የዘመናዊዉ ነፍጠኛ ማዕከል ካልተንበረከከ የኦሮሞ ነጻነት አይታሰብም

የዘመናዊዉ ነፍጠኛ ማዕከል ካልተንበረከከ የኦሮሞ ነጻነት አይታሰብም

ፍዳ ቱምሳ, July 23, 2020

ነፍጠኛ ማዕከል

የኢትዮጵያን ኢምፓየር ምስረታተከትሎየነፍጠኛ ማዕከላት ሆነዉየተመሠረቱ በርካታ ከተሞች በኦሮሚያና በደቡብ የሃገሪቱ ክፍሎችይገኛሉ። ከተማ የሚለዉመጠሪያ ራሱከነፍጠኛዉ ሥራዓት ጋር በእጅጉ የተያያዘ ቃል ነዉ። ነፍጥ ያነገቡ አካላት የተሰበሰቡበትና መሽገው የሚኖሩበት አካባቢ፣ እናም እነዚህ አካላት የከተሙበት በመሆኑ ከተማ ተባለ። እናም “ከተማ” የተባሉት በኦሮሚያና በሌሎች የደቡብ ብሄሮች ክልሎች ዉስጥ ያሉ ቦታዎች በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ፣ የነፍጠኛዉና በነፍጠኛዉየተመሰረቱ ናቸዉ። ከእነዚህ በርካታ ከተሞች ዉስጥ የዋናነቱን ቦታ ይዞ የሚገኘዉደግሞ ዛሬ ነፍጠኞችአዲስ አበባ ብለው የሚጠሩት ከተማ ነዉ። አዲስ አበባ ከተማ እስከ 1966 ዓ ም ድረስ የነበራት መልክ ከብዙዎቹ የነፍጠኞች ከተማ አንዷእና ትልቋእንጂ የተለየች አልነበረችም።

የየካቲት 25 ቱን የመሬት አዋጅ ተከትሎ በየቦታዉበተነሳዉ አብዮታዊ ማዕበል፣ በትግሉ ተሸንፈው በገጠር ትንንሽ ከተሞች መሽገዉየነበሩት ነፍጠኞችወደአዲስ አበባና ፣ “ትላልቅ” ወደሚባሉት ከተሞች መጉረፍ ተያያዙ።በዚህ የነፍጠኞች ፍልሰት የአዲስ አበባ ከተማ የነፍጠኛው ቁጥር ምናልባትም በአጭር ጊዜ በሁለት እጅ ሳያድግ አልቀረም።

ወደአዲስ አበባ የጎረፉት ነፍጠኞች፣ ገበሬዉንና ገባሩን ነፃነት ያጎናፀፈዉንና ፣ የተቀጣጠለዉን አብዮት አቅጣጫ በማስቀየር በኩል የተጫወቱት ሚና ቀላል አልነበረም። ዛሬ ወደኋላ ተመልሰን በትዝብት የምናያቸዉዕልቅቶችም ሆነ የአምባገነን አስተዳደር እንዲመሰረት ያደረጉት እነኝሁ ወደፊንፍኔ የጎረፉት ነፍጠኛችና ልጆቻቸው (ግልገል ነፍጠኞች) ነበሩ።

ገና ከጅምሩመሬትና የከተማ ትርፍ ቤት ያጣው ነፍጠኛግብ ግልጽ ነበር። የትኩረታቸው መሰረት ዛሬም እያደረጉት እንዳለው የህልውናቸው ዋና ጠላት ብለው በፈረጁት የኦሮሞ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ነበር። ግባቸው በዋናነት የኦሮሞን ሕዝብ የገዛ መሬቱ ባለቤትነት ማስናከል ነበር። በዚህ ረገድ እንደ አላማ አድርገዉየተያያዙት የኦሮሞ ምሁራንን የመግደል ፣ የማስገደል ሥራላይ መሰማራትን ነበር። በዚህ ረገድ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሱት ጥፋት ዝርዝሩ በታሪክ የተመዘገበ ስለሆነ እንለፈዉ። እዚህ ላይ ማመልከት የፈለግነዉ ፣ የካቲት 25ትን ተከትሎአዲስ አበባ ከመካከለኛ የነፍጠኛ መናሃሪያ ወደ ዋነኛዉ የነፍጠኛ ምሽግ መቀየሯን ነዉ።

ከባለመሬትነት የተገፋዉና በአዲስ አበባ የመሸገው ይሄ የነፍጠኛ ወገን የነፍጠኝነት ሀልውናውን ለማስቀጠል አዲስ ጭምብል መልበስ ነበረበት።ይሄ አዲስ ጭምብል ደግሞ “ኢትዮጵያዊነት” የተሰኘ ጭምብል ነው። “በኢትዮጵያዊነት” ና “በኢትዮጵያ አንድነት” ስም ያጡትን ሥልጣን መልሰው ለመቆጣጠር ከወቅቱ ገዢዎች ጋር በመዳበል የወሰዱት እርምጃ ለጊዜውም ቢሆን ተሳካላቸው። ለመሬት ፣ ለነፃነትና ፣ ለዕኩልነት የታገለዉን ወገን የተለያየ ስም በመስጠት ማስወጋትና መውጋቱ ሰከነላቸው። በዚህ ወቅት ነበር በአዲስ አበባ የመሸገው የአዲሱና የዘመናዊዉ ነፍጠኛ ርዕዮት “ኢትዮጵያ” ና “ኢትዮጵያዊነት” የሚል ካባ ደርቦ ብቅ ያለው።

በ1983 ይሄ ዘመናዊ የነፍጠኞች አስተሳሰብ በብሄር ብሄረሰቦች ትግል ተመትቶ ለጊዜውም ቢሆን ለዘብ እንዲል ለማድረግ ተችሎ ነበር። ይሁን እንጂ የ1983 ለዉጥ ባስከተለዉ ጫና ሁለተኛዉ ዙር የነፍጠኞችፍልሰት ወደአዲስ አበባ ተጀመረ። ዳግም አዲስ አበባ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ የነፍጠኛ ማዕከል ሆነች። ከበፊቱ በተለየ ቱባ ቱባ ነፍጠኞች ከአሰላ ፣ ከጎባ፣ ከጭሮ፣ ክሆሳእና፣ ከሶዶ፣ ከዲላና ከለሎችም ቦታ ወደፊንፍኔ ጎረፉ። እናም ትናንት በትግል ያጡትን የገጠር መሬት ዛሬ በፊንፍኔ ዙሪያ ያሉትን የኦሮሞ ገበሬዎች በማፈናቀል የመሬት ነጠቃ ተግባራቸዉን ተያያዙት። ይህን ለማስፈጸም ሀ ብለዉ ሲጀምሩ፣ ህገመንግሥቱ ላይ የተደነገገዉን የፊንፍኔ ከተማ ድንበር በማስፋት ነበር የጀመሩት። በደርግ ጊዜ ከነበረውና ህገመንግስታዊ እውቅና ከተሰጠው ድንበር በመሻገር የህገመንግሥት ጥሰት ሀሁ በነፍጠኞች በተቀረጸው የአዲስ አበባ ቻርተር ተጀመረ። ለአዲስ አበባ አዲስ ድምበር ተበጀላት። አድስ አበባ ማለት ፣ የከተማዋን ክልልና በመስተዳድሩ ዉስጥ የሚገኙትን 23 የገጠር ቀበሌዎች ያጠቃልላል ተባለና ነፍጠኞች የከተማዉ ክልል አካል ያልሆኑትን 23 የገጠር ቀበሌዎች የመጀመሪያ የኦሮሞ ማፈናቀል ድግስ አካል አደረጉት። የመስፋፋት ጉዞዉ ቀጥሎ ዛሬ አቃቂ፣ ኮተበ ወዘተ ወደ አዲስ አበባ ተጠቃለሉ አሉን። ይሄ ጉዞ የዘመናዊ ነፍጠኛች አያቶችበፊንፊኔ ይኖሩ በነበሩ የኦሮሞ ጎሳዎች ላይ የፈጸሙት ግፍ አካል ሆኖዛሬም ቀጥሎአል።

ይሄመስፋፋት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ወለደ። የቄሮ ቀሬ ትግልና ድል እምብርትም ሆነ። በቄሮ ድል ለአጭር ጊዜም ቢሆን የለውጥ አየር ተነፈስን። ይሁን እንጂ የኦሮሞ ህዝብ በቄሮ ትግልና መስዋዕትነት የተገኘዉን ድል አዲስ አበባ በተሰገሰጉት ዘመናዊ ነፍጠኞችተነጠቀ፤ የለውጥ ተሰፋውም ጨለመ። ዛሬ አዲስ አበባን ሀገሪትዋ ከምታፈራው ሀብት ከግማሽ በላይ የምትውጥ ከተማ አድረገዋት ዘመናዊ ነፍጠኞች የትናንቱን የገባር ሰርአት በአዲስ መልክ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ማስቀጠል የቻሉባት መአከላቸው ሆናለች።

ዛሬ የደረስንበት እርከን የሚያመላክተን የኦሮሞ ህዝብ ቀጣዩ ትግል ከማን ጋር መሆን እንዳለበት ነዉ። የኦሮሞ ነፃነት ይሄን የነፍጠኞች ማዕከል የሆነ ከተማ ከማንበርከክ ጋር በቀጥታትስስር አለዉ። የኦሮሞ ህዝብየነፅነት ትግል ነቀርሳ አዲስ አበባ ነዉ። ይህ ነቀርሳ ገዳይና አጥማጅ ነው። ይህነን ነቀርሳ የሚመግቡየደም ሥርየሆኑትን መንገዶችበመዝጋት ብቻነቀርሳዉንማመንመንና ዳግም እንዳይንሰራራተደርጎ እጅእንዲሰጥካልተደረገ የነፃነታችንና የህልውናቸንጉዳይ አጠያያቂ ይሆናል። አዲስ አበባ ..ከነፍጠኞችእስካልጸዳች ድረስ የኦሮሞ ነጻነት አይታሰብም።

ለዚህም ነዉ የሰላማዊ ትግላችን ትኩረት አድስ አበባን በማንበርከክ ላይ ያለመ መሆን አለበት የምንለዉ። ይሄን በማድረግ የዘመናዊ ነፍጠኞችማዕከል እናፈርሳለን። በዛ ፍርስራሽ ላይ አዲሱ ኡማዊነት ኢትዮጵያዊነትን ተክቶ የኩሽ ህዝቦች የማንነታችንና የዜግነታችን መገለጫ ይሆናል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.