የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ አራት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

– ትላንት የነበሩት፣ ዛሬ ያሉትና ወደፊት የሚኖሩት ፈተናዎች –

ብርሃኑ ሁንዴ , Caamsaa 11, 2018                                           

Abiy Ahmed basaastoota Weyyaanee gurguddoo fi gooftoolii isaa wajjin yeroo Sagalee Qeerroo Bilisummaa Oromoo basaasu ilaali kanaaf bakka tana taa’e gurbaan hubadhu yaa burjaajaa’a

ክፍል አስራ አራት

በዛሬው ፅሁፌ ውስጥ ሀሳቤን ለማቅረብ ወደፈለኩት ጉዳይ ከመግባቴ በፊት፣ ሚድሮክ ( MIDROC)ን በተመለከተ አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። የለገ ደምቢ ጉዳይ ከአዲስ አበባው (ፊንፊኔ) ማስተር ፕላን የተለየ አይሆንም ቢባል ነገር ማጋነን የሚሆን አይመስለኝም። የሁለቱም ዕቅዶች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዘመቻ ማወጅና በተለያዩ መንገዶች የዚህን ሕዝብ ማንነትና ዘር ለማጥፋት ነው። በነዚህ ጉዳዮች ላይ በተገኘው ድል በኩልም ከታየ፣ ሕዝባችን የጠላቶቹን እጅ በመጠምዘዝ ሁለቱንም ዕቅዶች ማስቆም ችሏል። ለዚህ ሁሉ ድል ምስጋናው ለሕዝባችን በተለይም ደግሞ እነዚህን የማንነት ማጥፊያ ዕቅዶችን ለማስቆም ከፍተኛ ማስዋዕትነት ለከፈሉት ጀግኖቻችን ይሁን። ከዚህ መረዳት የሚቻለው ደግሞ ኦሮሞ የፈለገውን ለማግኘት ጉልበትም፣ አቅምም፣ ችሎታም፣ እውቀትም፣ ሃብትና አንድነትም እንዳለው ነው።

የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ ጠንክሮ መቀጠል አለበት  

በኦሮሞ አነጋገር ወይም ተረት ውስጥ አንድ አባባል አለ። ይሀውም፥ “ሊነጋጋ ሲል ጨለማው በጣም ይጠነክራል” ይባላል። የኦሮሞ የነፃነት ትግልም  ከዚህ ጋር ይመሳሰላል። እንዴት ቢባል፣ ይህ ትግል በየትኛውም መልክ ይሁን ከግብ ለመድረስ እየተቃረበ ነው። ይሁን እንጂ ልክ እንደ ተረቱ ይህ ትግልም ወደ ግቡ እየተቃረበ በሄደ ቁጥር የሚከፈለው መስዋዕትነትም ከድሮው የባሰ እየጨመረ ይሄዳል ማለት ነው። ለዚህም ነው ጠላትም ከምንጊዜውም በበለጠ ኃይሉን አቀናጅቶና አጠናክሮ በመላው ኦሮሚያ በተለያዩ መንገዶች ሕዝባችንን እየጎዳ ያለው። የመጨረሻው ድል ግን የፍትህና ነፃነት ትግል በመሆኑ፣ ኦነትም ጠላትን አሸንፎ፣ ባርነትንና ጭቆናን ደምስሶ የተፈለገውን ግብ እንደሚደርስ ምንም ጥርጥር የለውም።

የኦሮሞ የአገር ባለቤትነትን ማረጋገጥ ማለት ምን ማላት ነው?

ብዙ ጊዜ ይህ ጉዳይ ሲነሳ ኦሮሞ አገሩን ለመግንጠል ወይም ከኢትዮጵያ ለመገንጠል እንዳሰበ ተደርጎ ይወሰዳል ወይም ይታያል። ይህ አወሳሰድ ግን ስህተት ነው። ኦሮሞ ከየትም አይግነጠልም። የትም አይሄድም። ድሮም እዚያው መሬቱ ላይ ነበር፣ ዛሬም ነገም እዚያው ይኖራል። ይሁን እንጂ ጠላት አገሩን ወሮ፤ የኦሮሞ ሕዝብ በገዳ ስርዓቱ ስር የነበረውን ነፃነቱንና አገሩን አጥቶ፤ ባዕድ የኦሮሞ መሬትና ንብረት ባለቤት ሆኖ፤ ባንድ በኩል የኦሮሞን ንብረት እየዘረፉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮሞን በገዛ መሬቱና አገሩ ላይ እያሰሩ፣ እያሰቃዩ፣ እየገደሉ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ለበሽታ፣ ለረሃብና እርዛት እንዲጋለጥ እያደረጉ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ከሰው በታች ኑሮ እንዲኖር አድርገውት እስከ ዛሬ ስለደረሱ፣ ይህንን ጨቋኝ ስርዓት አስወግዶ፣ ከነመሰረቱ ነቅሎ፣ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ማስቻል ነው።

የጨቋኝ ስርዓትን ነቅሎ ነፃነቱን የተጎናፀፈ ቀን ደግሞ፣ ያጣውን በሙሉ መልሶ ስለሚያገኝ፤ የአገሩና የንብረቱ ባለቤት ስለሚሆን፣ የአገሩ ባለቤትነት ተረጋገጠ ማለት ነው። የወደፊት የአገር ግንባታን በተመለከተ ደግሞ፣ እንዴትና ከማን ጋር መኖር እንደሚፈልግ፤ ምን ዓይነት አገርና መንግስት መመስረት እንድሚፈልግም የሚወስነው የኦሮሞ ሕዝብ ነው። እንደ እውነተኛ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ውስጥ መኖርም ሆነ፣ የራሱ ነፃ መንግስትና ነፃ አገር ለመመስረት የመጨረሻ ውሳኔ የሚኖረው የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ነው ማለት ነው። ይህ ሁኔታ ባልተፈጠረበትና የሕዝቡ ውሳኔ ምን መሆን እንድሚችል ሳይታወቅ ከወዲሁ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት ጥያቄን እንደ መገንጠል ማየት ወይም መተርጎም ትክክል አይደለም።

የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት በኦሕዲድ/ኢሕአዲግ ውስጥ በሚደረጉት ለውጦች ሊረጋገጥ ይችላል?

ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የግድ ጥናትና ጥልቅ ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም። ካለው ሁኔታና ከድርጅቶቹ ታሪክ በመነሳት ብቻ የዚህ ጥያቄ አጭር መልስ “አይቻልም” የሚል ይሆናል። እዚህ ላይ ለምንድነው የማይቻለው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል። የዚህን ምክንያት ባጫጭሩ ለማብራራት እሞክራለሁ።

  • ኢሕአዲግ ባጠቃላይ የኦሮሞ ጠላት እንጂ ወዳጅ አይደለም። ሲፈራረቁ በነበሩት የሀበሾች መንግስታት ስር ኦሮሞ ተመሳሳይ ጭቆናና ስቃይ ቢደርስበትም፣ በኢሕአዲግ መንግስት ስር ግን ከምን ጊዜውም የበለጠ ስቃይና መከራ እየደረሰበት ነው ያለው። ስለዚህ ከጠላት ምንም ስለማይጠበቅ፣ እንኳንስ የአገር ባለቤትነት መረጋገጥ ቀርቶ፣ በዚህ ድርጅት ስር የኦሮሞ ሕልውናም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።
  • ዛሬ የለውጥ ሞተር አድርጎ ራሱን የሚያየው ኦሕዲድም ራሱ ከእንቅልፉ እንዲነቃ ያደረገው የኦሮሞ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነው። ይህ በመሆኑ የኦሮሞን ሕዝብ ማመስገንን ትተው፣ እንደ ልማዳቸው ዛሬም ሕዝብን መዋሸትና ማታለል ሲሞክሩ ይታያሉ። የኦሮሞ ሕዝብ ዝም ብሎ ጊዜ ሲሰጣቸው፣ ልክ ሕዝቡን እንዳረጋጉት በማየት ያው የተለመደውን ፀባያቸውን ለማሳየት ይፈልጋሉ። መስራቾቻቸውን ለማገልገል የተለመደ ስራቸውን ይሰራሉ። ሕዝቡ ከተነሳባቸው ደግሞ የሚይዙትንና የሚለቁትን ስለሚያጡ፣ ሕዝብን ያባብላሉ። የኛ ጌታ ሕዝባችን ብቻ ነው እያሉ አሁንም ሕዝብን ለማታለል ይሞክራሉ። ባጠቃላይ ራሳቸውን ችለው በሁለት እግሮቻቸው መቆም ኣልቻሉም። ይህ ለራሱ መቆም ያልቻለ ድርጅት ደግሞ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት እንዲረጋገጥ በጭራሽ ማድረግ አይችልም።
  • ኦሕዲድ ለኦሮሞ ሕዝብ የቆመ አስመስሎ ነገር ግን ይህንን ሕዝብ ለጠላት እያጋለጠ ነው። ይህ ድርጅት በቦታው ባይኖር ወያኔ ኦሮሚያ ውስጥ እንደ ፈለግች ዞራ ሕዝባችንን ማሰቃየትና መግደል ባልቻለች ነበር። ስለዚህ ስር ነቀል ለውጥ አምጥተው የኦሮሞን ጥያቄ መመለስ ቀርቶ የዚህን ሕዝብ ሰላምና ደህንነት እንኳን ማስጠበቅ ያልቻለ ድርጅት ነው። ለሕዝብ የሚቆረቆሩ የኦሮሞ በሔርተኞች በዚህ ድርጅት ውስጥ ቢታዩም፣ ኦሕዲድ ግን እንደ ድርጅት አሁንም የተቋቋመለትን ተልዕኮ እየፈፀመ ነው ያለው።.
  • ከዚህ ደርጅት ውስጥ የወጣ ጠ/ሚኒስተር አራት ኪሎ ስለገባ፣ በዚህና በለውጥ ስም እየነገዱ፣ በእጅ ኣዙር ግን ከበስተጀርባቸው ተደብቃና ኣድፍጣ ተንኮል እየሰራች ያለችውን ወያኔ እያበረታቱና እፎይታ እንዲታገኝ እያደርጉ ናቸው እንጂ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ፍላጎትም ሆነ ጉልበት የላቸውም። በተጨማሪ ደግም ለራሳቸው ለግል ጥቅማቸው ብለው በዚህ ስርዓት ውስጥ ተሰግስገው ከጠላት ጋር የሚሰሩ በዚህ ድርጅት ውስጥ ብዙ ናቸው።
  • ለውጥ ለማምጣት የሚጥሩ እንኳን ቢሆን፣ እንሱ ሊያመጡ የሚፈልጉት ለውጥ ይህንን የበሰበሰውን የወያኔ ስርዓት ጠጋግነው በሕዝብ ላይ ለማቆየት ካልሆነ በስተቀር በነዚህ ድርጅቶች ስርና በዚህ ስርዓት ውስጥ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት በፍፁም ሊረጋገጥ አይችልም። ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ስፅፍ እንደቆየሁት፣ ኦሕዲድ ለኦሮሞ የነፃነት ትግል አጋር ከመሆን ይልቅ እንቅፋት እንደሚሆንበት ይህ እውነታ ግልፅ መሆን አለበት።

እንግዲህ፣ የኦሮሞን የአገር ባለቤትነት ማረጋገጥ ቀርቶ በነዚህ ድርጅቶች ስር ይህንን ሰው በላ ስርዓት በመጠጋገን አንዳንድ ጥቃቅን ለውጦች እንኳን መመጣት አንደማይችሉ አንዳንድ ምሳሌዎችን በመጠቃቀስ ለማብራራት ሞክሬአለሁ። ስር ሰዶ እስከዛሬ የደረሰውን የጭቆና ስርዓት አጥፍቶ የኦሮሞን የአገር ባለቤትነት ማረጋገጥ የሚችለውና ዋስትና ሊኖረው የሚችል ይህንን የነፃነት ትግል አጠንክሮ በመቀጠል፤ ኦሮሞ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን ማስቻል ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ሌላ መንገድም ሆነ መፍትሄ ወይም አማራጭ ያለ አይመስለኝም።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ።

13. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ ሦስት
12. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?  ክፍል አስራ ሁለት
11. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ አንድ
10. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስር
9. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ዘጠኝ
8. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስምንት
7. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሰባት
6. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስድስት
5. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አምስት
4. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አራት
3. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሦስት
2. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሁለት
1. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አንድ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.