ቦምቡ እንኳንም ቶሎ ፈነዳ እንጂ ; Messages of Condolences

0

ቦምቡ እንኳንም ቶሎ ፈነዳ እንጂ ; Messages of Condolences

By Tullu Liban

blank

በዶር አምባቸው መኮንንና በሁለቱ ጓዶቻቸው ላይ እንዲሁም በኤታማዦር ሹሙ ሰዐረ መኮንንና በጄኔራል ገዛኢ አብርሃ ላይ ባለፈው ቅዳሜ የተፈፀመው የጭካኔ ግዲያ እጅጉን ሊወገዝና ሊኮነን ይገባል። መገዳዳል ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደማያመጣ በ53ቱ መፈንቅለ መንግስት፣ በቀይና ነጭ ሽብር ዘመቻ፣ በወያኔ የ25 ዓመታት የሰቆቃ ዘመን አይተናል። የሞከርነውንና የከሸፈውን አማራጭ ለምን እንደጋግመዋለን ግን?

በተለይም የአማራ አክቲቪቶች ነን የሚሉ የሞት ሰባኪያን የሚፅፉትንና የሚለጥፉትን የግደል፣ ወጥር፣መክት … ጥሪ ስናስተውል አሁን የሆነውን ማየታችን አይገርመንም። አሁንም መዘናጋት አያስፈልግም። እነዚህ ሞት ጠሪ እብዶች ይፀፀታሉ፤ ይመለሳሉ ብሎ ለማሰብ ያስቸግራል። እነርሱ ይህን ክፉ ዕድል የተመኙት ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ ነበር።

የአማራ ሊህቃን እንወዳታለን ለሚሏት ኢትዮጵያ የሚበጅ፣ አሁን ላለንበት ነባራዊ እውነታ የሚመጥን፣ እኩልነትንና ብዝሃነትን የሚቀበል አመራጭ ማቅረብ መቻል አለባቸው። የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት እንደመፍታት ወደ እርስ በርስ ሽኩቻ መግባት ይኸውና ደም ወደመቃባት አምርቷል። ይህ ትምህርት ሊሆነን ይገባል።
ከቅርብ ወራት ወዲህ በአማራ ክልል እያቆጠቆጠ የመጣው ፅንፈኝነት ቅርፅና ይዘቱ አልለይ ብሎ ብዙዎቻችንን ስጋት ላይ እንደጣለን ሰንብቷል። መንገድ ላይ መኪና እያስቆሙ ጥራጥሬና እንስሳት ከመዝረፍ ጀምሮ ጎረቤት ክልሎችን እስከመውረር የደረሰ እብሪት እያየን ነበር። ከዚያም አለፍ ሲል “አማራ የሰውነት የውሃ ልክ ነው፣ ኢትዮጵያ ለፈጣሪዋ ለአማራ መስገድ አለባት” የሚል እብሪተኛ ዲስኩር የፖለቲካ መሪዎች ነን ከሚሉ ሰዎች ስንሰማ ነበር። ናዚዎችና ፋሽቶች ከዚህ የተለየ ቅስቀሳ ስለማድረጋቸው በአግራሞት ስንታዘብ ቆይተናል። የሂትለር የአርያን ዘር ትርክት ከዚህ የተለየ አልነበረምና።

የሚያስገርመው ነገር የአንዳንድ የአማራ ጉምቱዎችን እብሪትና የፊደላውያን ተከታዮቻቸውን ጥራዝ ነጠቅ ትንኮሳ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፍ የእዮብን ትዕግስት ይጠይቃል። እንደኔ እንደኔ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ የሚመጣ መሪ (አማራውንም ጨምሮ) እንደ አብይ አህመድ እንዲህ ዓይነቱን እብሪት የሚታገስ አይመስለኝም። እንዲህ ስል ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ወይም የመለስ ዜናዊን ፈለግ ለምን አልተከተሉም ብዬ ቅሬታ ማቅረቤ አይደለም። በአብይ አህመድ አያያዝ ያልረካ የመቻቻል ፖለቲካ በማን እንደሚረካ ለመገመት ያስቸግረኛል። አብይን የሚያጥላላና የሚጠላ የአማራ ሊህቅ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የተሻለ ለዘብተኛና አቃፊ መሪ ለማግኘት በቅርቡ ይቻለዋል ብዬ አላምንም። ኦሮሞው ወይም ሲዳማው አብይን ቢያማርር አይገርመኝም። ጥያቄ አላቸውና። ነገር ግን ከሌላ ብሔር ሆኖ የአማራ ሊህቃንን ትርክት በበጎ መንፈስ ተመልክቶ በይቅር ባይነት ለመጓዝ የሚሞክር መሪ ስለማይመጣ በአብይ ቅሬታ ያላቸው የአማራና የትግራይ ሊህቃን በመፅሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት ኢየሱስን መጠበቅ እንዳለባቸው ይሰማኛል። ለምን ቢሉ ከየትኛውም የገባር ሕዝብ ወገን የሚመጣ የፖለቲካ መሪ ምኒልክንና ሰሜናዊ ነገሥታትን እያወደሰ፣ ራሱ የተገኘበትን ሕዝብ እያስቀየመ ኢትዮጵያን ላሻግር ብሎ ቃል አይገባምና ነው።

በደቡብ ገባር ሕዝቦች አይን (ኦሮሞን ጨምሮ) የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ልብ ለትግራይና ለአማራ የሚራራውን ያህል ለሌላው አይራራም።

እንዳለመታደል ሆኖ የአማራ ወጠጤ ድርጅትና እና ህወሃት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምርረው ይጠሏቸዋል። ህወሃትስ ምክንያት አለው። የአብን ምክንያት ግን ፍፁም ግልፅ አይደለም።

ተመሠርቶ ገና በአንድ ዓመት ዕድሜው የአማራን ክልል እያተራመሰ ያለው ነውጠኛው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መሪዎች “አማራ የሰውነት ውሃ ልክ ነው፣ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ለፈጠራት አማራ መስገድ አለባቸው” ብለው ያለምንም ሐፍረት ሲናገሩ ከመስማት በላይ የሚሰቀጥጥ ወሬ አይኖርም።

እነዚህ ወገኖች አሁን ደግሞ ነውራቸውን ለመሸፈን የአብይ አህመድ መንፈስ ነው አሳምነው ጽጌን አነሳስቶ ጓዶቹን እንዲገድል የቀሰቀሰው ሊሉን እየዳዳቸው ነው።
እጅግ የሚያስገርመው ነገር ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስን የመሳሰሉ በከፍተኛ የኦሮሞ ጥላቻ የሚሰቃዩ አረጋዊ ደርጋውያን ሳይቀሩ አብይ አህመድን ሲያጥላሉ፣ ኦነግን አማራ ክልል ውስጥ ግጭት ቀሰቀሰ ብለው ሲወነጅሉ፣ ቄሮን ሲራገሙ፣ ጀዋር መሐመድን በሐሳባቸው ሲሰቅሉት፣ ኦ ኤም ኦን ቴሌቪዥንን በህልም ሚሳይል ሲያጋዩት በአማራ ክልል የተንሰራፋውን መረን የለቀቀ ሥርዓተአልበኝነት፣ የአብንን ጋጣወጥነት፣ የኢሳት ቴሌቭዥንን የውሸት ጎተራነት ( አሁን ከተሻለው እንጃ)፣ የአማራ አክቲቪስት ነን ባዮችን ብልግናና ዘር ተኮር የአመፅ ቅስቀሳ አይደለምና ማውገዝ በጨረፍታ እንኳን አይተቹም። (በቅርቡ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ “ኢትዮጵያ ወዴት” በተባለ መድረክ ያሰሙትን ዲስኩር ማዳመጥ በቂ ነው)።

ይልቁንም ሻለቃው የእስክንድር ነጋን ህገወጥ ባላደራ እንደ ጥሩ የሲቪክ እንቅስቃሴ ሲያንቆለጳጵሱት ነው የሰማነው።

እንዲህ ዓይነት የአማራን ሕዝብ ከኢትዮጵውያን ወገኖቹ የሚለይ ፅንፈኝነት ካልተወገዘና በመደበኛ መገናኛ ብዙኃንም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ የሚካሄድ የግደለው ፍለጠው ሽለላና ቀረርቶ ካልተገታ የአማራን ክልል ወደ መጥፎ ቀውስ ከመክተት አልፎ ሀገሪቷንም ወደ መጥፎ ትርምስ ይወስዳታል።

በርግጥ አሁን የፈነዳው ቦንብ የንፁሓን ወገኖችን ህይወት ቢቀጥፍም ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንኳንም ፈነዳ ያሰኛል። በዚሁ የሚያልፍ ከሆነ ነው ታዲያ።
አሁን በአምባቸው መኮንንና በጓዶቻቸው ላይ የተካሄደው ጥቃት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላይ እንዲደረግ በኃይሉ ቢታኒያ በሚል የፌስቡክ ስም በሚፅፍ የአማራ አክቲቪስት ነኝ ባይ በጥቅምት ወር 2018 ታውጆ ነበር። ያ ሰው አሁን ያን የፌስቡክ አካውንት ዲአክቲቬት አድርጎታል። ይኸኔ በሌላ ስም ፍለጠው ቁረጠው እያለ ይሆናል።

ከዚህ በታች ያለውን ሟርት ተመልከቱት።Ethiopia

France strongly condemns the series of attacks perpetrated on Saturday, June 22 in Ethiopia, aiming especially for the president of the amhara region, ambachew mekonnen, as well as the chief of staff of the army, general seare mekonnen.

We reiterate our support to the Ethiopian Prime Minister, Abiy Ahmed, in his efforts of reforms and gathering of the Ethiopian people, essential to the stability of the country.

2 COMMENTS

  1. Fact is Mengistu Hailemariam was from the tribe of KONSO , as Hailemriam Desalegn was also from the tribe of KONSO as the next leader after Abiy most likely will also be from the tribe of Konso.

    We Konso people are paying too many sacrifices since we are determined to fulfill not only our dream but also our obligation of leading Ethiopia.

  2. Most likely it is the Gondares that drove the Welloyes to the limit ,since Gondares do not know how to behave with mutual respect in a civilised manner.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.