraandhala 21, 2020

History repeats itself. The two leaders parties (Abiy’s Prosperity Party of Ethiopia, 2019 and Mengistu’s Worker’s Party of Ethiopia, 1984)  were formed at the Minilik Palace.

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ መንግስት ያቋቋመዉ ፓርቲ ተመስርቶአል፡፡ የመጀመሪያዉንም ያሁኑንም የመሠረቱት ኮሎኔሎች ናቸዉ፡፡ ፈርዶብን !! ሁለቱም ፓርቲዎች የተመሠረቱት በአራት ኪሎ ቤተመንግሥት ዉስጥ ነበር። የመጀመሪያው፤ ኢሰፓ፣ ከሱ ቀድመዉ የነበሩ ፓርቲዎችን/ድርጅቶችን አፍርሶ፣ዉስጥ ከነበሩና፤ ከሽብር የተረፉ፤ አድርባይ የሆኑ ወገኖችን በመያዝ ፣ የፓርቲዉ አባል ካልሆኑ ለህልዉናቸዉ የሚያሰጋቸዉን በቢሮኪራሲዉ ዉስጥ የነበሩ ግለሰቦችን በዉዴታ ግዴታ በመሰብሰብ በኮሎኔል መንግሥቱ ሀይለማርያም ማዕከልነት የተመሰረተ ድርጅት ነበር፡፡

ይህ ድርጅት፤ኢሰፓ፤ ህልዉናዉ ከመንግስትና ከመንግስቱ ሀይለማርያም ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ፓርቲዉ የመንግስት ስልጣንና መንግሥቱ ሀይለማርያም ከሌለ፣ የሚያያይዘዉ ምንም ዓይነት ሙጫ አልነበረም፡፡ እናም መንግሥቱ ሀይለማርያም ሀገር ለቆ ሲሄድና የመንግሥት ስልጣን የታጣ ቀን በነጋታዉ ድርጅቱ ተነነ፡፡ በሀሳብና በአላማ ላይ የተሰባሰበ አባላት የነበረው ድርጅት አልነበረም። አባላቱ፣ በአብዛኛው ሥልጣንና ሥልጣን የሚያስገኘዉን ጥቅም ብቻ ያሰባሰባቸዉ ወገኖች ነበሩ፡፡ እንደ ዛሬው ሳይሆን ያኔ ለፖለቲካ ሰዎች ሥልጣን የሚያስገኘዉ ጥቅም ቢኖር ራስን ማትረፍ ብቻ ነበር። ዛሬ የዚያ ድርጅት አባላት እንኳንስ እንደ ጓድነት ሊተያዩ ይቅርና፣ ሰላምታም የሚለዋወጡት ጥቂቶች ናቸዉ፡፡

ዛሬ በታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይ የተመሰረተዉ ብልጽግናም ከኢሰፓ አመሰራረት ብዙም አይለይም፡፡ እንደ ኢሰፓ ሁሉ፣ ሌሎቹን ድርጅቶች አክስሞ በታጋይ ኮሎኔል ዶር አብይ ማዕከልነት የተመሰረተ ድርጅት ነዉ፡፡ ከኢሰፓ የሚለየዉ፣ የኢሰፓ አባላት የተሰባሰቡት ራስን ለማዳን የነበረ ሲሆን፤ የብልጽግና አባላት ግን የተሰባሰቡት የዘረፉትን ለማስጠበቅና ተጨማሪ ዘረፋ ለማከናወን፣ የሰሩትን ወንጀል ለመቅበርና፣ ከተቻለ ንጹህ ነን በማለት እጅን ለመታጠብ፣ አልያም ትናንት በታዛዥነት የፈፀሙትን ወንጀል ዛሬ በአዛዥነት ለማስፈፀም ነዉ፡፡

ወደ ተነሳንበት ርዕስ እንመለስና፣ ብልጽግና ያለ ሥልጣን ህልዉናዉ ሊኖር ይችላልን? ለሚለዉ ጥያቄ መልስ እናፋልግ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የተመሰረተዉ በመንግሥት ነዉ፡፡ የፓርቲዉ አባላት አባል የሆኑት በአብዛኛዉ ፓርቲዉ መንግሥት በመሆኑ እንጂ የያዘዉ አላማ ላይ እምነትና ጽናት ኖሮአቸዉ አይደለም። ለዚህ ማረጋገጫዉ በሰዓታት በሚቆጠሩ ጊዜያት፣ የጥቂቶች መሳሪያ ከሆነው አብዮታዊ ዴሞክራሲ፥ ምንነቱ ወደማይታወቅ “መደመር” መሸጋገር ብቻም ሳይሆን የማያዉቁትን ያልገባቸውን “መደመር” በሰባኪነት መሰለፋቸዉ ነዉ።

ባለፉት 29 ዓመታት ኢህአደግ(ፓርቲ)ና መንግሥት አንድ የሆነበት አስተዳደር ተመስርቷል። በፓርቲና በመንግሥት መሀከል ልዩነት እስከ ዛሬም የለም። የትኛዉ የፓርቲ ሥራ፣ የትኛዉ የመንግሥት ሥራ፣ እንደሆነ ከቶዉንም መለየት አይቻልም። የትኛዉ የመንግሥት ሠራተኛ፣ የትኛዉ የፓርቲ ተሿሚ መሆኑ ያልተለየበት ስርዓት ተገንብቷል።

ባለፉት ዓመታት የተደረጉት የህዝቦች ትግል አንዱ መስክ ይሄንን ፓርቲና መንግሥትን መለየት የማይቻልበትን ስርዓት ለመቀየር ነበር። ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር የመጀመሪያዉ እርምጃ መንግሥትንና ፣ የመንግሥት ሰልጣን የያዘዉን ፓርቲ የሀላፊነት ወሰኖችን መመስረትና ለዴሞክራሲ ግንባታ የሚያገለግሉትን ተቋማት መገንባት ነዉ። ዴሞክራሲያዊ ስርአት የትኞቹ የመንግሥት የሀላፊነት እርከኖች የአሸናፊ ፓርቲ/ ፓርቲዎች ተሿሚ እንደሆኑና የትኞቹ ደግሞ የመደበኛዉ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ዘርፎች እንደሆኑ መወሰንን ይጠይቃል።

ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚደረገው ሽግግር ከተሳካ አብዛኛዉን ዛሬ በፓርቲ አባልነት ብቻ የመንግሥት የሥራ ዕርከን ላይ የተቀመጠዉን አካል፣ ለሥራዉ ብቁ ሆኖ ከተገኘ ከፓርቲዉ ጥገኝነት ያላቅቀዋል፣ አልያም ለሥራዉ ብቁ ሆኖ ካልተገኘ ከስራ ያሰናብተዋል። የመንግሥትንና ፣ የፓርቲን ሰልጣንና ሀላፊነት ወሰኖችን ማበጀት በፈደራልም ሆነ በክልሎች ደረጃ ለዉጡ መሠረት እንዲይዝ ከተፈለገ መከናወን ያለበት ጉዳይ ነዉ።

እዚህ ላይ ነዉ እንግድህ ፣

1ኛ) ብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ሳይሆን ህልሁና ሊኖረዉ ይችላልን?
2ኛ) ብልጽግና ፓርቲ ተመርጦ መንግሥት ቢሆንስ መንግሥትንና ፓርቲን መለያየት ይችላልን?? በፊንፊኔ ቋንቋ ይመቸዋልን?
3ኛ) ብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ሳይሆን፣ በተቃዋሚነት (በተፎካካሪነት) ህልዉናዉን አስጠብቆ መቆየት ይችላልን? የሚሉ ጥያቄዎች ማንሳት ያለብን።

ለነዚህ ጥያቄዎች የምንሰጠዉ መልስ፣ የሚቀጥለዉ ምርጫ ፍትሀዊ፣ ነጻና ተገዳዳሪ መሆን ይቻለዋልን? ለሚለዉ ጥያቄ መልስ መስጠት ያስችለናል።

በኛ አስተሳሰብ ታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይ ምርጫዉን የ“ማሸነፍ” ጉዳይ ያቋቋሙት ፓርቲ ህልዉና ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ተገንዝበዉታል። ኮሎኔሉ ፓርቲአቸዉ/ብልጽግና ከ”ገዥ” ፓርቲነት ወደ ተፎካካሪ ፓርቲነት ተቀይሮ፤ በማንኛዉም ይህ የተፎካካሪነት እድል በገጠመዉ ክልል ህልዉና ሊኖረው እንደማይችል ይረዳሉ፣ ተረድተዋልም። በመሰረቱ በመንግሥት የተመሰረተ ፓርቲ ህልዉናዉ የሚቆየዉ የመንግሥት ስልጣንን እስከ ተቆጣጠረ ብቻ ነዉ። ብልጽግናም ሆነ ወራሾቹ ነኝ የሚላቸው የወያኔ ውልዶች የሆኑ ድርጅቶች አባላቱ የተሰባሰቡት ፓርቲዉ መንግሥት በመሆኑ እንጂ፥ ፓርቲዉ መንግሥት ለመያዝ ባደረገዉ የትግል ጉዞ አልነበረም ፤ አይደለምም።

እናም፣ ብልጽግና የመንግሥት ስልጣንን (የክልሎች ሆነ የፈዴራል) መቆጣጠር ባቆመ ማግስት፥ አባላቶቹ እንደ ለመዱት መንግሥት የሆነ ፓርቲ ፍለጋ የሚንከራተቱ ይሆናሉ። ይሄንን ለማሳየት ባለፈው የሀገራችን ጉዞ ያየነውና ከሌሎችም ሀገራት ተሞክሮ ብዙ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

እነኝህ ከላይ ያነሳናቸዉን ነጥቦች ለተመለከተ ሰዉ፣ የሚቀጥሉት ሰባት ወራት (ምርጫው ካለ) ብልጽግና ለህልውናው መቀጠል፣ ተፎካካሪ (ተቃዋሚ) የሚባሉ ወገኖችን ለማገትና ለመደምሰስ የሚያደርገዉ ጉዞ ወቅት ከመሆን የተለየ መሆን ይችላል ብሎ መገመት አይቻልም። ለብልጽግና ማሸነፍ (ሠርቆም ሰብሮም) የህልዉና ጉዳይ ነዉ። በዚህ ጉዞ ገላጋይ የሚባል ምንም አካል አይኖርም፤ ገለልተኛ ሊሆን የሚጥር ካለም በብልጽግና አይፈቀድለትም። በተፎካካሪነት (በተቃዋሚነት) የቆሙ ወገኖች ይሄንን ተረድተው ይህንን አደጋ ለመቋቋም መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።

በሌላ በኩል፤ በቀጣይ የህዝብ ትግል ፤ ይህ የዴሞክራሲ ጉዞ ሰምሮ መንግሥትና ፓርቲ ቢለያዩ፣ በመንግሥት ሥራ ላይ የተሠማሩ፣ በፓርቲዉ ምክንያት ጥቅም የነበራቸዉ ወገኖች ከፓርቲዉ ይለያሉ። እናም በሚልዮን የሚቆጠር ደጋፊ ካልሆነ አባል የሚኖረዉ ፓርቲ አይኖርም። ይሄም ጉዳይ ታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይንና ጓዶቹን ያስጨንቃቸዋል። ለዚህ ነው ብልጽግና ፓርቲ “ተመርጦ” መንግሥት ቢሆን መንግሥትንና ፓርቲን መለየት የማይችል አካል የሚሆነው።

አሁን ባለው ሁኔታ ታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይ ወደ አምባገነንነት ጉዞውን ለማስቀጥል ብልጽግናን መሳሪያ በማድረግ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ጥቂትም ቢሆኑ በቅንነት ወደ ዴሞክራሲ መሸጋገርን አላማ አድርገው የተነሱ ወገኖችን ይፈታተኑኛል ብሎ ስለሚያስብ፤ በተለይም መሰረት አላቸው ብሎ ከሚያስባቸው ቦታዎች (ከክልል) አመራር በማንሳት ወደ ፌዴራል በማምጣት ማንሳፈፍና እርሱ በተመቸው ጊዜ የማስውገዱን ስራ ይቀጥላል። አሁን በትንሹ ከምናየው ወደፊት መተንበይ የምንችለው … የዚህ ፓርቲ አባላቱ በሙሉ ለታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይ ታማኝነትና ታዛዥነት የተለየ ምርጫ እንደማይኖራቸው ነው።

መንግሥታዊ ፓርቲ እያለና እየመራ ወደ ዴሞኪራሲ ለመሸጋገር የተቻለበት ቦታ የለም። ለምን ቢባል የራሱን ጉድጓድ የሚቆፍር፣ የራሱን ህልዉና የሚያከስም በተለይም እጁ በደም የተጨማለቀ፣ ኪሱ በሥርቆት የኮረበተ ኣካል አለ ብሎ ለማመን ስለማይቻል ነው። ትልቁ የትግላችን ስህተትም የሽግግሩን መሪ መንግሥታዊ ፓርቲ ለሆነ አካል መስጠቱ ነበር።

ትልቅ መስዋዓትነት ለከፈልከው የኦሮሞ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች የምናስተላልፈዉ መልዕክት፣ ትልቁን የሽግግሩን መሪ ምርጫ ስህተት ሰርተናል። መጭው ምርጫ አሁን በምናየው የታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይ አካሄድ፤ አንተ እንዳሰብከው ፍትሀዊ፣ ነጻና ተገዳዳሪ አይሆንም፤ ይሁን እንጂ ወደ ዴሞኪራሲ ለመሻገር በምታደርገው ጉዞ ሌሎች ወደሚዘረጉልህ ወጥመድ መግባትን ትተህ የኔ የምትላቸው ድርጅቶችህ ከጎናቸዉ ቆመህ፣ ራሳቸዉን በሥልጣን ላይ ለማቆየትና ያንተን መብት ለመርገጥ የቆሙ ወገኖችን አላማ ለማጨናገፍ በጀመርከዉ የሰላምና የሰላማዊ ትግል መንገድ አንድነትህን አጠንክረህ እንድትገፋበት ነዉ። ከአሁን ጀምሮ የሚነሱ ማንኛዉም ሁከቶችና ረብሻዎች አነሳሾቹ መንግሥት ካልሆኑ ህልዉናቸዉ አደጋ ላይ ያሉ የ”ብልጽግና” ሰዎች መሆናቸዉን አትዘንጋ፤ በሌላ ማላከክንም አትፍቀድላቸዉ። ዴሞኪራሲያዊ ሽግግር ላንተ አማራጭ ወደሌለው ማንነትህ ተከብሮ፡ በራስህ ግዛት ራስህ እያዘዝክበትና እየተዳደርክበት፤ በጋራ ወደምትገነባው ህብረ ብሄራዊ ዴሞክርሲያዊ ፌዴሬሽን መሸጋገር እንደሆነ አትዘንጋ። ይሄንን ለሚያጨናግፉ እድል አትስጥ።

ከዚህ ዛሬ ከደረስንበት አጣብቅኝ ለመላቀቅ ተቃዋሚ ወይንም ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንድን ግለሰብ በማምለክና ማዕከል በማድረግ የተገነባ የፓርቲ ህይዎት፤ ዕድሜ ልካቸውን ከፓርቲ አመራር ከማይለቁ ግለሰቦቸ ተላቀው፤ ሀሳብን ማዕከል ባደረገ የትግል ስልትና ሀገርን ለማስተዳደር የሚያስችል ድርጅታዊ ተቋም ግንባታ ላይ ያተኮረ ሰላማዊ ትግል በማካሄድ ለዴሞክራሲያዊ ሽግግር የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የህዝብን ጥቅም ማዕከል ያደረገ የትግል ስልት በመንደፍ ትግላቸውን አቀናጅተው አቅማቸውን በመገንባት ብልጽግና ፓርቲን በመገዳደር ወደ ፖለቲካ ስልጣን የሚመጡበትን መንገድ መቀየስ አለባቸው። ብልጽግና ፓርቲንና መንግስትን በመለየት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ፍቃደኛ ካልሆነ፤ ስጋታችን በሀገሪቱ ዴሞከራሲ ህልም ሆኖ እንዲቀር ከማድረግም አልፎ ሀገር እንዲበታተን መንገድ መክፈቱ ነው።

በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የሚዲያ ተቋማትም ወይ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ የሚያቅራሩ፤ አለያም የተቃዋሚ ወገኖችን ለቅሶና ዋይታ ብቻ የሚያዥጎደጉዱ፤ የጥቁርና ነጭ ዜና አቅራቢዎች መሆን የለባቸውም። ይህ አይነት አካሄድ ትግሉን ዕዳር ለማድረስም ሆነ ለዴሞክራሲ ግንባታ አያገለግልም። ለዚህ ብዙ መስዋዕትነት ለተከፈለበት የሽግግር ጉዞ መሳካት የሚዲያ ተቋማት የህዝብ ወገን በመሆን የመንግስትን/ብልጽግና ፓርቲ አካሄድ እንዲሁም የተቃዋሚዎችን ድክመቶች በመተቸት ላይ ቢሰማሩ ምናልባት ወደ ዴሞክራሲያዊው ሽግግር ለመመለስ ያለንን እድል ያግዙ ይሆናል።

የዛሬው ብልጽግና ፓርቲ መሪ በህዝብ ትግል ተገፍተው ከሚያገለግሉት አለቃ (ወያኔ)ተላቀው ከህዝብ ጎን ቆሜአለሁ ብለው ሥልጣን እንደያዙ ሁሉም የሚያውቀው ነው። ነገር ግን የብልጽግና ፓርቲ መሪ ስልጣን ከያዙ በኋላ የህዝቡን ጥያቄዎች ወደ ጎን ትተው ለራሳቸው ጥቅምና፤ የበላይነት ለማስፈን በአምባገነንነትና በማን-አለብኘነት የሞተውን አሮጌ የነፍጠኞች ሥራዓት ከመቃብር አውጥተው የማንሰራራትና የማጠናከር የህልም ጉዞ ላይ ናቸው። በዚህ የህልም ጉዞ ከተቀጠለ ማንም ልስተው የማይገባ ጉዳይ ግን፤ የህዝቡ ትግል ይበልጥ ተጋግሎ የታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይንም መጨረሻ ከቀድሞው ኮሎኔል የማይለይ እንደሚያደርገው ነው። ከቀደመው ኮሎኔል ምናልባት የሚለየው፤ የህልውና ጊዜው ታጋይ ኮሎኔል ዶ/ር አብይ ከሚያስበውና ከሚያልመው በተፃፃሪው በጣም አጭር መሆኑ ነው። የብልጽግና ህልውናም እንዲሁ አጭር ነው። የህይወትና የደም ዋጋ የተከፈለበትን የህዝብን አደራ ወደ ጎን ትቶ ለረጅም ጊዜ መቆየት አይቻልምና።

4 Comments

 1. በስመ ቅዱስ፣ ጠቢብ፣ ታጋሽ፣ ቸር፣ ፈጣሪ፣ ፍፁም፣ አንድ፣ አምሳል፣ ዋቅ አምላክ፤ አሜን።
  …………………….
  ለመላው የዋቄፈና ሃይማኖት በተለይ
  ለሌሎች ወንድም የእስላም እና ክርስትያን ምእመን የኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ መልእክት:-
  ……………………
  ኢትዮጵያ ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በመሲሁ ደጃል (ሀሳዊ መሲህ) ፈተና ስር ወድቃ፣ በደጃሉ የክተት (የመደመር) አዋጅ ወይ የደጃሉን ብልፅግና (ገነት) ወይም የዘር ጥፋት ምረጡ እየተባልን ባለንበት በዚህ ፈታኝ ወቅት በተለይ የሃይማኖት መሪዎችና የማህበረሰብ የበላይ ጠባቂዎች እውነት በአንድ አምላክ እናምን ከሆነ የሀሳዊ መሲሁን (የመሲሁ ደጃል) ሌተናል ኮሎኔል ሰላይ ዶክተር አብይ አህመድ ዘእምነገደ ጉራጌ ወብሄረ ኤርትራን ወደር የለሽ የጥፋት ሴራ ተልእኮ በማክሸፍ ረገድ ባለን አቅም ሁሉ በመስራት ህዝቦቻችንን እና እናት ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከጥፋት እንታደጋት ዘንድ ጥሪዬን በቅዱስ የኢትዮጵያ ዋቅ ስም አቀርባለሁ።
  በዚህ ዘመን መሲሁ ደጃል በኢትዮጵያ መሬት ላይ መገኘቱ አስፈሪም አሳፋሪም ነው።
  መሲሁ ደጃል ወይም ሀሳዊ መሲህ የሁላችንም የጋራ ጠላት ነዉ።
  በዋቄፈና፣ በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች በሁላችንም በእኩል የተወገዘ ሉሲፈር ነው። የሀሳዊ መሲሁ ደቀ መዘምራኖቹ እነ ዳንኤል ክብረት፣እነ ምህረት ደበበ፣ ባልደረቦቹ (አስሃቦቹ) እነ አቡበክር አህመድ፣ ካምል ሸምሱ እና አህመዲን ጀበል እንዲሁም ሌሎችም አለክላኪ የዲያብሎስ (የእብሊስ) ተላላኪዎች የኢትዮጵያ ህዝብን በመከፋፈል እነርሱ በሚቀርፁት የጥፋት አጀንዳ እየተጋጨላቸው ይገኛል።
  የኢትዮጵያ አፄዎች የፖለቲካ መሪ እንጅ ፃዲቃን መላእክት ሆነው አያውቁም። የኢትዮጵያ መሪ መሆን ማለት ለአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ብቻ እንደሆነ ማሰብ መሰረታዊ
  .

 2. ስህተታችን ነው። አማርኛ ተናጋሪ መንግስት ጥፋት ቢሰራ ተጠያቂው ያው መንግስት ከሌለ ደግሞ ተተኪው የዘመናችን መንግስት ሊሆን ሲገባ በንፁህ ማህበረሰብ ላይ ያነጣጣረ እይቻን ትክክል ካለመሆኑም በላይ ወደ መፍትሄ የማያመራን ይሆናል። አብይ ኦሮሞ እና አማራን ካላጋጫቸው በስተቀር በስልጣን ላይ መቆየት አልችልም በሚል ሰንካላ ሀሳብ የሚንቀሳቀስ አደገኛ አውሬ ነው። እስልምናን ከክርስትናም እንደዚሁ ነው የሚመለከታቸዉ። ይህ የአቅመ ቢስ ለስራ ያልታደለ ጠፍ አእምሮ ተንኮል ባለ ተንኮሉን ይዞ እንደሚጠፋ የዋቄፈና ሃይማኖታችን የሚያስተምረው እውነት ነዉ። የክርስትናው (የስመት) እና የእስልምና (የድነት) ሃይማኖቶችም በዚህ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው አውቃለሁ።
  መሲሁ ደጃል የትግራይን ህዝብ ወይም ተወካዩን ህ.ወ.ሃ.ት.ን ነቀርሳ፣ የቀን ጅቦች ብሎ አዋርዷቿል። የእነርሱ ውርደት እንደ ሀገር ለሚያስብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ውርደቱ ነዉ። ደጃሉ ይህን ያለው የሪሞት (የሩቅ) ጌታውን፣ አምባገነን፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት የህሳይያስ አፈወርቅን ቃል ለመከወን እንደሆነ ልብ ልንል ይገባናል።
  የደጃሉ የክተት (የመደመር) ስብከት የመነጨው ታላቁን የኦሮሞ ህዝብ በመፍራት እንደሆነ ግልፅ ነው። ብልፅግና (ገነት) የተባለው ደግሞ የዋቄፈና ሃይማኖታችንና እስራኤል በሙሴ አማካኝነት ከዋቄፈና ከወሰደችው የሰላምና የብልፅግና አርማ ከሆነው የኦዳ ዛፍ (Fig
  tree) ትምህርት ስሙ ተቀድቶ
  አርማው ደግሞ እስላምን ለመደለል ከሳውዲ አረቢያው አል-ሰቢል ዩኒቨርሲቲ 15% ብቻ ማሻሻያ ተደርጎለት ለማታለያነት እያዋለው ይገኛል።
  ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያኖች ሆይ፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ከኛ የምትሻው አንድ ነገር ብቻ ነው። ይህም አምላክን በሰጠን አእምሮ በሰከነ መንፈስ ተደማምጠን ቀደም ሲል የነበሩ መንግስታት በሁላችንም ላይ በመሆኑ

 3. አንደኛችን የሌላችንን ይቅርታ መጠበቅ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሁላችንንም ይቅርታ በመጠየቅ እንደ ህዝብም እንደ ግለሰብ ተገቢ የጉዳት ካሳ እንዲከፍለን ለማድረግ እንድንችል አስቀድመን ደጃሉን ከሳሎናችን ማስወገድ አለብን በማለት አደራ ሰጥቻቿለሁ።
  ክቡራን ፓትርያርኮች፣ ካርድናንድ፣ ሙፍቲዎች፣ እና ፓስተሮችም ይህንን የኢትዮጵያ ዋቄፈና ሃይማኖትና የአባ ሙዳን አቋም እውነትነት በመገንዘብ ስለ እውነት ብላችሁ ሃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪዬን በቅዱስ ዋቅ ስም አቀርባለሁ።
  ………………………
  ሆራ (አምላክ ይባርካችሁ) ።
  ቡላ (አምላክ እድሜ ይስጥልኝ)።
  ሆፎላ (ቅን ሀሳባችሁ ይሳካላችሁ)።
  ……………………
  የኢትዮጵያ: ፍፁም እውነት ሀገር ኦርቶዶክስ ዋቄፈና ሃይማኖት
  ሰማያዊ ምድራዊ ነፍስ መጋቤ እውነት አባሙዳ ዘብሄረ ሆር (ኦሮሞ)
  ነገደ ሸገር መንበረ መደወላቡ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.