ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ: የህዝብን ሉዓላዊነት ለድርደር ማቅረብ ህገ-መንግስትንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን መናድ ነው!

ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ: የህዝብን ሉዓላዊነት ለድርደር ማቅረብ ህገ-መንግስትንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን መናድ ነው!

አንደሚታወቀው ሁሉ የሲዳማ ህዝብ ለዚህች አገር ሰላም፣ መረጋጋትና አንድነት የራሱን የታሪክ አሻራ ያኖረና በአንፃሩ ደግሞ በሀገር ግንባታ ህደት ውስጥ ተጋርጦበት የነበረውን ሁለንተናዊ በደልና አፈና በጽናት ስታገል የቆየ ህዝብ እንደሆነ ጠላትም ሳይቀር የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የሀገርቷን ሥልጣን ኮርቻ የሚቆናጠጡ ገዢዎች ሲዳማን ሳይሆን የሲዳማን ሀብት ለመቀራመት ወጥነዉና ይህም ዕቅድ እንዲሳካላቸዉ የህዝቡን ቋንቋ፣ታሪክ፣ ባህልና ማኅበራዊ አሻራ ለመናድ ለትተቀን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ቢሆንም የሀገር ግንባታ ሂደት የማንነት ፈተና በማይሆኑበት መልኩ መስራት ይቻላል የሚል ጠንካራ አቋም ማራመድ የጀመሩት የሲዳማ ቀደምት ታጋዮችና ሰማዓታት በከፈሉት መራር ትግል ላለፉት 28 አመታት ስራ ላይ የዋለው ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት እውን ሆኗል፡፡

ምንም እንኳን የሲዳማ ህዝብ የጭቁን ብሔሮችን ድምጽ አስተጋብቶና ታግሎ ለ1987 ዓ.ም ህገ-መንግስት በታሪክ የማይረሳ አሻራውን ለማሳረፍ ቢበቃም ሲዳማ ምድርን እንጅ የሲዳማ ህዝብን አምርረው በሚጠላው ገዢ መደብ በተጠነሰሰ ሴራ ህዝባችን የህገ-መንግስቱ ትሩፋት ተቋዳሽ እንዳይሆን በዉስን አምባገነን ኃይሎች ታግዶ ሌላ ሰላማዊ የትግል ምዕራፍ እንድጀምር ተገዶአል፡፡ በገዛ ሀገሩ ወደ ዳር የተገፋ ሰፊው የሲዳማ ህዝብ በደሙና አጥንቱ በተጻፈው ህገ-መንግስት እያለም ለሞት፣ ለስደትና ለእስራት ሲዳረግ ቢቆይም ቅሉ ህዝብን ለትግል ከመትጋት ያገደው አልነበረም፡፡

ስለሆነም ትውልድ ስቀባበል ቆይቶ ለዚህ ዘመን ትውልድ የደረሰው የትግል ችቦውን ላለፉት ሁለት ዓመታት ታዓምራዊ ክስተት በሲዳማ ምድር አሳይቷል፤ የሰማዓታት አጥንትን የሚያኮራና የዓለምን ማኅበረሰብ የሚያስደምም ዴሞክራሲያዊ ትግል ተካሂዷል፤ በውጤቱም ህዝባችን በፖለትከኞች ሴራ ስጠመዘዝ የነበረውን እራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ በክልል የመደራጀት ጥያቄን በህዝብ ይሁንታ እንዲረጋገጥ ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡
በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 47 ላይ በዝርዝር የተቀመጡ ተግባራት ከብዙ ፈተናዎች ሲጠላለፍ ቆይቶ በህዝባችን ብርቱ ትግልና አጋሪነት ተፈጻሚ ሲሆን አሁን የቀረው ከነባሩ ክልል ም/ቤት ስልጣን የማስረከብ ተግባር ብቻ ነው፡፡ ሉዓላዊ የሆነው ህዝብ ድምጹን ሰጥቶ የሚገባውን ካደረገ በኋላ ቀሪውን ህገ-መንግስታዊ ጉዳይ ገቢራዊ ከማድረግ ረገድ ከመንግስት አስፈጻሚዎች የጣልቃ ገብነትና የቁርጠኝነት ማነስ ምልክት ከመታየቱም በላይ ከህገ-መንግስቱና ከሉዓላዊ ህዝብ በላይ በመሆን ስለ ህዝብ ጉዳይ ለመደራደር የሚሞከረሩ አዝማሚያዎችም እየታዩ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም ህገ-መንግታዊ ስርዓትን ተከትሎ በህዝባችን ተሳትፎና ዉሳኔ ይሁኝታ ያገኘዉን የሲዳማ ብሔር በክልል የመደራጀት ጉዳይ በፖለቲካዊ እና በጎንዮሽ ድርድር ለመተካት የሚደረገው ሙከራ የሰፊውን የሲዳማን ህዝብ የሚንቅ ተግባር በመሆኑ ድርጅታችን አጥብቆ እየተቃወመ ከዚህ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡-

1ኛ. በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ስልጣን የተሰጠው የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከዚህ በፊት ህዝብን ወክሎ ህገ-መንግስት ያጎናጸፈውን ስልጣን በነጻነትና በጊዜ ገደብ ባለመፈፀሙ ምክንያት በአካባቢያችን ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ትምህርት ወስዶ ዳግም ለታሪካዊ ስህተት በማይዳርገው መልኩ ስልጣንን ለብሔሩ ም/ቤት በሚቀጥሉ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲያስረክብ አበክረን እያሳሰብን ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ህዝባችን ላይ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ቀዳሚ ተጠያቂ እንደሚሆንም ጭምር እናሳውቃለን፤

2ኛ. በህገ-መንግስቱ ላይ በግልጽ በተቀመጠዉ አኳኋን ከህዝበ-ውሳኔ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ፖለቲካዊና የጎንዮሽ ድርድርን ድርጅታችንና ህዝባችን አጥብቆ የሚያወግዘው፣ የሚቃወመዉና በሰላማዊ መንገድ የሚታገለውም እንደሆነ ይገልጻል፤

3ኛ. ታሪካዊና ብዙ ዋጋ ያስከፈለ የህዝብ ጥያቄ ከግብ ደርሶ ህዝባችን የሚገባውን ክብር ሳያገኝ ለስልጣንና ለተለያዩ ጥቅሞች የህዝባችንን አንድነት ፈተና ለመሆን የሚጥሩ ግለሰቦች ከዚህ ከጸረ-ህዝብ ድርጊታቸዉ እንዲትታቀቡ አጥብቀን እናስጠነቅቃለን፤

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን)
ጥር 18 ቀን 2012 ዓ/ም
ሀዋሳ/ ኢትዮጵያ

ማለዳ ሚዲያ

2 Comments

 1. ONCE AGAIN AS ALWAYS ADDIS ABABA PEOPLE ARE DOOMED TO STAY PERMANENTLY DENIED FROM HOLDING PROTEST UNDER PROSPERITY PARTY. THE PROTEST ABOUT ABDUCTED GIRLS GOT DENIED BY PM ABIY AHMED.CLAIMING AFRICAN UNION SUMMIT WHICH IS A WEEK AWAY WILL BE DISRUPTED BY THE PROTEST SCHEDULED TO BE HELD A WEEK EARLY.

  ORTHODOX CHURCH , BALDRAS , ADDIS ABABA UNIVERSITY STUDENTS …. ARE DENIED PROTEST PERMITS BY PROSPERITY PARTY.
  IT IS TIME FOR ADDIS ABABA PEOPLE TO START NON VIOLENT RESISTANCE (NVR) AGAINST PROSPERITY PARTY PP BY STAYING HOME FOR ONE DAY OR MORE DAYS AND DIASPORAS SHOULD START CAMPAIGN TO BOYCOTT SENDING REMITTANCE MONEY FROM DIASPORA UNTIL HUMAN RIGHTS OF ETHIOPIANS SUCH AS ADDIS ABABA PEOPLE’S FREEDOM OF EXPRESSION IS RESPECTED .

  https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/የራሳቸውን-ሀይማኖት-በሚያስፋፉ-ባለስል/

 2. Sorry to be the bearer of a bad news but the Federal government is not going to intervene in Sidama province state government and Hawaassa
  City government’s lack of professionalism in f anything OPDO wants to sabotage Sidama State anyway it can , because in a closed meeting OPDO has decided it is a good idea if the Sidama State / Hawaassa people fail miserably being a lesson for other ethnicities not to ask for their own self administration statehood, that way other ethnicities such as Kunama , Kaffaa , Wolaita …. reverse their demand to be granted a referendum for their self administration statehood , even if a referendum is granted after real chaos and deficit is seen in Sidama state /Hawassa city OPDO is hoping in the future other ethnic people will vote against having their own statehood.

  http://ayyaantuu.org/ከሲዳማ-አርነት-ንቅናቄ-የተሰጠ-መግለጫ-የ/

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.