የራስን ጥፋት ለመደበቅ የኦነግን ስም ማጥፋት ከተጠያቂነት አያድንም

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር, Ebla 5, 2019

Ajjeechaa ABO Mirga Resolutions of the Oromoo Liberation Front National Councilየኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን አስተዳደር የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ
ኦነግ በመግለጫው የአማራ ክልል መንግስት ወሰን ለማስፋፋት እና ለድብቅ አላማ የክልሉን ልዩ ፖሊስና ከመከላከያ ሰራዊት የተቀነሱ በቁጥር 100 የሚደርሱ የቀድሞ ወታደሮችን ከኦሮሞ ልዩ ዞን አስተዳደር እውቅና ውጪ ዳዌ ሀራዋ እና ሪቄ በሚባሉ ወረዳዎች በማሰማራት በቀኤያቸው በሰላም በሚኖሩ ህዝቦች ላይ ጥቃት በመክፈት የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት እየተጋፋ ይገኛል ብሏል።

እነዚህ ሀይሎች ዝግጅት ላይ በነበሩት ጊዜ እና ጥቃት ማድረስ በጀመሩበት ወቅት ይዘው የሚንቀሳቀሱት ባንዲራ የፌደራል መንግስት አሊያም የክልሉ መንግስት ሳይሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሀይሎች ባንዲራ መሆኑ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ያለውን ትንኮሳ የበለጠ አስጊ የሚያደርግ መሆኑን መገንዘቡንም ነው ግንባሩ ያስታወቀው።

የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ በትናንትናው እለት ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫም በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ስም የሚንቀሳቀሱ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች የሚወስዱትን እርምጃ ህጋዊ ለማስመሰል የችግሩን መንስኤ ወደ ኦነግ በመቀሰር በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እየሰራ ያለውን ድርጅት ለመወንጀል መሞከራቸውንም በመግለጫው አንስቷል።

አሁን በአማራ ክልል የኦሮሞ ልዩ ዞን የተከፈተው ዘመቻ መነሻ ለሀገሪቱ ህግና ስርዓት የማይገዙ ሀይሎችን በማሰማራት የዞኑን ሰላም በማደፍረስ ህጋዊ የሆነውን ዞን አፍርወስ ወደ ሌሎች ዞኖች መቀላቀልና ወሰንን ለማስፋፋት የሚደረግ ሴራ ነው ብሎ እንደሚያምንም ኦነግ አስታውቋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የኣማራ ክልል መንግሰት ልዩ ሀይል እየወሰደ ያለው እርምጃ በሰላማዊ መንገድ የራሱ ቀኤ ላይ የሚኖር ህዝብ ላይ የተወሰደ እና ህግን የጣሰ ነው ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል።

ለደረሰው ጉዳትም ተጠያቂ የሚደረገው የክልሉ ልዩ ሀይል እና ክልሉን የሚያስተዳድር መንግስት ያሳሰበው ግንባሩ፥ የአማራ ክልል መንግስትም በሀሰት የኦነግን ከመወንጀል እና ስም ከማጥፋት እንዲቆጠብ ጠይቋል።

በመጨረሻም የአማራ ክልል መንግስት በአካባቢው የተከሰተውን ችግር በሰከነ መልኩ እንዲፈታ የጠየቀ ሲሆን፥ የፌደራል መንግስትም ጉዳዩ ወደ ሌላ አቅጣጫ ከማምራቱ በፊት እንዲቆጣጠረው አሳስቧል።

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...