ያመለጠን አጋጣሚና የኦሮሞ ሕዝብ ሰቆቃ

ያመለጠን አጋጣሚና የኦሮሞ ሕዝብ ሰቆቃ

ብርሃኑ ሁንዴ, Bitootessa 20, 2020

በኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ታሪክ ውስጥ ብዙ ያመለጡን አጋጣሚዎች ቢኖሩም፣ የ2018 አጋጣሚ ግን የማይመለስ ወይንም ቢመለስም እንኳን ከባድ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ነው። በ1991 የተደረገው ስር ነቀል ለውጥ ለኦሮሞ ብዙ ድሎችን ከማስመስገብም አልፎ ከ 2016 እስከ 2018 ለተደረገው ሕዝባዊ እንቅስቃሴና ለቄሮ ትግል ትልቅ መሰረት የጣለ ነው። ምክንያቱም የቁቤ ጄኔሬሽን ተብለው የምታወቁትን ወጣቶች ወይም ቄሮዎችን  የወለደ ትግል ወይም ለውጥ በመሆኑ ነው። ይህ በኦሮሞ ብሔርተኝነት የተገነባውና ቆራጥ ትውልድ የ150 ዓመታት የኦሮሞ ሕዝብ ጭቆናን ማብቃት ስችል በተሰሩት ጥቂት ስህተቶች ይህ ትግል ተቀልብሶ ባልተጠበቁ ኃይሎች እጅ ገብቶ ይኸው ዛሬ ሕዝባችን ከምንጊዜውም የበለጠ ሰቆቃ ውስጥ ገብቶ ይገኛል።

የምያሳዝነው ግን ኦነት የተጠበቀውን ወይም የተመኘውን ግብ እንዳይደርስ የሚያደርገው የውጭ ኃይሎች ጥንካሬ ሳይሆን፣ የውስጣችን ችግር ነው። በኦሮሞ ውስጥ ያሉት ችግሮች ደግሞ መጠነ ሰፊና የተለያዩ ገፅታዎች ያላቸው ሲሆኑ በዋናነት የትግላችን እንቅፋት የሆኑት አድርባይነትና ራስ ወዳድነት ነው። ለሕዝብ ወይም ብሔራዊ ፍለጎት ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ ለግል ጥቅማ ጥቅም መገዛት አንዱና ዋንኛው ፀረ ኦነት ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዚህ ትግል ውስጥ ሚና የነበራቸው እንኳን በግል ጥቅማ ጥቅም ተገዝተው፤ የሕዝባችንን ሰቆቃ እያዩ ግን ለራሳቸው ምቾት ብለው ፀረ ሕዝብ ድርጊት ሰስሩ መታየት እጅግ ያሳዝናል። “የማይነጋ መስሎት ….” እንደሚባለው ተረት እነዚህ ለግል ጥቅምና ምቾት ብለው የሕዝባችንን ስቃይ በዝምታ የምመለከቱት ነገ ከታሪክ ተጠያቂነት እንደማይድኑ መገንዘብ አለባቸው።

ወደ ፅሁፉ ርዕስ በመመለስ፣ ያመለጠን አጋጣሚና የኦሮሞ ሕዝብ ሰቆቃ ያልኩበት ዋንኛው ምክንያት በ2018 የሕዝባችን አመፅና የቄሮ እንቅስቃሴ ወያኔን አንበርክኮ ድል ስቀናጅ፣ ወዲያውኑ ትግሉን ወደ ተፈለገው ግብ ከመውሰድ ይልቅ ለOPDO ዕድል መስጠ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነበር። ይህ ቀድሞውኑ ለኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት ቆሞ የማያውቀውን ተለጣፊ ድርጅት አምኖ የሽግግር ለውጡን እንዲመራ ዕድል መስጠት ዛሬ ባጠቃላይ ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ በተለይ ደግሞ የምዕራቡና የደቡቡ የኦሮምያ ክፍል ሕዝቦቻችን ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንዲገቡ አድርጔል። ዛሬ የ 2016 እስክ 2018 ተመሳሳይ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ቢነሳ እንኳን በዚያን ጊዜ የነበረውን ያህል ሕዝባችንን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ አንቀሳቅሶ ድል እንዳያመጣ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ተፈጥሯል።

ዛሬ PP ተብየው ከOPDO የተወለደው ድርጅት በብዙ መንገዶች ሕዝባችንን እያወናበደና እያታለለም አልፎም ደግም ለሆዳቸው የምያድሩትን ጥቂቶች በገንዘብና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ወደ ራሱ እየሳበ፤ ለነፃነት ትግላችን እንቅፋት እንዲሆኑ እያመቻቸ ነው። በጎኑ ደግሞ ሁሉን ነገሮች በእጁ ካስገባና ራሱን ካረጋጋ በኋላ ወደ አምባገነንነት በመለወጥና ሁሉንም ነገር በኃይል ለማሸነፍ እየሰራ ይገኛል። ጌታችን ሕዝባችን ነው ሲሉ የነበሩትም ዛሬ ድምፃቸው አይሰማም። ተቸገረው ይሁን ወይንም ደግሞ ቀድሞውኑ ሕዝብን ለማታለል እንደሆነ አይገባም። እንግዲህ አመቺ ያልሆኑ ጉዳዮች በተፈጠሩበት ሁኔታ ውስጥ የ2018 አጋጣሚ ተመልሶ እንኳን ቢመጣ፣ በዚያን ጊዜ ካስከፈለን መስዋዕትነት የበለጠ እጅግ ከባድ መስዋዕትነት ማስከፈሉ የማይቀር ነው። ለዚህም ነው ያመለጠን ኣጋጣሚ ያልኩት።

በሌላ ጉዳይ ተመልሰን እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት።

2 Comments

  1. Prostitutes and pimps had went out of business in Addis due to CoronaVirus Covid-19 , all along the prostitutes and the pimps insured the safety of their favorite high paying customers-the foreigners ferenjis.

    Now with the pimps and the prostitutes out of the picture the real feeling sentiments of the Ethiopians is coming out.

    https://www.zehabesha.com/ethiopian-pm-urges-tolerance-as-anti-foreigner-sentiment-rises-over-virus/

    https://borkena.com/2020/03/19/ethiopia-reported-anti-foreigner-sentiment-over-covid-19-pandemic-manufactured/

  2. Dear Berhanu Hunde,

    Thank you very much for your concern. However, this time it will not be the Oromos alone who will pay the price. In 2018, Oromos sacrificed 6000 of its youth to bring the change. This time the Oromos will eliminate its enemies first and die if necessary. This time we will make sure that OPDO is our number one enemy. If they want to save their lives let them leave their positions. within a week.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.