የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ ስድስት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

– ትላንት የነበሩት፣ ዛሬ ያሉትና ወደፊት የሚኖሩት ፈተናዎች –

ብርሃኑ ሁንዴ , Caamsaa 18, 2018 

ክፍል አስራ ስድስት

እንደምታወቀው የኦሮምኛ ቋንቋ (Afaan Oromoo) የኦሮሙማ (Oromummaa) ሶስት ምሰሶዎች ከሆኑት (የኦሮሞ ቋንቋ፣ የኦሮሞ ታሪክና የኦሮሞ ባህል) ውስጥ ኣንዱና አንጋፋው ነው። የኦሮሞ የነፃነት ትግል ካስመዘገባቸው ድሎች ውስጥ ኣንዱና ዋንኛው ደግሞ የኦሮምኛ ቋንቋ ፊደላት Qubee Afaan Oromoo ናቸው። ቁቤ የማንነታችን ምልክት ናት ማላት ይቻላል። ጠላትን እያንበረከከ ያለው አዲሱ ትውልድ እንኳን የሚጠራው በዚህ ፊደል ነው። ቁቤ የነፃነት ምልክት ናት ከተባለ ሀሰት አይሆንም። በዚህ ምክንያት ቁቤ ለጠላቶቻችን የራስ ምታት ሆናባቸው፤ እሷን አጥፍቷት፣ በሳብያን ወይም ግዕዝ ፊደላት ለመተካት ይመኛሉ። የሳብያን ወይም ግዕዝ ፊደላት ኦሮምኛን ለመፃፍ እንደማይመቹ ሲነገራቸው፣ ይህንን እውነታ አምነው አይቀበሉም። ይሁን እንጂ እነሱ ተቀበሉትም ኣልተቀበሉት፣ ለኛ የሚሆነውን እኛው ራሳችን ነው የምንወስነው እንጂ ሌላው ለኛ ለመወሰን መብት የለውም። ስለዚህ ይህንን የማንነታችን መገለጫ የሆነውን መጠበቅና ማሳደግ የኦሮሙማ ግዴታ ነው።

የኦሮምኛ ቋንቋ ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ ኣንድ ቋንቋ ማደግ እንደሚኖርበት ኣድጏል?

እንደ ርዕስ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከመሞከሬ በፊት፣ በዚህኛው ክፍል ፅሁፌ ውስጥ የኦሮምኛ ቋንቋን ጉዳይ ያነሳሁበት የተለያዩ ምክንያቶች ኣሉኝ። በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳተኩር ያደረገኝ ደግሞ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ” የሚል አንድ ምልክት (logo) በፌስ ቡክ ላይ እንደ አጋጣሚ በማየቴ ነው። ይህ ምልክት የመጀመሪያ ወይንም የመጨረሻ ንድፍ ይሁን የማውቀው ነገር የለኝም። ያም ሆነ ይህ ጉዳዩ ሳበኝና ይህንን ፅሁፍ እንዳቀርብ ኣነሳሳኝ። ባሁኑ ወቅት ብዙ ትልልቅ ችግሮች እያሉን፣ ይህንን ጉዳይ እንደ ትልቅ ነገር ኣድርጌ በማየት ነገር ለማጋነንም አይደለም። ይሁን እንጂ ኣንድ ነገር ትንሽ ነው ብለን ዝም ብለን የምናልፈው ከሆነ፣ ቆይቶ ግን ትልቅ ችግር ሆኖ ሊመጣ ይችላል። ለዚህ ነው ይህንን ጉዳይ ከአፋን ኦሮሞ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የፈለኩት። ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ወደ ኋላ ላይ እመለስበታለሁ።

አሁን ወደ ርዕሱ ጥያቄ ለመመለስ፣ የኦሮምኛ ቋንቋ ዛሬ ያለበት ደረጃ የሚያስደስትና የሚያኮራ ቢሆንም፣ ይህ ቋንቋ በ27 ዓመታት ውስጥ ማደግ እንደሚኖርበት ያደገ አይመስለኝም። እውነት ነው በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የስራ ቋንቋና የትምህርት ቋንቋ መሆን ችሏል። ይሁን እንጂ በተለያየ መንገድ ከታየ፣ በዚህ ቋንቋ ላይ ተፅዕኖ አንዳለ ለመረዳት አያዳግትም። ኣንደኛ  የባዕድ ተፅዕኖ ኣለ። ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት፣ ኦሮምኛ የኦሮሞ ማንነት እና ቁቤ አፋን ኦሮሞ ደግሞ የነፃነት ምልክት በመሆናቸው፣ እነዚህ ባዕድና ጠላትን አያስደስቱም። ስለዚህ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በድብቅም ሆነ በግልፅ በዚህ ቋንቋ ላይ ተንኮልና ደባ ይሰራል። ሁለተኛ  እውነት እንናገር ከተባለ፣ ይህ ቋንቋ ዛሬ ባለቤት የለውም። ይህን ስል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እውነት ይህንን ቋንቋ ለማሳደግ በፅኑ የሰራበት ወይም የሚሰራበት አይመስለኝም።

የማንነታችን መገለጫ የሆነችውን ቁቤ አፋን ኦሮሞን እንኳን ለማበላሸት ምን ሲሰራ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የቁቤን ቅደም ተከተል እንቀይራለን ሲሉ እንደነበርና ግን ከባድ ተቃውሞ ስለገጠማቸው ይህንን ስራቸውን ለማቆም እንደተገደዱ የሚታወስ ነው። ይህ የሚያሳየው ደግሞ ለዚህ ቋንቋ ምንም ደንታ እንደ ሌላቸው ያሳያል። ይህ ቋንቋ በደንብ እንዲያድግ ብፈልጉ ኖሮ በቂ በጀት ተመድቦለት ለቋንቋው እድገት ብዙ መስራት በተቻለ ነበር። ይህን ማድረግ ቀርቶ ይህ ቋንቋ አሁን የደረሰበትን ደረጃ ለመጠበቅ ጥረት ያደረጉ አይመስሉም። ይህ ቋንቋ ባንዳንድ ቦታዎች በጋዛ አገሩ በኦሮሚያ እንዲረሳ ተደርጏል። ለዚህ ኣንዳንድ ምሳሌዎችን ወደ ኋላ ላይ ለማንሳት እሞክራለሁ። ባጠቃላዩ ሲታይ፣ የኦሮምኛ ቋንቋ ማደግ እንደሚኖርበት ማደግ ኣልቻለም። 27 ዓመታት ረዥም ነው። ለጋብቻም ደርሶ ያለፈ የኣንድ ወጣት ዕድሜ ነው። ቋንቋው  ግን አሁንም ህፃን ነው ማለት ይቻላል።

የኦሮምኛ ቋንቋ በአገሩ በኦሮሚያ ከሌሎች ቋንቋዎች ቅድሚያ ማግኘት ኣለበት  

የኦሮምኛ ቋንቋ የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን ብዙ ጊዜ ይነሳል። ይህ ደግሞ የሁሉም ኦሮሞ ምኞትና ፍላጎት ነው ቢባል ሀሰት አይሆንም። ይሁን እንጂ ይህ ምኞትና ፍላጎት እንዲሁም ዓላማ እንዳለ ሆኖ፤ ኣንድ መረሳት የሌለበት ጉዳይ አፋን ኦሮሞ በገዛ አገሩ በኦሮሚያ ውስጥ እንኳን የአገሩ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ሙሉ በሙሉ መታየት ኣልቻለም። በኦሮሚያ የክልሉ የመንግስት የስራ ቋንቋ ይሁን እንጂ በሁሉም ቢሮዎች ውስጥ ይህ ቋንቋ የበላይነት ኣለው? የተለያዩ ቢሮዎችና ተቋማት በዚህ ቋንቋ በደንብ እየሰሩ ነው ያሉት? የቋንቋውስ ጥራት እየተጠበቀ ነው? የንግድ መስርያ ቤቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ የምግብና መጠጥ ቤቶች፣ መዝናኛ ቦታዎችና የመሳሰሉት ስማቸው በዚህ ቋንቋ ተፅፈው ይገኛሉ? ተፅፈው ከሆነ ደግሞ በስርዓት ተፅፈዋል?

ለምሳሌ ያህል የትምህርት ተቋማትን ብንወስድ፣ በኦሮሚያ የሚገኙ ዩኒቭርሲቲዎች ስማቸው በኦሮምኛ የተፃፉት በጣም ጥቂት ናቸው። እስቲ ኣንዳንድ ምሳሌ ለመጥቀስ እሞክራለሁ። ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ በተረፈ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በሙሉ ስማቸው በባዕድ ቋንቋ የተፃፉ ናቸው። በብዛት ስማቸው የተፃፈው በአማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች ሲሆን፣ ኣልፎ ኣልፎ በኦሮምኛ ቢታይም በጣም ተደብቆ ነው። ይህ ለምን ሆነ? በኦሮምኛ መጠቀም የዝቅተኝነት ምልክት ሆኖ ነው ወይንስ ለቋንቋው ካላቸው ንቀት የተነሳ ነው? ይህን ቋንቋ መደበቅ ማለት የኦሮሞን ማንነት መደበቅ ማለት እኮ ነው!! ማንነታችን ደግሞ በገዛ አገራችን ይደበቃል? ይህ ጉዳይ ቀላል ሊመስል ይችል ይሆናል እንጂ ትልቅ ችግር ነው። ስለዚህ ትክረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

በስተመጨረሻ፣ የቋንቋችን ማደግ የህብረተ ሰባችን ማደግ ነው፤ የአገራችንና የብሔራችን ዕድገት ነው። ይህንን ቋንቋ ለማሳደግ የሚደረገው ትግል የኦሮሞ የነፃነት ትግል አካል በመሆኑ፣ በዚህ ላይ ጠንክሮ መስራት የኦሮሙማ ግዴታ ነው። አፋን ኦሮሞ የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን ከመመኘት በፊት፣ እስቲ በጋዛ አገሩ በኦሮሚያ ትልቅ ትኩረት ያግኝ። መስተካከል ያለባችው ነገሮች ይስተካከሉ። ቋንቋችን በኦሮሚያ ከሁሉ ቅድሚያ ኣግኝቶ፣ የሚገባውን ቦታ እንዲይዝ ማድረግ የግድ ይሆናል። ቋንቋችን የሚደበቅበት ጊዜ ኣልፏል። የንግድ መስርያ ቤቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ የምግብና መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ ቦታዎች፣ ማንኛውም በኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ ተቋማት እና የመሳሰሉት ሁሉ ስማቸው በዚህ ቋንቋ መፃፍና መስራትም ኣለባቸው። በኦሮሚያ ቢሮዎች ውስጥ የዚህ ቋንቋ ጥራትና ደረጃ ተጠብቆ መሰራት ኣለበት። ቋንቋችንን የምናሳንስበትና የምንደብቅበት ጊዜ ማብቃት ኣለበት።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ።

15. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?ክፍል አስራ አምስት
14. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ አራት
13. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ ሦስት
12. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?  ክፍል አስራ ሁለት
11. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስራ አንድ
10. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አስር
9. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ዘጠኝ
8. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስምንት
7. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሰባት
6. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስድስት
5. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አምስት
4. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አራት
3. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሦስት
2. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሁለት
1. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አንድ

2 Comments

  1. Eenyuuf himaa jrta?akkuma Habashaa eechaaka’e eecha adeema odeessitu.Waan Oromof himamu fi kan alagaa irraa dhokfamu jiraachuu qaba.Ak ati barruu afaan qomaaxee fi an buroos dhimma itti baatee barreesitu kuni saba bira kan akka sirna nafxnyaa nu Irratti kakasuuf yoo ta’e qofa kuni.
    sila dhimma Oromo qabaatte kana kommunitii oromo kan jaarrmiyaa fedhe iyuu haa ta’uu urra deemtee barsiifta.Ammaa alaagaaf gabaasa jirta miti ree?

    • Obbolessoo ceephoonkee kan afaan oromoof dhimmuurraa madde utuu hin taanee oromoo fakkaatte diinummaa afaanichaaf qabdu of saaxilukee agarsiisa. Barreessaan kutaa tokko kaasee hanga kutaa 16tti qabssoo bilisummaa oromoo ilalchisee yaadaa ijaarraafi waa’ee malummaa oromoorratti gadi faggeenyaan hubannoo nuuf gimmacheen galateeffamuu qaba malee arrabsamu hin qabuu adabadhuu ta’i siin jechuun barbaada.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.