የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው

የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው

(የኦነግ መግለጫ – የካቲት 14, 2012)

Ajjeechaa ABO Mirga Resolutions of the Oromoo Liberation Front National Councilየክስተቱን መንስዔና አጠቃላይ ምንነቱን አስመልክቶ እስካሁን በቂ ግንዛቤና መረጃ ባይኖረንም እንኳ በትናንትናዉ ዕለት (የካቲት 13, 2012) በቡራዩ ከተማ የተፈጸመዉንና የኮሚሽኔር ሰለሞን ታደሰ ሕይወት የጠፋበትን ግድያና የአካል ጉዳት ያደረሰዉን ጥቃት በጽኑ እናወግዛለን። በጠፋዉ ሕይወትና በደረሰዉ አካላዊ ጉዳት ለተጎዱትም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

በእንዲህ መሰሉ ጥቃትም ይሁን በሌላ በምንም መልኩ የተወሰኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ዒላማ አድርጎ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አላስፈላጊ ጫናዎች የሀገሪቱን ችግሮች ይበልጥ ያባብሱና ያወሳስቡ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣሉ ብለንም አናምንም። በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ መንገዶች እየታዩ ላሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ሁሉ ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ መንግሥት ከፍተኛዉን ድርሻና ኃላፍነት እንዳለዉ ይታወቃል። የዚህች ሀገር የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉም ይህንን አስመልክቶ የድርሻቸዉን ለመወጣት ግዴታ አለባቸዉ። ሰፊዉ ሕዝብም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሕዝብ የተጋረጡብንን ችግሮች በተመለከተ የችግሮቹን መንስዔና መፍትሄያቸዉን ለይቶ ያሉብን ችግሮች ለዘለቄታዉ መፍትሄ በሚያገኙበት አቅጣጫ ላይ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ በንቃት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነዉ ብለን እናምናለን።

ስለሆነም፣ ባሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ አስፈሪና ዘግናኝ የሆነ የስጋት ደመናን አንዣቦ ያሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ልያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ለማፈላለግ ሁሉም ወገኖች ኃላፍነትና ግዴታቸዉን በላቀ የተጠያቂነት/responsibility መንፈስ እንዲወጡ ኦነግ አጥብቆ ይማጸናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግሥት የዜጎች ነፃነትና ደህንነት ልረጋገጥበት የሚችለዉ ሁለንተናዊ መፍትሄ ልገኝ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደመንግሥት የተረከበዉን ታሪካዊ ኃላፍነትና ተጠያቂነት መወጣቱ የወሳኝነት ሚና እንዳለዉ ተገንዝቦ ይህንን ኃላፊነቱን በገንቢ ሁኔታ እንዲወጣ በአፅንዖት እናሳስባለን።

ድል ለሰፊዉ ሕዝብ !
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
የካቲት 14, 2012

2 Comments

 1. ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው የአሃዳውያን እናውቅላቸዋለን የንቀት እና የዘረኝነት ፖለቲካ በህግ ሲታገድ እና ሁሉም ህዝቦች ያለ ማንም ሌላ ህዝብ ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ሀቀኛ ፌዴራላዊ ስርኣት ስር ሲሰድ ብቻ ነው። የፌዴራሉን ስርአት የሚቃወሙ ሃይሎች አማርኛ ተናጋሪ አሃዳውያን ብቻ ናቸው። እነዚህ ሀገራችንን እና ህዝቦቻችን ለዘመናት ሲያደሙ እና ሲግጡ የከረሙ ነፍጠኞች አይኔቸውን በጨው ታጥበው በኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ላይ እያላገጡ ይገኛሉ።
  በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣
  የትምህርት፣ እና የቅርስ ድርጅት
  (UNESCO) በኣለም ቅርስነት የተመዘገበ የገዳ ፖለቲካ ስርኣት ባለቤት የሆነውን የኦሮሞ ህዝብ ከገዳ ፖለቲካ ውጭ በነፍጠኞች ህግ ትገዛለህ ማለት በግልፅ ቋንቋ ባርነት
  ይሻለዋል ማለት ነዉ።
  ኢትዮጵያ ውስጥ የአሃዳዊ ስርኣት ናፋቂዎች የነፍጠኞች ርዝራዦች እና በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ፎቢያ ያለባቸው የጉራጌ ባለሀብቶች መሆናቸው እርግጥ ነው። የጉራጌ ሊህቃን ከኤርትራ ተማርከን ወደ ኦሮሞ ቀጠና ስለመጣን በኤርትራ ታግዘን ፌዴራልዝሙን እንቀይራለን የሚል የተሳሳተ አቋማቸው የትም እንደማያደርሳቸው ማስተዋል አለመቻላው የሚያሳዝን ነገር ነው። የብልፅግና ፓርቲ መስራቾች ስለ ሀቀኛ ፌዴራልዝም በኢትዮጵያ ውስጥ የተነሳሳውን ሰላማዊ የህዝቦች ትግልን በተለይ የቄሮን ጥያቄ
  አቅጣጫ ለማሳት በሚሊዮን የሚቆጠር ኦሮሞን ባፈናቀሉበት ወቅት የጉራጌ ልሂቃን ከጉራጌ ባለሀብቶች 50 ሚሊዮን ብር አሰባስበው በእነ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ አማካኝነት 2000 መጠለያዎችን ለኦሮሞ ተፈናቃዮች እንሰራለን ሲሉ ለፕሮፓጋንዳ ላይሆን ይችላል ብዬ በጥርጣሬ መከታተል አለብን ብዬ መክሬ ነበር።
  አይደለም ዛሬ በዚህ በቴክኖለጂ በተራመደ ዘመን ጥንት እንኩዋ ድንጋይ የማናገር አቅም

 2. ባለን ቃሉዎች የበላይ ጠባቂነት የሚመራው የኦሮሞ ህዝብ በእጅጉ ጥንቁቅ ህዝብ መሆኑን መዘንጋት ታሪክን መዘንጋት ይሆናል። ዛሬ ሀቀኛ የአማራ ልሂቃን የኦሮሞን ህዝብ ትግል በሚደግፉበት ዘመን በኦሮሞ ውስጥ ተወልደው ያደጉ እነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ዶክተር አብይ አህመድ፣ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከጥንቱ ነፍጠኞች የተሻሉ አሃዳውያን ለመምሰል መዳከራቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው።
  አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ወደ አረብ ሀገር ከመላካቸው ከሳምንታት አስቀድመዉ OBN ለተባለው የብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ አንሃዱፉ ፕሮግራም ቃለመጠይቅ በ1984 ክልላዊና ብሄራዊ ምርጫ ወቅት ኦ.ነ.ግ. 3 ሚሊዮን እጩዎችን በማቅረቡ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. በኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈፀም በመዘጋጀቱ እና ይህንንም ለኦ.ነ.ግ. አመራር በግልፅ በማወጁ ኦነግ ተገፍቶ ከሽግግር መንግስት መውጣቱን አምኗል። በወቅቱ በበረው የሽግግር መንግስት ዉስጥ ከ12 የኦነግ የፓርላማ አባላት አንዱና የኦሮሞ ህዝብንና ትግሉን ሲያስጠቃ የነበረው አቶ ሌንጮ ለታ ስለ በደኖ እልቂት ተጠይቆ ኦነግ ድርጊቱን ያልፈፀመ እና ከትግራይ ሀገር ድንጋይ ከጉራጌ ቆጮ አላጋዘም በማለት ማስጠቃቱን ታሪክ ይመሰክራል።
  ዛሬም የኦሮሞ ህዝብ በተመሳሳይ የታሪክ አጋጣሚ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት፣ጥቂት ጡት ነካሽ አስጠቂ ልጆቹም በገሃድ የሀሳዊ መሲህ (መሲሁ ደጃል) ቅጥረኞች ሆነው እያገለገሉ ቢሆንም እውነት ምንም ጊዜ ቢሆን እውነት ስለሆነች ሀቀኛ የኦሮሞ ልጆች ከሀቀኛ የትግራይ፣ የአማራ፣ የአፋር፣ የሶማሌ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ፣ የወላይታ (የኦዳ ቅጠል በል)፣ የጋምቤላ፣ የበኒ ሸንጉል-ጉምዝ፣ የአገው (አዊና ዋግ)፣ ስልጤ፣ ጋሞ፣ …ወዘተ ሁሉም ሀቀኞች ጋር ሁሉንም እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ የፌዴራል ስርኣት መዋቅርን እናጠናክር።

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.