ከነባር የፊንፊኔ ኦሮሞ ተወላጆች የተሰጠ ማሳሰቢያ!

July 11, 2019

ፊንፊኔ ከአመሰራረቷ ጀምሮ በእኛ በነባር የኦሮሞ ልጆችን እና የኦሮሞን አርሶ አደሮች ደምና አጥንት ላይ ግፍ እየተሰራ መመስረቷን እንኳን የኢትዮጲያ ህዝብ ቀርቶ የአለም ታሪክ በገሀድ ያውቀዋል።

በተለይ በሀገራችን ጭቁን የኩሽ ህዝቦች ላይ ለዘመናት የቆየ መሬታቸውን ፣ ቋንቋቸውን ፣ ባህላቸውን እንዲሁም በአጠቃላይ ማንነታቸው ላይ ያተኮረ ዘረፋና ግፍ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም ግን በግዜ ሂደት ወደ 10ሺዎች የሚቆጠሩ ቄሮዎችን ገብረን አንጻራዊ የለውጥ ተስፋ ሰንቀን ጥያቄዎቻችን እስኪመለሱ ድረስ በትህግስት በመጠባበቅ ላይ ሳለን ፤ በቄሮ ደም ላይ ቆሞ የሚቀልድና በደማችን ላይ የሚሳለቅ እራሱን “የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት” ብሎ የሚጠራ በእስክንድር ነጋ የሚመራ መንግስት ነኝ ብሎ ሲመጣ በጥንቃቄ በመከታተል ላይ እንገኛለን።

በአንድ ሀገር ውስጥ አንድ መንግስት እንጂ ሁለት መንግስት ሊኖር አይችልም። በፕሬዝዳንት ማሜ የሚመራው ሌላ ” የፊንፊኔ ባላደራ ” መፈጠሩም ይታወቃል።ስለዚህ መንግስት በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት መንግስት ሲፈጠር እርምጃ ሳይወስድ ዝምታን ከመረጠ! እኛ ነባር የፊንፊኔ ኦሮሞች 3ኛ የፊንፊኔ ባላደራ ሆነን በቅርብ ለህዝባችን መግለጫ ለመስጠት የምንገደድ መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን።

ይህን ስንል ትክክለኛ አካሄድ ነው ብለን ሳይሆን ፥ የመንግስት እያሳየ ያለው ትህግስት እና ዝምታ ስላልተዋጠልን ጭምር ነው።በማንኛውም ግዜና ሰዓት አሁን ካለው ከከተማው መስተዳድር ውጪ የከተማው መንግስት ነኝ የሚሉትን አካላት ላይ ህጋዊ ክልከላ ወይም እገዳ ካደረገ እኛም ነባር የፊንፊኔ ኦሮሞች አላስፈላጊ የሆነ ህዝብን የማወዛገብ ስራ እጃችንን እንደምናነሳ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ከጥቂት ሳምታት በኃላ ማሳሰቢያችን መልስ የማያገኝ ከሆነ በሚዲያ ወጥተን መግለጫ ለመስጠት እንደምንገደድ ለማሳወቅ እንወዳለን።በማንኛውም መንገድ ህግና ስርዓት እንዲከበር ከመንግስት ጋር በጋራ ለመስራትም ዝግጁ ነን።

#ነባር_የፊንፊኔ_ኦሮሞች_ባላደራዎች
Haaromsa Finfinnee

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...