የአድዋ ጦርነት እና ኦሮሞ

የአድዋ ጦርነት እና ኦሮሞ

አድዋ ተጨቋኞች ተገደው ጨቋኞቻቸውን ከኢጣሊያ ወራር ነጻ ያወጡበት ድል ነው!

በመጀመርያ ደረጃ ጦርነቱ የተካሄደበት ጊዜ “ኢትዮጵያ” የሚባል ሀገረ መንግሥትም አልነበረም።

መጋቢት 06, 2021

የኦሮሞ ጦር መርዎች እና ፈረሰኞች የአድዋ ጦርነት ላይ ያሳዩት ጀግንነት አይካድም። እንዲያውም የኦሮሞ ጦረኞች በጦርነቱ ላይ ከፍት ተሰልፎ ተዋግቶ ባይዋጉ ኖሮ ድል የሚባል ነገር አይታሰብም ነበር። ነገር ግን፡ የኦሮሞ ጦረኞች ጣልያንን የተዋጉት የምኒልክ ቀኝ ተገዥ (ገባር) በመሆን ነው እንጅ እንደ ነጻ ህዝብ አልነበረም። የአድዋ ጦርነት የተካሄደ ጊዜ (1896 እአአ) የኦሮሞ ህዝብ የምኒልክ ወራር ሃይል ከውጭ በእርዳታ ባገኘው የጦር መሣሪያ በጨለንቆ እና አኖሌ ከደረሰበት ግፍ እና ጭፍጨፋ ገና አላገገመም ነበር። የመሀል ሀገር ኦሮሞ እንደሆነ ቀድሞዉኑ በሃይል የአቢሲንያ አካል ተደርጎ ስለነበር ወዶ ሳይሆን ተገዶ በነቅስ አድዋ ላይ እንድዘምት ተደርጓል። እነ ገበየሁ ጉርሙ፣ ቁሴ ዲናግዴ፣ ባልቻ ሣፎ እና ሌሎች የጦር መርዎች በጦርነቱ ላይ ከምኒልክ ጎን የተሰለፉት ልክ ኬንያኖች፣ ናይጀርያኖች እና ህንዶች WWI እና WWII ላይ ከቀኝ ገዥያቸዉ ኢንግሊዝ ጎን በመሰለፍ እንደተዋጉት ዓይነት ነው። ልዩነት የለውም።

በመጀመርያ ደረጃ ጦርነቱ የተካሄደበት ጊዜ “ኢትዮጵያ” የሚባል ሀገረ መንግሥትም አልነበረም። ከጦርነቱ በፍት የነበሩት አስርት ዓመታት እና በጦርነቱ ማግስት የኦሮሞ እና የደቡብ ህዝቦች ለዘመናት የነበራቸው ሉዐላዊነት በምኒልክ ወራር ሃይል (ነፍጠኛ) ተደፍሮ የአቢሲኒያ ኤምፓየር ሥር ለማጠቃለል ተከታታይ ዘመቻ ስደረግበት የነበረ ወቅት ነው። አንድ ሀገር (ብሔር)፣ አንድ ቋንቋ እና አንድ ሃይማኖት በመተት እና በአሻጥር ነጻነቱን ጠብቆ ለዘመናት ስኖር የነበረው ኩሩ ህዝብ ላይ የተጫነበት ጊዜ ነው። እንግድህ የኦሮሞ እና ደቡቡ ጦረኞች አድዋ ላይ የተሳተፉት በተጫነባቸው የባዕድ ማንነት እና በቀኝ ተገዥነት ስሜት ነው። ከምኒልክ በኃላ አጼ ኃይሌስላሴም ቢሆን “ኢትዮጵያ” የሚትባለውን ሀገረ መንግስት መስርቶ ኤምፓየርነቷን አጠናክሮ የቆየው አንድ ሀገር (ብሔር)፣ አንድ ቋንቋ እና አንድ ሃይማኖት በሚል ትምክተኝነት እና ጠባብነት ነው። ዛሬ ድረስ ያልተመለሰውን የኦሮሞ፣ የኦጋደንያ፣ የአፋር እና የሌሎች ጭቁን ህዝቦች የተደራጀ ብሔራዊ የነጻነት ጥያቄ የተፈጠረውም ይሄንን የባዕድ አገዛዝ ገርስሶ የራስን ነጥጻነት መለሶ ለመጎናጸፍ ነው። ይሄንን እውነታ አድበስብሰን ማለፍ የለብንም።

እኛ የዛሬ ትውልድ፡ የዚች ሀገር (“ኢትዮጵያ”) የቀኝ ገዥነት እና ተገዥነት እንድሁም የግፍ እና ጭቆና አገዛዝ ታርክ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰን ይቅር በመባባል ተፈቃቅዴን አብረን ለመኖር ወይም በሠላም ተለያይተን በጥሩ ጉርብትና ለመኖር እስካልወሰንን ድረስ፤ ዛሬም እንደ ትላንቱ በባዶ ፉከራ እና ሽለላ እንድሁም በቃላት ጋጋታ ብቻ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖር” ”አንድ ሀገር” “አንድ ምናምን” “እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያልን አንዱን እንደ ጠላት፣ ሌላውን እንደተቆርቋር እያሰብን መቀጠል አንችልም። በዚህ ጉዳይ ላይ ፈጽሞ ውዥንብር ውስጥ መግባት የለብንም። በግዘያዊ ጥቅም ተታሌን እውነተኛውን ታርክ መካድ የህሊና ተወቃሽ እንደምያደርገን መርሳት አይኖርብንም። የአጼ ምኒልክ የአድዋ አኩሪ ታርክ ስዘከር፤ በአኖሌ እና በጨለንቆ በንጹሐን ኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍ እንድሁም በከፋ እና ወላይታ ህዝብ ላይ የንጉሡ ወራሪ ሃይል ያደረሰው አስከፍው የጭፍጨፋ ታርክ ሊካድ አይገባም። ለዚህ አስከፍ ታርክ የመታሰቢያ ሐውልት ማቆም ስያንስበት ነው እንጅ አይበዛበትም። ነገር ግን፡ የነፍጠኝነት እና የገባር ሥራዓት ትላንት በንጽሐን ህዝብ ላይ የፈጸመውን በደል እና ግፍ በግልጽ ኮንነው የታርክ ተወቃሽ ከማድረግ ይልቅ ዛሬም አንዳንዶች “የነፍጠኛ ዘር ነኝ” “ነፍጠኛ ነኝ” በማለት ስኩራሩ ማየት የሚያሳዝን ነው። ትውልድን በሐሰተኛ ታርክ አደናግሮ ወደፍት ለመራመድ መሞከር ቅልነት ነው። የጠቅላይነት እና ኤምፓዬርነት አካሄድ የትም አያደርስም።

የሚያዋጣው ላለፈው ጊዜያት አስከፍም (መጥፎ) ሆነ በጎ ታርክ ላይ መግባባት በመፍጠር፣ ይቅር በመባባል፣ ለብዛሀነቶች ዕውቅና በመሰጣጠት በእኩልነት እና ድሞክራሳዊነት ላይ የተመሰረተች አገር መስርቶ አብሮ መኖር ነው። ካልሆነ ትውልድ ወደ ሌላ አማራጭ ማማተሩ አይቀርም… ግልፅ እና አስተማማኝ እንቅስቃሴዎችም ከተጀመሩ ስንብቷል።

ኢምፓየሯ እና ጨቋኛ ኢትዮጵያ በቁሟ ከሞተች የሰነበተች ቢሆንም ግባዐተ መረቷ በቅርብ ቀን እነደምፈጸም ቅንጣት ያሀል አያጠራጥርም!

ክብር እና ሞገስ ለጭቁኑ የአድዋ ሰማዕታት!

ጌቱ ሣቃታ ሮሮ

03.02.2020

ፊንፊኔ “አ.አ” ኦሮሚያ

1 Comment

  1. Gofta koo!
    ባለፉት 5 ዓመታት ስከራከርበት የነበረውን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2 ዓንቀፆች አሣምረህ ስለገለጽክልኝ እጅግ በጣም ላመሰግንህ እወዳለሁ። Please, Sir, accept my heartfelt appreciation!

    በግሌ ከቅኝግዛት አፍቃሪ ነፍጠኞች በስተቀር ከማንም ጋር አብሬ በፍቅር በመተሳሰብ መኖር እችላለሁ እንደ አገር ግን ኦሮሚያ ቢበዛ ከ3 ብሔሮች በላይ እንደ አንድ አገር ሆና(ሆነን) መኖር አንችልም/የለብንም የሚል ሃሳብ/አስተያየት አለኝ። አብረን የምንኖረው ብሔር ቋንቋችን ከዳር እዳር ሊናገር እኛም ቋንቋቸውን ከዳር እዳር ልንናገር እና በጋራ በምንመሰርታት አገርም ማንኛችንም ያለስማበለው እንድንዳኝ ዳኞቻችን ሁሉ የምንመሠርታት አገራችንን ቋንቋዎች በሚገባ ማወቅ ይገባቸል። ይህ ደግሞ የዜጎቻችንን መብት ሳንቀማ የነሱንም ሳንቀማ ሁላችንም የኛ የምንለው አገረ መንግሥት በተግባር መመስረት ያስቸግራል።

    ቅኝገዢያችን ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ እንዳትበታተን ቅኝግዛት አፍቃሪ እና ተንከባካቢ መሆን አይጠበቅብንም። ትፍረስ ትበታተን። ቅኝግዛት መጠበቅ የኛ ጉዳይ መሆን የለበትም። ከኛ የሚጠበቀው በቅኝግዛት ባርነት አብረውን ሲማቅቁ ከኖሩ ህዝቦች ጋር መልካም ጉርብትና ትብብር ለመፍጠር መጣር ብቻ ነው።

    ድል ፀረ-ቅኝግዛት ትግል ለሚያካሂዱ የወቦ ሠራዊት!

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.