የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?  ሁለተኛ ዙር፥ ቁጥር ስምንት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?  ሁለተኛ ዙር፥ ቁጥር ስምንት

ብርሃኑ ሁንዴ, Adooleessa 4, 2019

Bilisummaaበሁለተኛ ዙር ቁጥር ሰባት ፅሁፍ ውስጥ የተሞከረውን መፈንቅለ መንግስት በሚመለከት ኣንዳንድ ነገሮችን አቅርቤ ነበር። በዚህኛው ቁጥር ስምንት ፅሁፍ ውስጥም ከዚያው ከተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ጋር የሚገናኝ አንዳንድ ጉዳዮችን አቀርባለሁ።

ከተሞከረው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ምንድነው ሊሆን የሚችለው?

ከተሞከረው የመፈንቅለ መንግስት በኋላ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ በኦነት ላይ ሊያመጣ የሚችለው ጫና ምን መሆን እንደሚችል ኣንዳንድ የሚታዩኝን ነገሮች ለመግለፅ እሞክራለሁ። እንደሚሰማውና እንደሚታየው መንግስት አንዳንድ እርምጃዎችን እየወሰደ ያለ ሲሆን፣ ትኩረት ውስጥ ያስገባው ደግሞ በቅድሚያ የአማራ ክልል እንደሆነ ነው የማስበው። በዚህ ክልል ውስጥ የተለያዩ ችግሮችን ስፈጥሩ የነበሩና ያሉት ወይንም ደግሞ ወደፊት ሌሎች ችግሮችን ልፈጥሩ የሚችሉ የአማራን ብሔርተኝነት የምያንፀባርቁ ኃይሎች ናቸው። ስለዚህ መንግስት እነዚህን ኃይሎች ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰዱ የማይቀር ይሆናል። ቀድሞውኑ ይህ መንግስት ብሔርተኝነት ለአገሪቷ አንድነት አስጊ ነው እያለ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስገልፅ እንደነበር የሚታወስ ነው። በተለይም የኦሮሞ ብሔርተኝነት አስጊ እንደሚሆን የመንግስት መሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ስገልፁ ነበር።

ይሁን እንጂ የትኛው ብሔርተኝነት (ማለትም የኦሮሞ ብሔርተኝነት ወይንስ የአማራ ብሔርተኝነት) ለዚህች አገር ችግር ይሆናል? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊ ይሆናል። ለዚህ ጥያቄ በቀጥታ መልስ ከመስጠት በፊት ግን የነዚህን ሁለቱ ብሔርተኝነት ልዩነት ማየት አስፈላጊ ይሆናል።

በኦሮሞ ብሔርተኝነትና በአማራ ብሔርተኝነት መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

የኦሮሞን ብሔርተኝነትና የአማራን ብሔርተኝነት ካወዳደርን፣ በመካከላቸው ያሉት ልዩነቶች ከዚህ በታች እንደተዘረዘሩት ሊገለፁ ይችላሉ።

 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት ካገኘው እውቅና አንፃር ሲታይ በዕድሜም ሆነ በብስለት ከአማራ ብሔርተኝነት ይበልጣል
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት በኢምፓየሯ የጭቆና ስርዓት ውስጥ የተፈጠረ፤ በዚህ ስርዓት ውስጥ የተለያዩ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ያደገና አብቦ ዛሬ የደረስበት ደርጃ ላይ የሚገኝ ጠንካራ ብሔርተኝነት ነው
 • የአማራ ብሔርተኝነት ግን በጨቋኙ የእምፓየር ስርዓት ውስጥ ተደብቆ የቆየና ነገር ግን በድብቅ በኢትዮጲያ ብሔርተኝነት ሽፋን የአማራን የበላይነት ለማስፋፋት እንደ ቁልፍ ያገለገለ ነው
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት ፍላጎትና ዓላማ የኦሮሞን ሕዝብ ከጭቆና ስር ለማውጣትና የዚህ ሕዝብ መብት አንዲጠበቅ ለማስቻል ነው
 • የአማራ ብሔርተኝነት ፍላጎትና ዓላማ ግን የአማራን ሕዝብ መብት ለማስጠበቅ ነው ይባል እንጂ፣ የተደበቀ ዓላማው የአማራን የበላይነት መልሶ በሕዝቦች ላይ ለመጫን ነው
 • የአማራ ብሔርተኝነት ከአማራ ወሰን አልፎ በሌሎች ላይ ጉዳት ለማስከተል ተብሎ የተፈጠረ ነው እንጂ የአማራ ብሔርተኞች እንደምሉት የሕዝባቸውን ፍለጎት ለማስጠበቅ አይደለም
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት የኦሮሞ ሕዝብ መብት እንዲጠበቅ ለማስቻል እንጂ ከኦሮሚያ ወሰን አልፎ ሌሎችን የመጉዳት ዓላም የለውም።
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት በብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት ያምናል። በተቃራኒው የአማራ ብሔርተኝነት በእኩልነት ሳይሆን የአማራ የበላይነት እንዲረጋገጥ ይፈልጋል
 • የአማራ ብሔርተኝነት ያረጀውንና የበሰበሰውን የድሮ ስርዓት ያሞግሳል ወይንም ያ ስርዓት ተመልሶ በሕዝቦች ላይ እንዲጫን ይፈልጋል ስለዚህም አሁን ያለውን የፈዴራሊዝም ስርዓት ይቃወማል
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት አሁን ላለው የፌዴራል ስርዓት መሰረቱ ነው፤ ይህ ስርዓት በይበልጥ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲሻሻል ይረዳል። ይህ ደግሞ አንስተኛው ዓላማው ነው
 • የአማራ ብሔርተኝነት የዚህችን አገር አንድነት ይሰብካል እንጂ ለአገሪቷ አንድነት አደጋ እንደሆነ ብዙ የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ። ለምን ከተባለ፣ ይህ ብሔርተኝነት የብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲረጋግጥ አይፈልግምና
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት ግን ሌሎች ስሙን እንደምያጠፉት ሳይሆን፣ የብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲከበር ያስችላል እንጂ ይህችን አገር ለማፍረስ ዓላማም ሆነ ፍላጎት የለውም። በሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ግን ያምናል
 • የኦሮሞ ብሔርተኝነት በአገሪቷ እየታየ ላለው ለውጥ ሞተሩ ነው። የአማራ ብሔርተኝነት ግን ይህንን ለውጥ ለመቀልበስ ተብሎ የተፈጠረ ነው

እንግዲህ እያወቅን እውነታውን መቀበል ካልፈለግን በስተቀር ካዚህ በላይ በተዘረዘሩት ነጥቦች ላይ ተመርኩዘን ካየን፣ የትኛው ብሔርተኝነት ለዚህ መንግስትም ሆነ ለአገሪቷ አንድነት አደጋ እንደሚሆን መገንዘብ የሚያዳገት አይመስለኝም።

ይሁን እንጂ መንግስት ይህንን እውነታ ተገንዝቦና ኣምኖ ይወስዳል ወይንስ ሁለቱንም ብሔርተኝነት ባንድ አይን አይቶ በሁለቱም ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ይወስድ ይሆን? የሁለቱም ቡድን ብሔርተኞች ለዚህ መንግስት ጠላቶች ናቸው ተብለው ይወሰዳል? እነዚህን ጥያቄዎች ያነሳሁበት ምክንያት መፈንቅለ መንግስቱ ከከሸፈ በኋላ መንግስት አንዳንድ የጠነከሩ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ስለምገምት ነው። ይህም በአማራ ክልል ውስጥ ታጥቀው ሌሎች ሕዝቦችን ለመጉዳት ተደራጅተው ያሉትን ኃይሎችና በኦሮሚያ ውስጥ ለፍትህና ነፃነት የሚታገሉትን ኃይሎች ሁሉንም እንደ ጠላት በማየት እጅግ በጠነከረ መልክ ሊዘምትባቸው እንድሚችል ስለታየኝ ነው። ምን ሊፈጠር እንደሚችል የምናየው ቢሆንም፣ ነገር ግን የታጠቀው ኃይል ሁሉ ጠላቴ ነው ብሎ ለፍትህ፣ ዲሞክራሲና ነፃነት የምንቀሳቀሱትንና የአንድን ብሔር የበላይነት ለማረጋገጥ የሚንቀሳቀሱትን ባንድ አይን ማየት ስህተት ነው ብዬ አምናለሁ።

የኦሮሚያን ጉዳይ በተመለከተ ለቤታችን ችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማግኘት በሰላማዊ መንገድ በውይይት መሆን ለሁሉም ይጠቅማል እንጂ አንዱ ሌላውን በጉልበትና በጠመንጃ ለማጥፋት መሞከር የመጨረሻ መፍትሄ አያስገኝም። ለፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ የሚደረገው ትግል ይቆይ ወይም ይራዘም ይሆናል እንጂ ግብ መምታቱ የማይቀር ነው። የኦሮሞ የነፃነት ትግልም (ኦነት)ም ከዚህ እውነታ የተለየ አይሆንም። በስተመጨረሻ እውነት ብቻ ነው የሚያሸንፈው።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ በደህና ቆዩ

1 Comment

 1. ምከረው ምከረው ደግመህም ምከረው
  ኢምቢ ካለማ ታሪክ ያስተምረው
  ነፍጠኛ በያዘው ነፍጡ ይውገረው።

  ፊት አትስጥ ለነፍጠኛ
  ይገላፈተሃል እንደመጋኛ።

  ያልጠረጠረ ቀስበቀስ ተመነጠረ
  ነፍጠኛን ያቀፈ ከሕዝቡ ተቆራረጠ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.