የባህር ዳሩ ኣስቸኳይ ሚስጥራዊ ስብሰባ ተጠናቀቀ
Via Rundassa Eshete, Jan 17, 2020

የዛሬ ዓመት ገደማ የተካሄደውን የኣ/ኣበባ የኢሌሌ ሆቴል ሚስጥራዊው የነ ደመቀ መኮነን የጥፋት ስብሰባ ላለፉት 2 ቀናትም በባ/ዳር ቀጥሏል ። ችግሩ ኣሁንም ሚስጢርነቱን ኣልጠበቀም ።
በደመቀ መኮነን መሪነት የመከላከያ ፥ የምርጫ ቦርድ እና የሕግ ኣውጪው ኣካላት ብቻ በተገኙበት ለ2 ቀናት ማለትም (ጥር 4 -5/2012 ዓ/ም) በባህ/ዳር ሲካሄድ የቆየው ሚስጥራዊ ውይይት የሚከተሉትን ውሳኔዎችን በመመሪያ መልክ ኣሳልፏል።
- ኣገራዊ ምርጫ የኛ ፓርቲ (ብልፅግና ፓርቲ ማለታቸው ነው) ውጤታማ እንዳይሆን ከወዲሁ እንቅፋት በሆኑ ኣካባቢዎች “የስጋት ቀጠና” በማለት በፈረጅናቸው በሙሉ (የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ፥ ሲዳማ እና የወላይታ ዞኖች) የበለጠ ኣጥብቀን እንሰራለን፡፡
- መከላከያ ሰራዊት በዋናነት ኣ/ኣበባን ጨምሮ ኦሮምያ ክልል በሙሉ ፥ ኣማራ ፥ ሶማሌ ክልል ፥ ዓፋር እና ደቡብ ክልል በተለየ መልኩ በመከላከያ ሰራዊቱ ስር እንዲሆኑ በማድረግ ኣጥብቆ መስራት ኣለብን። በኬንያ ምርጫ ያጋጠመ መሰል ችግር በኛ ላይም እንዳይደገም ከወዲሁ መጠንቀቅ ኣለብን፡፡
- ተጨማሪ የውጭ ሃይል ድጋፍ እንዳለን ኣሁንም በሚስጥር መያዝ ይጠበቅብናል፡፡ በሰራዊቱ መካከል ችግር እንዳይገጥመን ኣሁንም ኣሁንም ስምሪቱን ከቦታ ቦታ ማዟዟር እና ብርጌድ መቀላቀል ፥ ቀጥተኛ ግኑኝነት ያላቸው የመከላከያ ኣመራር ኣባላት ማለያየት ፥ ከህዝቡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የፀጥታ ሃይሎች (የክልል ልዩ ኃይሎች ማለት ነው) በኣንፃራዊ ኣከባቢ መሃል ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ለምሳሌ በኦሮሚያ ክልል የኣማራ ልዮ ኃይልን የመከላከያ ደምብ ልብስ ኣስለብሰን ማሰማራት ኣለብን፡፡
- በኣገር ኣቀፍ የዳኞች ቦርድ ሰብሳቢ ፥ ኣለም ኣቀፍ የሕግ ኣማካሪዎች ፥ ስቪል ማህበራት ፥ ሚድያዎች ፥ የሰብኣዊ መብት ተሟጓቶች እና የውጭ ታዛቢዎች ሁሉ የኛው ናቸው። ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ግዜና እኛን በሚቃረኑ ሕጎች ላይ ባፋጣኝ ማስተካከያ እንዲደረግ ካሁኑ ማመቻቸት ኣለብን።
- ምርጫ ቦርድ ለፓርቲያችን ስኬት ሲባል የምርጫ ግዜ ገደብ ከመደበኛው ከ5-6 ወር እንዲራዘም መስራት ኣለበት፡፡ ቀኑ እስኪደርስ እንያንዳንዱ እርምጃችን ስኬታማ ማድረግ ኣለብን፡፡ በምንራመድባቸው መንገዶች እንቅፋት የሚሆኑ ኣካላት ፥ ተቋማት ፥ ግለሰቦች መጥረግ ግድ ይለናል፡፡ የሚሉ 5 ኣስቸኳይ ውሳኔዎች መወሰናቸውን ታውቀዋል፡፡
ፍልፍል ልፍዓተይ ተስፋ ወክዕዖ