ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለመቀጠል ማለፍ ያለባት ፈተናዎች

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለመቀጠል ማለፍ ያለባት ፈተናዎች

በፍዳ ቱምሳ, Guraandhala 9, 2020

የኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል አለመቀጠል ሰዎች ስለ ፈለጉት ብቻና በምኞት የሚሳካ ጉዳይ አይደለም። እንደ ሀገር የመቀጠል አለመቀጠል ጉዳይ የሚወሰነው በዚያች ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች፡ በተለይም የፖለቲካ ተዋናዮች በሚወስዱት የተሳሳተ እርምጃ፡ ወይም መውሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች በጊዜው መውሰድ ተስኖአቸው ሳይወስዱ በመዘግየታቸው ምክንያት ይሆናል። ብዙዎች የኢኮኖሚ ችግር፡ የማህበራዊ ኑሮ ችግር፡ የተፈጥሮ ሀብት እየመነመነ የመሄድ ችግር … ለመፍታት በምናደርገው እንቅስቃሴ ሀገር ማቆየት የምንችል ይመስላቸዋል… በኢትዮጵያ እነኝህን ችግሮች ለመፍታት ከመነሳታችን በፊት በህዝቦች መካከል ያለ ግንኙነትና፡ በህዝቦችና በሀገረ መንግስት መካከል ያለ ግንኙነት፤ መፋለስና ይሄም ለፈጠረው ያለመግባባት መሰረት ለሆኑት ጉዳዮች መፍትሄ መሻት ያስፈልጋል።

በእነዚህ ያለመግባባት መሰረትና ሀገርን የማስቀጠል ፈተናዎች ላይ እርምጃዎች ለመውሰድ፡ በፈተናዎቹ ምንነት ላይ መስማማት ያስፈልጋል። በኛ እምነት ከፈተናዎቹ መካከል ምናልባትም ዋናዎች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ ሁለቱ አብይ ሆነው ይታዩናል። እነዚህም አንደኛ እያንዳንዳችን ራሳችንን ከሀገሪቱ ጋር የምናስተሳስርበት ማንነት እና ሁለተኛ የሀገሪቱን የፖለቲካ ማእከል የሚመለከቱ ጉዳዮች ናቸው።

ዛሬ ከእያንዳንዳቸን የሚጠበቀው ራሳችንን ከሀገሪቱ ጋር የምናስተሳስርበት ማንነት “ኢትዮጵያዊነት” ብለን የምንጠራው ማንነት እንዲሆን ነው። “ኢትዮጵያዊው ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት የቻሉት ፡ እኛ “ኢትዮጵያዊው” ነን የሚሉ በዋናነት አማሪኛ ተናጋሪ ብቻ ሆነው ባለበት ሁኔታ … “ኢትዮጵያዊነት” የሚለውን ማንነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ህዝቦች የማንነታቸው መገለጫ ማድረግ ከቶ አይቻልም። ዛሬም በሀገሪቱ “ኢትዮጵያዊው” ለመሆን አማሪኛ ተናጋሪ እናም ራስን ወደ አማራነት መቀየር ይጠበቃል።፡

ዛሬ “ኢትዮጵያዊነትን” ከአማራነት ብቸኛ ማንነት አላቀን፡ ሌሎች ማንነቶች እንዲያቅፍ እናደርጋለን ብለው የሚዳክሩ ወገኖች ከከንቱ ድካም በስተቀር የሚፈይዱት ነገር የለም። ዛሬም ሆነ ነገ ማንም ራሱን “ኢትዮጵያዊ” ብሎ ለመጥራት የወሰነ ስው .. የራሱን ማንነት ደጅ አስቀምጦ ወደደም ጠላ የአማራ ማንነትን መቀበል ይጠበቅበታል። “ኢትዮጵያዊነት” በሁለመናው አማራነትን .. ባህሉንና እምንቱን መቀበልን ይጠይቃል። “ኢትዮጵያዊነት” በኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ያሉ ማንነቶችን የሚያገል በመሆኑ በኔ እምነት በኢትዮጵያ ሀገረ ግዛት ነዋሪዎች የማንነት መገለጫ ሌላ መጠሪያ እንደሚያስፈገን መግባባት አለብን። እኛ “ኢትዮጵያዊ” ወይም ፡”ሃበሻ”፡አይደለንም .. ልንሆንም አንችልም .. የኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ነዋሪ ግን ነን። ምናልባትም እንደ ቡርኪናቤዎች (Upright People) እኛም የኢትዮጵያን ህዝቦች ማንነት የምንገልጥበት ሌላ መጠሪያ መፈለግ ይገባናል፡፡ “ኢትዮጵያዊነት” ለሃገረ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች የጋራ ማንነት መገለጫ ላይሆን፤ ለማዳንም በማይቻልበት ሁኔታ በአብዛኛው የተገዥነት ሰቆቃ ላይ ባመጸው ትውልድ ልብ ውስጥ ሞቶአል፡፡ ከሙት ቀስቅሶ ሌሎችን እንዲያቅፍ ለማድረግ ከቶም አይቻልም፡፡ እናም ለሃገረ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች ሁሉ የሚሆን ሌላ ስያሜ በጋራ እንፈልግ፡፡

የፖለቲካ ማእከላችን የአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) ጉዳይ ሌላኛው የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት የሚያፈርስ ጉዳይ ነው፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የተመሰረተችው የኦሮሞና የቀሩትን የደቡብ ህዝቦችን ማንነት ለማጥፋት ባለመ የሀገረ መንግስት ግንባታ ውጥን ነው፡፡ የዚህ ስርአት ዋነኛ መገለጫ ሆኖ እስከዛሬም የዘለቀው አቅኝዎች የከተሙባቸው መንደሮች (ከተሞች) የተመሰረቱበትን ህዝብ ማንነት በማጥፋት እናም የህዝቡን የሀገሩ ባለቤትነት በመንፈግ ነው፡ ፡ ይህ ጉድይ በብዙ ቦታዎች የማንነትና የባለቤትነት ጥያቄን አስነስቶአል። ይህ የማንነትና የባለቤትነት ጥያቄ ደግሞ ከየትኛውም ቦታ ይልቅ ጎልቶ የሚታየው በፊንፊኔ ነው፡፡ ለፊንፊኔ የማንነትና ባለቤትነት ጥያቄ መልስ ሳይሰጥ የኢትዮጵያን ፈተናዎች ማለፍና ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ከቶውንም አይቻልም፡፡

የዛሬው የፌዴራል ስርአትም አመሰራረት አንዱ ቁልፍ ችግርም ፊንፊኔ ነው፡፡ የፌዴራል ስርአቱ ኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ ፊንፊኔ ነች ብሎ ስያበቃ በሌላ በኩል ከቀደመው ስርአት በከፋ መልኩ የኦሮሞን ማንነት ከከተማዋ ለማራቅ የሚጥር ብቻም ሳይሆን ከተማዋን በመለጠጥ ኦሮሞን ከአካባቢው ለማጥፋት እየሰራ በመሆኑ ይህ ጉዳይ ለተከታታይ የኦሮሞ ህዝብ አመጽ መነሻ ሆኖአል። ማንም ራሱን ኦሮሞ ብሎ የሚያውቅ ዜጋ የፊንፊኔ ጉዳይ የኦሮሞ ህዝብ የህልውና ጉዳይ እንደሆነ ይገነዘባል። በፊንፊኔ ላይ የተፈጸመው ተከታታይ ታሪካዊ ደባ የኦሮሞን ማንነት ለማጥፋት የተደረገ አጠቃላይ ግፍ አካል መሆኑን እያናዳንዱ ኦሮሞ ይረዳል። ይሄንን ግፍ ትናንት በፈጸሙ ወገኖች ዘንድ ዛሬም ያለው አስተሳሰብና አካሄድ ከትናንቱ የተለየ ያለመሆኑን ኦሮሞ ያውቃል።

በነኝሁ ሀይላት ከተሰሩት ደባዎች አንዱና ዋነኛው ፡ ፊንፊኔ የኦሮሚያ አካል መሆንዋን ህገ መንግስቱ ቢደነግግም (ፊንፊኔ የፌዴራል መንግስቱ አካል የሆነችው በኦሮሚያ ግዛትነትዋ ነው) … የኦሮሞ ቋንቋ፡ ባህል፡ ማንነት በፊንፊኔ ውስጥ ማሳደግ እንዳይቻል .. የፊንፊኔን አስተዳደር .. በፌዴራል መንግስት ስር በማስገባታቸው ነው። በዚህ ረገድ ያለፈውና ዛሬም ያለው ሰርአት መገንዘብ ያቃተው ፊንፊኔ ከኦሮሞ ህዝብ ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑንና ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ የሀገሪቱን አንድነት የሚፈታተን መሆኑን ያለመረዳት ነው።

ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ከመሆንዋም በላይ ለኦሮሞ ህዝብ ደግሞ የደረሰበትን ታሪካዊ በደልን ለማረቅ በሚደረግ ትግል የተለየ ትርጉም ያላት ከተማ በመሆንዋ የፌዴራል መንግስቱ በከተማይቱ ከመገልገል ባለፈ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ውስጥ ያለውን እጁን ቢሰበስብ ለዚህ ችግር መፍትሄ ይሆናል እንላለን። የኦሮሞ ቋንቋ፡ ባህል፡ ማንነት ለፊንፊኔ ባዳ በሆነበት ሁኔታ ለኦሮሞ ኦሮሚያን ማሰብ አይቻለውም። የፊንፊኔ አስታዳደር ዋሰንና የባለቤትነት ጥያቄ መፍትሄ ሳያገኝ ..ኢትዮጵያ አትታሰብም።

የፌዴራል መንግስት ሌሎች የክልል ከተሞችንም ዋና ዋና የፌዴራል መስሪያ ቤቶችን (የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች) እንዲያስተናግዱ በማድረግ ሌሎች የክልል ከተሞችን ከማሳደግ ይልቅ ፊንፊኔን ከኦሮሞ ለመነጠል የሚያደርገው እንቅስቃሴ ሀገሪቱን የሚንጥ ውዝግብ ለመቀስቀስ ምክንያት ሆኖአል።

ትናንት የተጀመረውንና ዛሬም ቀጥሎ ያለውን የፊንፊኔን ከአማራ ክልል ጋር የማገናኘት እንቅስቃሴና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመካሄድ ላይ ያለው ኦሮሚያን ወደ ሁለት የማይገናኙ አካላት ለመቁረጥ እየተደረገ ያለው የተንኮል ጉዞና በአሁኑ ወቅት በተቀናጀ መልኩ ወደ ኦሮሚያ ለሰፈራ የሚደረገው እንቅስቃሴ .. የተለያዩ የኦሮሚያን ግዛቶች በወታደራዊ አገዛዝን ሰቆቃ ስር ማሰቃየት፤ “በኢትዮጵያዊነት” ስም “ብልጽግናን” ተከናንቦ የኦሮሞን ህዝብ አንድነት ለመናድ እየተደረጉ ያሉ እንቅሰቃሴዎች .. የኦሮሞን ህዝብ ነፃነቱን ከኢትዮጵያ ውጭ ወደ ማሰብ እንደሚያሸጋግረው መረዳት ያስፋልጋል።

ራሳቸውን ”ኢትዮጵያዊያን” ብለው ከሚጠሩና ሌላው የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን እነርሱን መሆን እንዳለበት ከሚስብኩት ጋር የኦሮሞ ህዝብ በአንድ ሀገር የመኖሩ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ እየገባ ነው። የሀገረ መንግስት ግንባታው የህዝቡን ማንነት በሚያጠፋበት መንገድ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ.. የኦሮሞ ህዝብ ራሱን አንድነቱን ማንነቱን በነፃነት ለማስጠበቅ የተለየ አማራጭ እንዲያልም እያስገደዱት ነው። ዛሬ ራሳቸውን “ኢትዮጵያዊያን” ብለው የሚጠሩ ወገኖች ኦሮሞንና ሌሎች ጭቁን ህዝቦቸን ወደዚህ አማራጭ እየገፉት መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

 

2 Comments

 1. Farm development investment is crucial not only for the economic development of the country but to ensure safety all throughout the country including in remote parts of Ethiopia . Well done Gambella!!
  The humble government of Gambella is currently lifting the people of Gambella to greatness.
  Gambella is a place that is on a remarkable rise , the development that is taking place in Gambella within the last year or two is so huge it is nothing but a success poster region of the change era, that made Gambella a place of infinite possibilities , all thanks to the new reformed Gambella’s regional government policy that took its time to study the tax records of each farm investors that operated in Gambella in the last two decades, by studying both federal and regional tax records of each farm investor in the last two decades Gambella was able to shake off the monkey on Gambella’s back quickly and sprint the growth development transformation goal of the region .

  Now Gambella can be a good example for other other regions to practice this major key responsibility , which Public servants must perform by reviewing federal and regional tax records of each investor that was awarded farm lands in the last two decades if the regions also choose to shake off the monkey on their back as Gambella region did and create the much needed job opportunities , the responsibility of mobilizing the public to work is overlooked by many regions governments due to that reason unfortunately many ethnic groups are resorting to creating their own statehood .
  Even Sidama Region should review the tax records of the farm investors before anything , I am sure it will be a shocking revelation an eye opener job creation task that will make identifying investors that actually intend to farm the lands they receive a reality, a very crucial job of the public servants but often remained not being carried out at all bringing the socio , economic and political conflicts that lasted for 20+ years until the new change reform came a couple of years ago.

  The investment activity in Gambella is so impressive the locals are finally getting the chance to earn a living by working for the investors who actually farm the lands , unlike almost all of investors in the years just until a couple of years ago who fenced the lands and leave the lands not farmed year after year for decades stagnating Gambella’s growth all that has changed now since giving lands that actually farm the lands is given the much needed consideration by Gambella region government public servants as it can be done allover Ethiopia abandoning the old ways of corruption land grab for fencing not for farming that was done until a couple of years ago. Looking back at the tax records of each farm investors that were awarded lands in Gambella was the first and most important job Gambella region’s government performed that resulted in the success we see in Gambella region now , learned from the farm investors tax records paid to the region and to the federal of the last three decades was the key since it was found out only a handful and of investors paid appropriate tax money while almost all of the rest paid almost nothing year after year for three decades , now all that is changing since creating jobs for the young is given upmost attention in Gambella this cuting down the youth unemployment rate by half each year for the last couple of years , even South Sudanese refugees are getting job opportunities in Gambella since it is starting to show there are more job opportunities than workers in many areas of Gambella .

 2. Fact : during tamrat layne’s time , meles’s time and hailemariam’s time Amhara “elites” has sold themselves to woyane more than anyother ethnicity in ethiopia.

  now amhara is having the biggest identity crisis , the older generation of amhara has lost their identity and has forced their children and grand children to loose their identity .

  anbessa siyarej yezinib mechawecha yihonal
  yezendrowochu amharawoch siyareju melaw amhara zinib endichawetibet asderegu

  zinib = yetemari student movement generation “elites”

  https://borkena.com/2020/02/06/ethiopian-christians-march-in-addis-as-police-shooting-victims-laid-to-rest/

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.