ትንሽ ስለ ኦነግ! – Abraha Desta
=========

Abraha Desta, Chairman of Arena Tigray and former philosophy lecturer at Mekele University

ኦነግን ማመስገን ዘረኛ-ነት ከሆነ ኦነግን መተቸት ቅዱስነት ሊሆን ነው? የራሴን ለራሴ ያለ ስህተት ከሆነ የራሴም ለራሴ የናንተም ለኔ የሚልስ ምን ሊባል ነው? ኦነግ ራስን በራስ የመተዳደር (Self Determination and Self Rule) ጥያቄ እንጂ የመገንጠል (Secessionist) ዓላማ አለው ብዬ አላምንም። የመገንጠል ዓላማ እንኳ ቢኖረው ለመገንጠል የፈለገበትን ምክንያት ጠይቆ መፍትሔ መፈለግ እንጂ ማጥላላት ምናመጣው!? እገነጠላለሁ ከሚል በላይ ተገንጣይን የሚያጥላላ ወገን የባሰ ገንጣይ የለም።

አሁንም ኦነግ የመገንጠል ዓላማ አለው ብዬ አላምንም። ቢኖረውም ለኦነግ ያለኝ ክብር አይቀንሰውም። ኦነግ ባሁኑ ሰዓት ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ላይኖረው ይችላል። ኦነጋዊ አስተሳሰብ ግን በኦሮሞ ህዝብ ልብ ውስጥ አለ።

ኦነግ የስልጣን ጥማቱ ለማርካት ሲል ከህወሓት ኢህአዴግ ጋር አልተሞዳመደም። ብአዴንና ኦህዴድ ለስልጣን ሲሉ የህዝባቸውን ጥቅም አሳልፈው በመስጠት የህወሓት ቅጥረኛ አሻንጉሊቶች ሆነው ከህዝብ ይልቅ ግዝያዊ ስልጣን መርጠው ጌቶቻቸውን ለማገልገል ህዝባቸውን ሲበድሉ ነበር።

ኦነግ ግን ህዝቡን መርጦ ከህወሓት ጋር ተጣልቶ ጫካ ገባ፤ ለህዝብ ቆመ እንጂ ለስልጣን አልተሸጠም። ክብር ይገባዋል። ከስልጣን በላይ ህዝብን የሚያስቀድም ድርጅት ያልተመሰገነ ማን ሊመሰገን!? አሻንጉሊት? አሻንጉሊት ክብር የለውም! ልብ በሉ የኦነግ አባላት ለ27 ዓመት ያህል በህወሓት ኢህአዴግ ሲሰቃዩ የኦህዴድ ባለስልጣናት የጨቋኑ ስርዓት ቁልፍ መሳርያ ነበሩ።

የኦነግ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚገባውን ሚና መጫወት አለበት ነው። ይህም ትክክል ነው። መደነቅ ያለበትን እናድንቅ።

It is so!!!

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...