የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሶስት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሶስት

ሁለተኛ ዙር

ብርሃኑ ሁንዴ, Caamsaa 4, 2019

ኦሮማራ

በሁለተኛ ዙር ክፍል ሁለት ፅሁፍ ውስጥ አሁን ያለው የኢትዮጵያ የፌዴራል ስርዓት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝና ይህንን ስርዓት የሚቃወሙት ኃይሎች ራሳቸውን እያደራጁና ኃይላቸውን እያጠናከሩ እንደሚገኙ፤ እንደዚሁም የኦሮሞ ድርጅቶች አቅምና ጉልበት ምን ያህል አስተማማኝ እንደሆነ ለመግለፅ አንዳንድ ነገሮች ቀርበው ነበር። በዚህኛው በክፍል ሶስት ፅሁፍ ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ትግል (ኦነት) ፀር የሆኑት ኃይሎች እየሰሩ ያሉትን ሴራና በኦሮሞ ጎራ (Oromo Camp) ውስጥ እየታየ ያለውን በሚመለከት ያስተዋልኩትን አቀርባለሁ።

የኦነት ፀር የሆኑት ኃይሎች የምጠቀሙበት ስልቶችና ከኦሮሞ ጎራ የሚያገኙት አጋሪነት

የኦሮሞን ጎራ ለማዳከም እንደዚሁም ኦነት እስካሁን ያስመዘገባቸውን ድሎች ለማጥፋት የኦነት ጠላቶች የተለያዩ ስልቶችና እስትራቴጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ በግልፅ እየታየ ያለው ጉዳይ ነው። እነዚህ ኃይሎች በተለያዩ መንገዶች ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ከነዚህ መንገዶች ውስጥ ኣንዱ ሚዲያ ነው። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሚዲያዎችን መያዝ ብቻ ሳይሆን፣ እንዴት በቁርጠኝነትና ሌት ተቀን በትጋት እየሰሩ እንደሆነ ማየትና መረዳት አያዳግትም። በሚዲያቸው በኩል ፕሮፓጋንዳ  በማድረግ በኦሮሞ ላይ በተለይ ደግሞ በኦነት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያደረጉ ነው። ለኦሮሞ ካላቸው ንቀትም አልፈው በግልፅ ኦሮሞን ስሰድቡና ስረግሙ ይስተዋላሉ። ሌሎች የአገሪቷ ሕዝቦች ከኦሮሞ እምነት አንዳይኖራቸው ለማድረግና ለራሳቸው ግን ከነዚህ ሕዝቦች ድጋፍ ለማግኘት የማያደርጉት ሙከራ የለም። ለዚህም ነው ሚዲያዎቻቸውን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀሙ ያሉት። የሚያሳዝነው ግን ከኦሮሞ ውስጥ እነዚህን ፀረ ኦነት የሆኑትን ኃይሎች የሚደግፉ መኖራቸው ነው።

የኦሮሞን የትግል ጎራ በእጅ አዙር ለማዳከም የምጠቀሙበት ሌላው ስልት ኦሮማራ በሚል ስም የሚደረገው ሴራ ነው። እዚህ ላይ እጅግ አጥብቄ አንባቢዎችን ማስገንዘብ የምፍልገው በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች ወይም ብሔሮች መካከል ጥሩ ግንኙነት መኖር የለበትም ማለቴ እንዳልሆነ ነው። በመሰረቱ  የነዚህ የሁለቱ ብሔሮች ወይም ሕዝቦች ግንኙነት ወሳኝ ስለሆነ መደገፍ አለበት። እነዚህ ሁለቱ ሕዝብች በጋራም ሆነ በጎረቤትነት በሰላም አብሮ መኖር ወሳኝ ነው። ይሁን እንጂ በአንድነት ስም ነገር ግን የተደበቀ አጀንዳና ዓላማ ይዘው በኦሮማራ ስም መሄድ ለኦነት ጎጂ ነው እንጂ የሚጠቅም አይመስለኝም። በዚህ ዓይነት  አካሄድ ውስጥ አንዱ ሌላውን ለማስደስት ሲባል ታሪክንና እውነታን የሚቃረን ነገር ስለሚሰራ፣  ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩት ችግሮች እያደጉና እየሰፉ ይሄዳሉ። አንዱ ሌላውን ለማስደስት በምልበት ጊዜ ይህ የሚታየው ከኦሮሞ በኩል ብቻ ነው። ኦሮሞ አማራን ለማስደስት የማያደርገው ነገር የለም። በአማራ በኩል ግን ይህ አይታይም ብል ሀሰት አይሆንም።

ከላይ ያነሳሁትን ጉዳይ እንደ ምሳሌ ለማቅረብ፣ ቅርብ ጊዜ በአምቦ የተደረገውን ማስታወስ በቂ ነው። አማራን ለማስደሰት ተብሎ አስትውሎም ሆነ ሳያስተውል፣ አውቆም ሆነ ሳያውቅ፣ አስቦበትም ሆነ እንደ ድንገት የኦዴፓ የአመራር አባል የሆነ ኦቦ አዲሱ አረጋ የተናገርው በእውነት የኦሮሞን ታሪክ የሚቃረንና ኦነትን የሚያቆሽሽ ነው። ኦነት ለምን እንደተጀመረና ለምንስ እየተካሄደ እንደሆነ ለዘመድም ሆነ ጠላት ግልፅ ነው። በኦሮሞ ላይ የተፈፀመው የእጅና ጡት ቆረጣ አስከፊ ድርጊት ታሪክ ማስረጃ የሚሆንለት እውነታ ነው እንጂ ልበ ወለድ አይደለም። ይህንን አስከፊ ድርጊት በአይናቸው ያዩት ሰዎች ዛሬ አየተናገሩ ያሉት ጉዳይ ነው። ይህ በመሬት ላይ ያለ እውነታ ሆኖ እያለ፣ በፅሁፍ የተቀመጠ ታሪክ የለም፤ ያለው በልበ ወለድ የተፃፈ ነው እያሉ ይህንን እውነታ መካድ በተለይ ደግሞ ከኦሮሞ ውስጥ ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የሚክዱ መገኘታቸው አጅግ አሳዛኝ ነው። አሳፋሪም ነው። ይቅርታ የማይደረግለት ጉዳይ ነው። ለጠላቶቻችን ሞራል የሚሰጠው ከኦሮሞ ውስጥ ይህ መታየት ነው። የራስን ቁስል የሚያውቀው ባለቤቱ ነው እንጂ ሌላው እይታመምለትም።

ይህ ከዚህ በላይ ያነሳሁት ጉዳይ ይባስ ብሎ የኦነት ማእከል በሆነችው አምቦ ከተማ መከሰቱ እጅግ ያሳዝናል፤ ያስቆጣልም። አምቦ የኦነት ማዕከል በመሆኗ የጠላቶች ሴራና ፀረ ኦነት ድርጊት እዚያ መደረግ አልነበረበትም። ሰላምን የሚፈልጉና ለኦሮሞ ማንነት ክብር ያላቸውን ብሔሮችና ብሔረ ሰቦችን ወይንም ሕዝቦችን መጋበዝ የኦሮሞ ባሕልም በመሆኑ ይህ መደገፍ ያለበት ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ በኦሮሞ ልጆች ደምና አጥንት ላይ ቆመው የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ ማቆሸሽ፤ የተደረገውን እንደ ልበ ወለድ ማቅረብ ለኦሮሞ የሚያሳፈር ሲሆን ለጠላቶቻችን ግን ትልቅ ድል ነው። ጉዳዩ ባለቤቱ ቀንዱን የሰበረው በሬ ባዕድ አይኑን ያጠፋል እንደሚባለው ተረት ነው። ይህንን ጉዳይ ያነሳሁት ለፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ጉዳያችን ምን ያህል እንደተናቀና ባዕድን ለማስደሰት ሲባል ያራስን ነገር ለመርሳት ወይም ለመደበቅ መሞከር አሳፋሪ እንደሆነ ላማስገንዘብ ነው።

የኦዴፓ (ODP) አካሄድ ኦነትን ይረዳል ወይንስ ተቃራኒው ነው እየተደርገ ያለው?

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በተለያዩ ፅሁፎች ስግልፅ እንደቆየሁት፣ በድሮው ኦሕዴድ (OPDO) ባሁኑ ኦዴፓ(ODP) ውስጥ ለኦሮሞ ሕዝብ የሚጨነቁ የኦሮሞ ብሔርተኞች ቢኖሩም፣ ፓርቲው ግን እንደ ድርጅት አሁንም የተቋቋመለትን ዓላማ ይዞ እየሰራ ያለ ይመስላል። በወያኔዎች የበላይነት ግዛት ስር በኦሮምያ ወያኔዎችን የወከለ ድርጅት ሆኖ ሲሰራ እንደነበር የማይረሳ ነው። ዛሬም ቢሆን ይህ ድርጅት ስሙን ቀየረ እንጂ ዓላማውንና አካሄዱን ቀይሮ እየሰራ ያለ እይመስልም። የነሱ አካሄድ ባዕድን ለማስደሰት እንጂ በእውነት የኦሮሞን ሕዝብ ወክለው፤ ለዚህ ሕዝብ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጠው እየሰሩ እንዳልሆነ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። ይህ ደግሞ ያለውን እውነታ ለወንድሞቻችን ለመንገር  ነው እንጂ በነሱ ላይ ፕሮፓጋንዳ ለማድረግ አይደለም። ለማንኛውም ይህንን ጉዳይ በሰፊው እመለስበታለሁ።

ተመልሰን እስከምንገናኝ በደህና ቆዩ

2 Comments

 1. Dear Berhanu Hundee,

  Hats off to you! Thank you very much for your relentless efforts to take your time and for attemting to shed light upon the ups and downs in the Oromo struggle for freedom. It is impressing and uplifting to see the efforts a few Oromo intellectuals are making to point out the direction our long march towards greater freedom is taking. Equally, it is not only frustrating and worrying that many of us are still in deep sleep but also devastating . In fact, the majority of us are not ready to wake up, and make the minimum sacrifice required of us; we are even reluctant to occasionally give up our coffee break and read articles pertinent to our affairs, and write two to three lines of comments. Worse, some of us choose to work for the enemies of our struggle for freedom (the majority of OPDO/ODP officials falling under this category). Those who claim to lead our struggle cannot go beyond personal ego and mini rivalries and focus on serving the sacred cause they are entrusted with (some leaders in the OLF factions falling in this category). Consequently, the struggle of our people is suffocated by the curse of mediocrity and exposed to the ambush from our extremely savage enemies. Qeerroo and qaree, who have shown extraordinary political maturity and exceptional unity seem to be held back by the direction the so called reforms by the government of Ethiopia is taking and the ambiguity displayed by political organizations trading in the name of the great Oromo people.

  The attack on our struggle for freedom and the character assassination, aimed at extinguishing the ray of our freedom, is not coming from sudden strength of our inferior enemies. The anti-Oromo lunatic fringes fully understand our immense potential as well as our iron strength. Nevertheless, they are encouraged by the fact that foolish and “galtuu” Oromo individuals are always there to be used as “working donkeys” to damage and/or destroy the Oromo struggle for freedom. Ironically, the anti-Oromo camp which is still rooted in 19th century Ethiopian political thought is more skillful in aggressively sabotaging political organizations claiming to advance Oromo causes. While the Oromo camp is trying to be more civil and accommodating in its approach to Ethiopian political affairs, the anti-Oromo camp is readily using the tactics used by Menilik II in the 19th century. For instance, the cruel attack on innocent civilians in Wollo, north Show, Benishangul Gumuz, etc., by the savage armed militia roaming the Amhara region is a repeat of the Aannolee mutilation and the massacre of Callanqoo, which “Amhara” gangs are capable of carrying out in the 21st century. Are they getting away with it this time around?

  The government of Ethiopia which has opened the door wide for the uncivilized anti-Oromo lunatic fringes seems to be either naïve or carelessly negligent of its duties. The neo Neftegna gangs which have regrouped as ‘Amhara National Movement’ are engaged in inciting violence against the non-Amhara ethnic groups within the Amhara region and beyond, including Finfinne. Their media are awash with disseminating hatred and encouraging ethnic cleansing of others from the Amhara region and the city of Finfinne. Their armed wings are busy carrying out savage attacks on ethnic “others” within Amhara region and cross borders. Both the federal government and the Amhara region government are deaf silent, and are not discharging their duties of protecting citizens. Evidently, since the anti-Oromo lunatic fringes, including those who have self-appointed themselves as “Addis Ababa Caretakers’ Council” aka “Balderas”, have clearly broken the country’s law, the government should have dealt with them in order to maintain law and order.

  Unfortunately, it seems that there is a confusion in understanding the notions of democracy and free expression within the Ethiopian government and among the Ethiopian peoples. Both democracy and right to free expression come with rights and responsibilities. The late Ethiopian dictator, Melee Zenawi, once claimed that ” the Ethiopian populace were not ready for democracy, and he was hoping to teach them gradually “. Although the dictator, who was an anti-Oromo himself and inflicted untold sufferings on our people, is not the subject of my comment here, I feel that his remarks have some truth if he was referring to the Abyssinian side of the Ethiopian population. Particularly, the anti-Oromo lunatic fringes and their donkey counterparts, who are toiling to fulfill the wishes and interests of the enemies of our people, fit Zenawi’s remarks perfectly. Whether one is preoccupied by filling his/her belly, picking leftovers from the resources robbed from us, or whether one is extremely naïve to the extent of hurting his/her own people, by willingly serving enemies, the great Oromo people must separate the ” wheat from chaff” before it is too late.

  Oromo, qeerroo and qaree, you have come long way to take our struggle for freedom to where it is now. You showed great maturity and asserted that you are superior to our extremely backward enemies. On approaching victory you decided to give the reform team emerged within EPRDF chances to address your fundamental questions. You have been awaiting patiently even though none of your questions are answered and none of your demands are met. I hope that your generosity to the the reform team in particular and other Ethiopians in general is noted by those who are committed to peaceful coexistence of the country’s peoples. The anti-Oromo lunatic fringes and their media outlets seem to have mistaken your civilised gestures and are determined to remain your number one enemy. Take note of the savage armed militia roaming Amhara region and pay careful attention to the gangs meddling with Finfinne affairs. Never go back to sleep. Keep your unity and prepare for self-defense in the event of imminent attack from the militia of Amhara region. The Ethiopian government and Oromia regional government do not seem willing or capable of dealing with the anti-Oromo fascism taking root in Amhara region and Finfinne. Do not get me wrong; I am related to the Amhara people to the extent that most of my relatives got intermarried with the decent people of Amhara and endowed me with beloved cousins, nephews and nieces. I love them and I have no grudge against the Amhara as people. The point here, is that there are anti-Oromo lunatic fringes, gangs and media outlets working day and night to destroy the great Oromo people as a nation. ‘In politics, being deceived is no excuse’.

  Qeerroo and qaree maintain your momentum and ascertain the safety and freedom of your people. Your own destiny and the future of your people is in your hands. The sky is not the limit to what the great Oromo people is poised to achieve, of course, if they understand their immense potential and use it to achieve their big objectives, freedom and abbabiyuumma. Take responsibility to make alliances with the peoples of Ethiopia who are committed to peaceful coexistence and creating a new Ethiopia, which will be mother to all her children.

  OA

 2. Maqaa baleesuun, sobbun, jeequu fi sodda ummun ,akkasummas immoo siyaasa oli antumma offuun malatoo ” Colonial politics ” ittii. Kana beekun kutanoon haala qabatamma jiru irraa ittii hundauun qabsoo Bilisumma keenya ittii fuufun, hummnootaa Bilisumma fi demokrassii barbadanii wajjini harrirro dhabachuun hojeechun murteesadhaa. Yeero ammaa kana wari farraa Bilisumma taan jeequmsaa fi sodaa ummun karaa Bilisumma fi demokraassi irraa gufachiisuuf halkaniif guyyaa hojeecha jiruu. “issue” addaa addaa ummun saba abdii kutachisuuf hojeetu. Kana dura dhabachu fi karroraan “Stratagy and tactics” adeemuun murteesadhaa. “Provocation and deffamation” dinnaa irraa annuuf damaqinssaan haala qabatamma saba keessa jiru irra ittii hundauun karroora yoo hojeenne ni moonnaa.
  Bilisumma fi demokrassiin haa laliissaan.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.