የአውራ ፓርቲው መሪነትና የ ”አጋሮች” እጣ ፈንታ

የአውራ ፓርቲው መሪነትና የ ”አጋሮች” እጣ ፈንታ

በዩሱፍ ያሲን – ኦስሎ, August 28, 2018

በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እረፍት ማግስት የህልፈታቸው እንደምታዎችን አስመልክቶ ኢሳት ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌና ለእኔ ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። የዛሬ 6 ዓመት መሆኑ ነው። በእሳቸው ሞት አባት አልባ (Orphan የእሳቸው ቃል ነው) እጓለ መውታ ይሆናሉ ያሏቸው ቅርበት የነበራቸው የሁለት ሰው ስም ጠቅሷል። ወይዘሮ አዜብ መስፍንንና አቶ በረከት ስምዖን። ትንበያው የያዘላቸው ይመስላል። ሁለቱን የፖለቲካ ስዎች የመለስ ዜናዊ ሞግዚትነት ማጣት የፖለቲካ ኮከባቸው እያዘቀዘቀ መጥቶ ኮስምነው፣ ኮስምነው ለጥቃት አመቻችቶ አጋለጣቸው። የፖለቲካ እጓለ ሙታን ቢባሉ አያስገርምም ለማለት ነው።

በታዳጊ ክልሎች የስልጣን ተጋሪ ባይሆኑም ቅሉ የኢሕኣዲግ አጋር ተብለው በ 5 ክሎሎች ማለትም በሶማሌ፣ በአፋር፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምበላና በሓራሪ በስልጣን የተፈናጠጡት ገዢ ፓርቲዎችና የብሔረሰቦችና የሕዝቦች የስልጣን ኤሊቶች ”አጋርነታቸው” ለፈጣሪያቸው ለአውራው ፖርቲ ኢሕዴአግ ነበር። ልክ እንደ መጽሓፍ ቅዱሱ (ዘ-ፍጥረት ወይም መቅድመ ወንጌል?) እግዚኣብሔር የፈጠራቸው መላዕክትን ፈጥሮ ለተወሰነ አጭር ጊዜ የተሰወረባቸው ፍጡራን ተጠፍጣፊ አስመስሏቸዋል። ግራ እየተጋቡ ናቸው። ምክንያቱ የኢሕአዲግ አራቱን ብሔራዊ ድርጅቶች ከግንባር ወደ ውሁድ ፖርቲ በሚለወጥበት ወቅት በታዳጊ ክልሎች ያሉት ”አጋር” ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶችም ወደ አዲሱ አንድወጥ ፓርቲ እንደሚቀላቀሉ ነበር እቅዱም፣ ፍላጎቱም ፣ ሕልሙም። ዓረቦች እንደሚሉት ንፋሱ ለጀልባዎቹ የጉዞ አቅጣጫ በተጻራሪ አቅጣጫ መንፈስ ተያያዘው ሆነና ኩነቶቹ ፊታቸውን አዞሩባቸው። ነገር ዓለሙ ተገለባበጠባቸው። እንኳን የእነሱ እጣ ፈንታ የፈጣሪያቸው ጠፍጣፊያቸው እጣ ፋንታ አነጋጋሪ ሆነና አረፈው። እሱም ድርጅቶቹ በጥቅምት ያደርጉታል በሚባለው ጉባያቸው እልባት ያገኝ ይሆናል። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የመዋሃዱ እቅድ እንዳለ ነው ቢሉም ውህደቱ በቅርብ ይጠናቀቃል ተብሎ አይታሰብም። አጋሮችን የመጠርነፉ እቅድ እየራቀ ይሄዳል ማለት ነው። የኢሕዴኣግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሁሉም ነገር በታቀደው አኳኋን በመከናወን ላይ እንደሆነ ቢያረጋግጡም ቅሉ። እንደውም ቃል በቃል ለመጥቀስም መግለጫው የተጀመረውን የለውጥ ሂደት እንደሚቀጥል ካረጋገጠ በኋላ ኢሕኣዲግ በተለመደው ድርጅታዊ ባህል፣ ዲሞክራሲያዊነትን በተላበሰና በሰከነ አግባብ ሂደቶችን በጥልቀት ገምግሟል ብሎ ያሰርጋል። እነዚህ ሁሉ ያልተለመዱ አባባሎች አይደሉም። እንዲያውም ለሰሚው ያሰለቹ ናቸው ቢባል ምንም ማጋነን የለበትም። ታዛቢዎቹ የሕወሓት መሪዎች ከስብሰባው መለስ መቕሌ  ከተመለሱ በኋላ የሚሉትን ነው የናፈቃቸው። ለምን ቢባል  በሁለት ቀን ስብሰባ ያ ሁሉ ቅሬታ መልስ ማግኘቱን ስለሚጠራጠሩ። ከሁሉ በላይ ግን ድርጅቶቹ በውስጠ ደንባቸው ላይ ለማከል የሚዘጋጁት ማሻሻያ ሓሳቦች ላንድወጥ ፓርቲነት የሚያዘጋጃቸው ሳይሆን ለየራስ ድርጅታዊ ሕልውናቸውን የሚያጠናክሩ ናቸው። የሚዋሃዱ ከሆነ ስሞቻቸው መቀየሩ ምን አመጣው ሌላ ጥያቄ። በተግባር የሚገለጽ የዓላማ አንድነት የኢሕዴኣግ የዘውታሪ ቃል ዓላማ ነው። እሱም ቢሆን በቀላሉም በቅርቡ የሚተገበር መፈክር አይሆንም።

ስለ መፈክሮች ካወራን ዘንድ ኢሕዴኣግም ሆነ ሕወሕት በርካታ የመፈክር ጋጋታ ነበረው። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጠፊያ ሲያጥራቸው የሚያደናግሩበትና ስሚ የሚያደነባቡርበት የትዮሪ አረፋ ያስነሱ ነበር። ገና ደደቢት በረሓ እሱና ሰዬ አብርሃ ከተጻራሪ ግንባሮች ጋር ለመከራከር በኮሞኒስት ቲዮሪ ልቀው እንዲገኙ ድርጅቱ ካሰማራቸው ጊዜ ጀመሮ የተካኑት አካሄድ ነው። በኋላ ላይ አረጋዊ በርሔናና ግደይ ዘረጽዮን ከሜዳ ያባረሩት በዚሁ የቃላት ጋጋታ ነበር። ቦርዡዋ፣ ቦናበርቲዝም፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ልማታዊ መንግስት በእዚህ ትጥቅ የሚደመሩ ወንጭፎች ነበሩ። ዛሬ ቀለሃው በየቦታው ተበትኖ ቀርቶዋል፣ እንጂ።

”አጋር” ድርጅቶችም ከሲቪል ኮሌጅ በተመረቁ ጥቂት መሪዎቹ ጧት ማታ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ጥልቅ ተሃድሶ፣ ብለው የሚደሰኩሩት እምበለ ምክንያት አይደለም። እነ አብዲ ኤሊ የመፈክር ጋጋታ አላስፈለጋቸውም። ልዩ ኃይል በማሰማራት በሕወሓት የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ተወጡት። ከጦር ሜዳ አብረው የመጡት እንደ አፋር ክልል መንጁሶች (የልጅ ወታደሮች) የሲቪል ኮሌጅ ካድሬነት ኮርስ አላስፈለጋቸውም። በክልላቸው ላይ በላይ መመሪያ ይዥጎዶጎድላቸው። ትናንትም፣ ዛሬም። ምክንያቱ ከሕወሕት ጋር የነበራቸው እትብት አልተቆረጠምና። አንዳንድ ካድሬዎች ታማኝነታቸው ወደ አዲሱ አመራርና ባለተራው ብሔራዊ ድርጅት ለማሸጋገር እየሞከሩ ነው።ገሚሶቹ እየተንገላቱ ናቸው። እንደከላይ የተጠቀሰው ፈጣሪያቸው የተሰወረባቸው አመልዕክት ፈጣሪያቸውን ለመክዳት እያኮበኮቡ ነው። መቼም ከእነሱ መሓልም ”ንቁም በባህላዊነ እስከ ንረክቦ ለፈጣሪነ (አምላካችን እስከምንገናኝ በእምነታችን ጸንተን እንኑር)” ብሎ የቅዱስ ገብርኤል ሚና የሚጫወት እምነት ጠንካራ አይጠፋም። ሕወሕት አሁንም አፈር ልሶ ይነሳል ብሎ ትንሴውን የሚጠባበቅ። በእዚህ ግንባር የአፋር ክልል መሪዎች አቋም ጠንካራነታቸውን ሳያሳዩ አይቀሩም ተብሎ ይተነበያል።

”አጋሮች” የሚመሯቸው ክልሎች በኋላ ቀርነታቸው (ታዳጊነታቸው) የዳር ሃገር ከመሆናቸው ውጭ ከሚያመሳስላቸው ይልቅ የሚያለያያቸው ባሕሪያት ያመዝናሉ። በሕዝብ ብዛት፣ የማሕበረሰብ ስብስቦች ጥንቅር፣ የፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍ ወዘተ አይመሳሰሉም። ያለ ሞግዚት ለጋራ ዓላማ የሚያስተባብራቸው ሃይል ሳያስፈጋቸው መቼም አይቀርም። ድሮ መገናኛቸው የኢሕዴኣግ ጉባኤ ነበር ማለት ያስደፍራል። የብሔረሰቦች ቀን ሲያከብሩም አብረው መጨፈሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው። የጋምቤላ ዲሞክራሲያዊ ድርጅትና የሶማሌ ፓርቲ፣ የሓራሪና ቤንሻንጎል ጉሙዝ ገዢ ፓርቲ ከእዚ ውጭ ጥረቶቻቸውን የሚያስተባብሩበት መድረክ አልታይ ብሎኝ ነው።

በኢሕዴኣግ ግንባር ውስጥ ስለተፈጠረ መመሰቃቀል በአጋሮች ዘንድ ያስከተለው ግራ አጋቢና አስቸጋሪ ሁኔታ አወሳሁ እንጂ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ማህበረሰቡና ያማገሩት ተቋማት ሁሉ ጤናቸው የተሟላ አይደለም። ሥርዓቱ እየተናወጠ ነው። ምን ይገርማል ታዲያ በአብዮታዊ ሽግ ግር ላይ መሆናችን ከታመነ ሊባል ይችል ይሆናል። አብዮት ደግሞ የሕብረተሰቡ ሹም ሽር ነው ይላል የ 68ቱ ካድሬው። ዶ/ር ዓብይ አህመድ ኢትዮጵያን ከእርስ በእርሱ ብጥብጥ አፋፍ፣ እፍፍ አደረጋት ተባለ እንጂ ባለፉት 27 ዓመታት ከሚያገናኙ መግለጫዎቻችን ይልቅ በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ ሆን ተብሎ ስለተተኮረ ሕብረተሰቡ የገባበትን ቀዛቃዛ እርስ በእርስ ጦርነት አላበረደውም። እንደ ጓደኞቹ ያንዣበበው ስጋት በፍቅር አስወጋጅ ዝማሪን አብሬ ብዘምርለትም በወደፊቱ አብሮነታችን ቀመር ላይ እንኳን የሁሉ ስምምነት  አልተበጀም። ገና በርካታ ውይይት፣ መግባባትና ስምምነት ሊደረስባቸው የሚገባ ዓበይት ጉዳዮች አሉ። በቅርቡና የመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫ በርካታ ጉዳዮች ተብራርቷል። የለውጡ አስተማማኝነትን የሚያረጋግጡ መተማመኛዎች ተሰጠዋል። እስከ 2012 (2020) ምርጭ ድረስ ግን በእርግጠኝነት መነጋገር አዳጋች ነው። ለምን ወደዚያ እንሄዳለን። የጥቅምቱ የኢሕዴአግ ጉባኤ የሻዕቢያ ካድሬዎች እንደሚያዘወተሩት  በዓወት ተዛዝሙ  (በድል ተጠናቀቀ) ካልተባለ። ካልታዘልኩ አላምንም እንዳለችው የገጠር ሙሽራ ጥርጣሬ እያንገላታን ነው!

1 Comment

  1. METEC mercinaries were too busy stealing not only from the Abay dam project but from everything in Ethiopia, that is why the METEC mercinaries did not enough have time to commit the genocide as Meles wanted to see during his lifetime.Metec was there involved in the Abay dam project only to make sure the dam will be constructed in a way that the dam eventually will collapse then flood flows towards to Tigrai. Meles made sure the foundation of the Abay dam is not upto standard on purpose so that the dam collapses with flood rushing to flow down to Tigrai , washing all fertile soil on the way bringing it to Tigrai while expediting the genocide of Benishangul / Amharas on the way too. Meles wanted Tigrai to have fertile soil of Amhara and Benishangul. The flood is expected to wash fertile soil of Amhara and Benishangul Gumuz bringing it to Tigrai and also do the genocide of Amhara people and Benishangul people. Metec succeeded in it’s mission so METEC took a 5 Billion birr tip for the main METEC employees that kept the secret while accomplishing their real mission .The money was there since rich business people in Ethiopia and diasporas sent it so METEC took it. Recent survey conducted by the Ethiopian workers union shows that Most Ethiopian’s that are employed by rich Ethiopian business people get paid only enough to feed their family members once a day, since the rich Ethiopian business owners are sending the profit money to the Abay dam bond rather than raising their employees income.

    As we all know the genocidal regime of Meles didnot succeed in wiping out other ethnicities with bullet because the METEC mercinaries failed to do so. Meles tried everything he can think of to wipe out the Amhara and Oromo etnicity from the face of this earth. Meles used Shabiya during the Badme war to kill those Ethiopians that had potential of threatening Meles’s grip on power. Basically Meles intentionally sabotaged Ethiopians so they did not make it back from the Badme war. The first round of the 1998 war was extremely screwed-up and gruesome, it was an extremely inept and embarrassingly flawed war plan from the beginning because Meles wanted those Amharas dead along with other Ethiopians that got potential to threaten his grip on power, he wanted them dead..The Badme war was badly planned because Meles wanted those Ethiopians that got potential to threaten his grip on power dead.No one to date has been held accountable for the wasted treasure in blood because Meles and METEC wanted those “tmkhtegna Ethiopians ” dead . METEC IS NOW RUN BY AZEB MESFIN ..
    For those that survived the Badme war who were talking ABOUT THE WAY HE LED THE WAR Meles resorted to give them something that keep them busy to keep the focus away from him(that something he gave them to get his focus away from him was a fake dam). It worked on some but not on all, that’s why the focus remained. While some people including some diaspora Ethiopians were busy talking about the dam, less talk was done about Meles’s crimes against humanity. Then he came up with one more plan on how to wipe out BENISHANGUL&Amharas -a flood.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.