የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ሁለተኛ ዙር፥ ቁጥር አስራ አራት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ሁለተኛ ዙር፥ ቁጥር አስራ አራት

ብርሃኑ ሁንዴ, Onkoloolessa 28, 2019

Previous: ቁጥር አስራ ሶስት

Bilisummaaዛሬ ማቅረብ ወደፈለኩት ጉዳይ ከመግባቴ በፊት በዚህ በዋንኛው ርዕስ ሳቀርብ የነበረው ፅሁፍ  ከነሃሴ ወር ወዲህ ተቋርጦ ስለነበር አንዳንድ የፅሁፎቼ ተከታታዮች ጠይቀውኝ ነበር። ይህ ቁጥር አስራ አራት ፅሁፍ የቆየበት ምክንያት ከጊዜ ጥበት ወይም እጥረት በመሆኑ አንባቢዎች እንድረዱኝ እፈለጋለሁ። ይህን ካልኩ በኋላ ባሁኑ ጊዜ እየታዩ ያሉትን ጉዳዮች በሚመለከት አንዳንድ ነገሮችን አቀርባለሁ።

ኦሮሞ ነፃ መውጣት ቀርቶ የኦሮሞ ሕዝብና ኦሮምያ እንዲያውም አደጋ ውስጥ ሊገቡ ነው

የለውጥ አየር ኢትዮጵያ ውስጥ መታየት ከጀመርበት ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ሰዎች ኦሮሞ ነፃ ወጥቷል እያሉ ስናገሩ ይሰማሉ። እነዚህ ሰዎች ለምን እንዲህ እንደምሉ የራሳቸው ምክንያት ብኖራቸውም፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ኦሮሞ ነፃ መውጣት ቀርቶ የኦሮሞ ሕዝብና ኦሮሚያ ባሁኑ ጊዜ ትልቅ አደጋ ውስጥ እየገቡ ናቸው። በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ ኦሮሞ እንደ ሕዝብም ሆነ እንደ ብሔር እንደ ዛሬ በግልፅ ተንቆም፣ ተሰድቦም፣ ተዋርዶም አያውቅም። ይህ ሁሉ የሆነው በልጆቹ ደምና አጥንት የተገኘው ድል በሌሎች ኃይሎች በመጠለፉና እነዚህ ኃይሎች ደግሞ የድሉ ባለቤት እንደሆኑ አድርገው ራሳቸውን በማቅረብ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ መቀለዳቸው ነው። ይህ ሁሉ እንዲፈፀም የሚያደርጉት ደግሞ ኦሮሞ ነን ባዮችና በቄሮ መራራ ትግል ከፍተኛ ስልጣንና ሹመት ያገኙ ግለሰቦች ናቸው። ወደ ሚኒልክ ቤተ መንግስት የገቡትም በራሳቸው ችሎታና ጥንካሬ ለዚያ የበቁ አድርገው በመተበት ለዚህ ደረጃ ያበቃቸውን ሕዝብ ጠላት አድርገው ሌሎችን በማስር፣ በመግደል፣ ንብረታቸውን በማውደም ወዘተ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እሮሮ ይፈፅማሉ። የኦሮሞን ጠላቶች ግን ለማስደስት ያማያደርጉት ነገር የለም። ሌት ተቀን ስንከራተቱ ይታያሉ።

ኦሮሞና ኦሮምያ ከምንጊዜም የበለጠ ከፍተኛ ችግር ውስጥ የገቡት፤ ሕዝባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ያዳገተው ኦሮሞ ባለተራ ነው እየተባለ ፕሮፓጋንዳ በሚነዛበት ጊዜ ነው። ኦሮሞ ባለተራ ቢሆን ኖር ከጥያቄዎቹ ውስጥ ቢያንስ አንድ መልስ ማግኘት በቻለ ነበር። የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ መልስ ማግኘቱ ቀርቶ፣ በመራራ ትግል እስካሁን የተገኙት ድሎች እንኳን ልጠፉበት ነው። በኦሮሞ ልጆችና የሌሎች ጭቁን ሕዝቦች ልጆች ደምና አጥንት የተመሰረተው ባሁኑ ጊዜ ያለው የፌዴራል ስርዓት ፈርሶ በሌላ ስርዓት እንዲተካ እየተሰራ ነው። በድሮ ጊዜ ስጨቁኑን እና ስዘርፉን የቆዩት የድሮው ስርዓት ናፋቂ ኃይሎች በኋላ በር ወደ ስልጣን ለመምጣት ዝግጅት እያደረጉ ነው። ታሪክ ይደገማል እንደሚባለው፣ ዛሬም በ21ኛው ክ/ዘመን ኦሮሞ በባርነት ስር እንድወድቅ እየተፍጨረጨሩ ያሉት እኛ ኦሮም ነን የምሉት ከሃዲዎች ናቸው። የፖለቲካ ስልትና እስትራቴጂ ነው እያሉ ኦሮሞን እየዋሹ ይህንን ሕዝብ ወደ ገደል ልወስዱት በብርታት እየሰሩ ነው። ባጠቃላዩ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ሁኔታ ውስጥ ገብተናል።

የኦሮሞ ነፃነት ትግል ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲገባና እንዲጠነክር ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው

እየተሰራ በነበረውና ባለው ተንኮል አልተነቃበትም እንጂ፣ የኦሮሞ ጠላቶችና አጋሪዎቻቸው (Collaborators) የኦሮሞን ነፃነት ትግል ለማዳከም ከተቻለም ለማጥፋት የተለያዩ ተንኮሎችን መስራት ከጀመሩ ቆይተዋል። የኦሮሞ ሕዝብ ጠንካራ ድርጅት ወይም ጠንካራ መሪ እንዳይኖረው ሲስራ የነበረው ተንኮል አሁንም በአዲስ መልክ እንዲቀጥል እየተሰራ ነው። ከነዚህ ተንኮሎችና ሴራዎች ውስጥ አንዱ ኦሮሞን ባይጠቅምም ኢሕአዴግን አፍርሶ ሌላ EPP የሚባል አዲስ ድርጅት ለመመስረት ዝግጅት እየተደረገ ነው። እንደሚታወሰው ኦቦ ጀዋር መሃመድ ይህንን ጉዳይ በሚመለከት አንድ ረጅምና ሰፊ ትንተና ያለበትን ፅሁፍ አቅርቦ ነበር። በዚህ በጀዋር ፅሁፍ የተናደዱትና ያልተደሰቱት ደግሞ በፉከራ ብቻ ተወስነው ሳይቀሩ የጀዋርን ሕይወት ለማጥፋት ሙከራ አድርገዋል። ጀዋር ራሱ እንደተናገረው ምክር እየሰጣቸው ከነሱ ጋር ለመስራት ቢሞክርም፣ እነሱ ግን አሁን ጀዋርን እንደ አንድ ዋንኛ ጠላት እያዩት ሊያጠፉት የምሞክሩ ይመስላል።

ጀዋር አንዳንድ ጊዜ ስህተቶችን ቢሰራም፣ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ስለሚወደድ፣ እንደዚሁም ደግሞ ተሰሚነትና ተቀባይነት ስላለው፣ አሁን በተፈጠረው ክስተት ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብ ከሱ ጎን ቆመዋል። እሱም ይህ የነፃነት ትግል ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር እንዳለበት የተረዳ ይመስላል። ወደዚህ መንገድ የሚመለስ ከሆነ ደግሞ ያለ ምንም ጥርጥር ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ከሱ ጋር ይቆማል። ለኦሮሞ ሕዝብ ብሔራዊ ፍለጎት (Oromo People’s National Interest) ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ከሆነ ጠንካራና አስተማማኝ ኃይል ከጀርባው እንዳለው መረዳት አለበት። ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብም በተለይ ደግሞ ቄሮ ኦሮሞ ከምንጊዜውም በበለጠ ትግሉን አፋፍመው፤ የኦሮሞ ሕዝብ ፍለጎት እንዲሟላ ለማድረግ ጊዜ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኗል።  አሁን ጊዜው ባንድነት የምቆሙበት፤ ከምንጊዜውም በበለጠ የኦሮሞ ኃይል ጠንክሮ ይህንን ትግል ወደ ሌላ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆን አለበት እንጂ አንዱ ለሌላው እንቅፋት የሚሆንበት ጊዜ ማብቃት አለበት። ይህ የነፃነት ትግላችን በአዲስ መልክና ጥራት ወሳኝ ወደ ሆነው ደረጃ መሸጋጋር አለበት።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.