ሰራዊት ወይስ አራዊት???

ሰራዊት ወይስ አራዊት???

Via Ejjeetto Sidama Affairs ESA

በእኛ ጊዜ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዲስፕሊን እንደዝህ አልነበረም ወታደራዊ ዩንፎርም ተለብሰዉ መንዘላዘል ከሰራዊቱ ባህርና ጨዋነቱ ዉጪ ነዉ፡፡

ደቡብ ክልል ግዘያዊ ወታደራዊ መንግስት ኮማንድ ፖስት ተስማርተዉ በተለይ ሲዳማ ዞን የተላከው ሰራዊት ፍጹም ከሰራዊቱ ጨዋነት ዉጪ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ሰራዊት ተብየዉ ምን አይነት ኢ-ሞራላዊና የልዕልና ድቀት ያላቸዉ በማፊያ አመራር እንደሚመራዉ ግራ በሚያጋባ መልኩ ከነትጥቃቸው አልኮል መጠጥ ጠጥቶ የህዝብን ሰላም እየጠበቁ ያሉበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ፡፡

እንግዲህ መጠጥ በመጠጣት ሰራዊቱ የህዝብን ሰላም ከመጠበቅ አልፎ የህዝብ እዳና ሰዉ በላ አዉሬ ሆኗል፡፡

በየወረዳው የተስማሩት ሰራዊት የወረዳ አስተደደር ገንዘብ ካለመጣችሁ ብሎ ሰራዊቱ በማስፈራራት ከዘረፋ ባልተናነሰ መልኩ ትልቅ ሀርሽ ዉስጥ ተገብቷል፡፡

በተጨማሪም ለመናገር በምቀፍ ሁኔታ አስፈራርቶ ሴቶችን ከባለበታቸዉ ነጥሎ ስብዕናን በሚጎዳ መልኩ ነዉር እየፈፀሙ አስገድዶ እየደፈሩ መሆኑን ተረጋግጧል፡፡

ግለሰቦች በቂምና በቂምና በበቀል ተነሳስተው ወታደሮችን እየመሩ ንጹሃን አርሶ አደሮችን እያስገደሉ ነው፤ በርካታ ትላልቂ ሽማግለዎች የሞት ሰለባ በመንግስት ሰራዊት እየሞቱ ነዉ፡፡

ነፍጥ አስተሳሰብ አንጋቢዎች ተላላኪ ኮማንድ ፖስት ተብየው የተማረና የህዝብ የምቆረቆር ምሁራን አሳዶ በማሰር ጅምል ጦርነት የሲዳማ ህዝብ ላይ እየፈጸመው ይገኛል፡፡

ነገሩ እነደዝህ ከሆኔ መንግስት ህዝብን በጋጥወጥ ሰራዊ (አራዊት) አሰላችተዉ በግፍ አንገት ለማስደፋት ለዳግመኛ ህዝቡ (ወጣቱ) መንግስትን የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ደፍሮ እዳያቀርብ ኢ-ሞራለዊ በአደገኛ ሁኔታ ሽንቁር ትዉልድ ለመፍጠር የህዝብ ሞራል ላይ ሚናዉን እየተጣ መሆኑን ያመላክታል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ በዝህ ዘመናችን በ21ኛዉ ክ/ዘመን አሳፋሪ ድርጊት ከመሆኑም ባሻገር የደካማ መንገስት መገለጫ ነዉ፤ በመሆኑም እስከ መቸም ብሆን የህቡ ትክክለኛ ይገባኛል የመብት ጥያቄ በዝህ አሳፋሪና አስነዋሪ ደባና ድርጊት የምቀለበስ አለመሆኑን አዉቀዉ መንግስት የገዛ ህዝቡን ከመበደል እንድ ታቀብ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰብያ፦ ከዝህ አስነዋሪ ድርጊቱ መንግስት የሚያቆም (የማይመለስ) ከሆነ ህዝባዊ ትግልን በማጠናከር የደካማ መንግስትን ግብኣተ መሬት የሚያፋጠን ስራን የሚናያጠናክር መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.