ኦነግ ለኦሮሞ ህዝብ ምኑ ነው?

ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ, Hagayya 29, 2019

ኦነግን ከኦሮሞ ህዝብ ትግል ማፋታት ከንቱ ድካም ነው። የኦሮሞ ድርጅቶች ሁሉ ለህዝባቸው ነፃነት፣ አንድነት፣ ህልውና እና ክብር ያደረጉት ትግል ሲመዘን የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው። ይህም ከመሠረታዊ ነገር ነው የሚጀምረው።

# የኦሮሞ ህዝብን ማንነት ማጥፋት የተጀመረው ህዝቡ የሚጠራበትን ትክክለኛ ስም በመቀየር ነበር። ገዥዎች “ኦሮሞ” የሚለውን ስም አጥፍተው አፀያፊ ፍቺዎች የሰጡትን ስም በግዴታ በህዝቡ ላይ ጭነው ነበር። ይህንን ሆን ተብሎ የኦሮሞ ህዝብን ለማዋረድ የተደረገውን ሴራ ተዋግቶ ህዝቡ በዓለም ዙሪያ “ኦሮሞ” በተሰኘው ትክክለኛ ስሙ ብቻ እንዲታወቅ ያደረገው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው።

# በታሪክ ሂደት ተበታትነው ወደ መረሳሳት ደረጃ ደርሰው የነበሩትን የምስራቅ፣ የምዕራብ፣ የሰሜንና የደቡብ ኦሮሞዎችን ሙሉእ በሆነ ሁኔታ አንድ ላይ ያሰባሰበው ድርጅት ኦነግ ነው። አሁን ያለው የኦሮሞ ህዝብ አንድነት የኦነግ የስራ ውጤት ነው።

# የኦሮሞ ህዝብ በባህሉ፣ በቋንቋው፣ በትውፊቱና በታሪኩ ሳያፍር ማንነቱን እንዲገልጽና ኦሮሞነቱን በየትኛውም መስክ እንዲያሳውቅ ከማንም በላይ የጣረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው።

# ኦነግ የኦሮሞ ብሄርተኝነት አባት ነው። Orommumaa እና Sabboonummaa የሚባሉትን ጽንሰ ሐሳቦች በመቅረጽ የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ያበለፀገው ኦነግ ነው። ከሰላሳ ዓመታት በፊት ኢብሳ፣ ቶላ፣ መገርሳ በሚሉ ስሞች ልጆቹን መጥራቱን አቁሞ የነበረው ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑ ኦሮሞ ዛሬ ኮራ ብሎ “ሃዊ፣ ቀነኒ፣ ፊራኦል፣ ኦብሰን፣ ሳርቱ” የሚሉ ስሞችን ለልጆቹ እየሰጠ ያለው ኦነግ በቀየሰው መንገድ inspire ስለሆነ ነው።

# ኦነግ “የቁቤ አፋን ኦሮሞ” አባት ነው። አፋን ኦሮሞ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ ምርምር አድርገው ውጤቱን ይፋ ያደረጉት ሼኽ ሙሐመድ ረሻድ እና ኃይሌ ፊዳ ናቸው። እነርሱ ያጠናቀሯቸውን ጥናቶች በማዳበር ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ ያዋለው ግን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው። ኦነግ በሽግግሩ ዘመን ከሰራቸው ስራዎች መካከል ትልቁ አፋን ኦሮሞ የትምህርት ቋንቋ ሆኖ የኦሮሞ ልጆች በቋንቋቸው እንዲማሩ ማድረጉ ነው (በዚህ ረገድ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኢብሳ ጉተማ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል)።
# ኦነግ የዘመናዊው የአፋን ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ አባትም ነው። በቁቤ አፋን ኦሮሞ የተጻፉ የግጥም እና የልብ ወለድ መጻሕፍትን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው ኦነግ ነው። በቁቤ የሚዘጋጁ ጋዜጦችና መጽሔቶችንም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተመው ኦነግ ነው።

# አሁን የስራ ቋንቋ ሆኖ የሚያገለግለውን የተማከለ የአፋን ኦሮሞ ዘይቤንም የፈጠረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው። ለቢሮክራሲ ስራ የሚያስፈልጉና በሂደት ለመጥፋት ተቃርበው የነበሩ የኦሮምኛ ቃላትን ከልዩ ልዩ የኦሮሚያ ዞኖች አሰባስቦ በመዝገበ ቃላት በመሰነድ በመላው ዓለም በሚኖሩ ኦሮሞዎች ዘንድ እንዲታወቁ ያደረገው ኦነግ ነው።

# ኦነግ የዘመናዊው የኦሮሞ የታሪክ ጽሑፍ አባትም ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው የኦሮሚያ ዞኖች ላይ ያተኮረ የታሪክ መጽሐፍ አሳትሞ ያቀረበው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነው (ከዚያ በፊት ይወጡ የነበሩት የታሪክ መጻሕፍት በአንዱ የኦሮሚያ ዞን፣ ወይንም በአንድ የኦሮሞ ነገድ ላይ ብቻ ያተኮሩ ነበሩ)።

# ለመጀመሪያ ጊዜ የገዳ ስርዓትን አተገባበር በተሟላ ሁኔታ የሚተርክ መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ናቸው። የገዳ ስርዓትን በዓለም ዙሪያ በስፋት ያስተዋወቁት ግን በውጭ ሀገራት የነበሩት የኦነግ የውጭ ግንኙነት ቢሮዎች ናቸው።

# ኦነግ ሁሉን አቀፍ የኦሮሞ ጥናት አባትም ነው። በኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ ታሪክ፣ ኢኮኖሚ፣ ቋንቋና የነፃነት ትግል ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበትን ዓለም አቀፍ ኮንፈረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የኦነግ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ነው። በዛሬው ዘመን በዚህ ዘርፍ ተጠቃሽ ሆኖ የወጣው የኦሮሞ ጥናት ማህበር (Oromo Studies Association) የተመሠረተው ኦነግ ሲያዘጋጃቸው በነበሩት ኮንፈረንሶች ላይ ሲገናኙ በነበሩት ምሁራን አማካኝነት ነው።

ኦነግ በነፃነት ትግሉ ዘርፍ ያደረገው አስተዋጽኦ ሲገመገም ደግሞ ከላይ ከሰፈረው በእጅጉ ይበልጣል። ስለዚህ ወደ ዝርዝሩ መግባቱ ለጊዜው አያስፈልገንም። በአጭሩ ግን “ኦሮሞዎች በነገድ፣ በጎሳ፣ በክፍለ ሀገርና በሃይማኖት ሳይለያዩ በኦሮሙማ መንፈስ አንድ ላይ ሆነው በተደራጀ ሁኔታ ለነፃነታቸው እንዲታገሉ የቀሰቀሰ፣ ለትግሉ ያሰማራ እና ያታገለ፣ በዚህም ከኦሮሞ ህዝብ መጠነ ሰፊ ድጋፍ፣ ከበሬታ እና አመኔታ የተሰጠው የመጀመሪያውና ዋነኛው ድርጅት ነው” በማለት ማስቀመጥ ይቻላል። የኦሮሞ ህዝብ የትግል መንፈስ ሳይቀዘቅዝ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ የደረሰው ኦነግ ባቀጣጠለው ጎዳና ላይ በመራመድ ነው።

ይህ ሲባል ግን ግንባሩ ችግር አልነበረበትም ማለት አይደለም። የግንባሩን እንቅስቃሴዎች ሰንገው የያዙ በርካታ ችግሮች ተፈጥረውበታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሰሞን “ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ትግል ውስጥ አንድም አስተዋጽኦ የለውም” የሚሉት ወጀላቴዎች የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ እያስገረመኝ ነው።

ከነዚህ ወጀላቴዎች ጋር ቃላት መመላለስ አያስፈልግም። ለጊዜው አንድ ነገር ብቻ ልወርውርባቸው። ኦነግ የሚባል ድርጅት ባይኖር ኖሮ ኦህዴድ የሚባል ድርጅት ባልተፈጠረ ነበር። ኦነግ ባይኖር ኖሮ ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶችም ባልተፈጠሩ ነበር።

ወደዚህ ደግሞ “ኦነግ 40 ዓመት ታግሎ ለኦሮሞ ህዝብ ምንም አልሰራም” የሚሉ አሉ። በእርግጥም ኦነግ በመሳሪያ ተዋግቶ የአራት ኪሎ ቤተ መንግስትን መቆጣጠር አልቻለም። ይህም የራሱ ምክንያት ስላለው ወደ ዝርዝሩ አልገባም። የዕድሜው ጉዳይ ለሚያስጨንቃቸው ሰዎች ግን “የፍልስጥኤም፣ የኩርድ፣ የቺቺኒያ እና የሌሎች ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ብዙ ዓመት ተዋግተው መቼ አሸነፉ?” እንላቸዋለን።
ከዚህ በተረፈ ኦነግ ብዙ ነገር ሰርቷል።

ወያኔ በነዛው የበደኖ ፕሮፓጋንዳ ላይ ግግም ብለው የኦነግን አራጅነት ሊያስረዱን ለሚፈልጉት ደግሞ “ዓላማችሁ ኦነግን መምታት ሳይሆን ኦሮሞን መጥላት ነው” ብለን እቅጩን እንነግራቸዋለን (የበደኖውን ፊልም ቀርጾ በቲቪ ያሳየው ወያኔ ነው። ኦነግ ሲያርድ ቀራጩ አጠገቡ ነበረ ማለት ነው?)
—-
በመጨረሻም:

የኦነግ ድርጅታዊ ልሳን የሆነው ጋዜጣ “በከልቻ ኦሮሚያ” ይባላል። ይህ ጋዜጣ በአማርኛ ቋንቋ ይዘጋጅ እንደነበረ የምታውቁት ስንቶቻችሁ ናችሁ? አዎን! ግንባሩ እንደሚወራው አማራ ጠል አለመሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል።

Similar Articles

Comments

  1. Akkassi mallee hayuufii gootta koo. Dhugaa haasai, dhugaa katana, dhugaan bulli, nuuf jiraadhu! ኦነግ ኦሮሞ ነው: ኦሮሞም ኦነግ ነው:: የማንንም መብት ሳይነካ የራሱን መብት ለማስከበርና የራሱን እድል ለመወሰን እየታገለ ያለን ይህን ታላቅና ጀግና ህዝብ ለግማሽ ምእተመት ያህል በትግሉ የመራው ድርጅት ኦነግ ነው::

  2. Dhugan jirtu tanuma.wareegama qaaliin firii argamtee akka biqillee hindaraarree beekani taaiti wallaalumani wal faffacaasani diina uufirrati gobsun dhaabatu qaba.kan nu yaadchisu qabu waan kalee godhee odo hintaanee waan amma fi boru gochuu qophaaina godha jiru tauu qaba.ee waan kalee godhantuu utubaafi dagalee taee asiin nu gaee qooda isaan taphatani waakatun uff sobuun diina waan gammachiisan itti fakkata.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...