የአማራ ጎራ (Amhara Camp) vs የኦሮሞ ጎራ (Oromo Camp) – ተመሳሳይነታቸውና ልዩነታቸው

ብርሃኑ ሁንዴ, 5 ሚያዝያ 2019

ባጠቃላዩ ሲታይ ይህ ጉዳይ ከተነሳ ብዙ ማለት ይቻላል። ይሁን እንጂ በዚህ ርዕስ የተነሳውን ባጭሩ ለመመልከት እስቲ የሁለቱን ክልላዊ አስተዳደርና የሁለቱንም ብሔሮች የፖለቲክ ንቅናቄን እንይ። ለዚህም ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት ድርግጅቶች ከአማራ ጎራ አማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አዴፓ) እና አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሲሆኑ ከኦሮሞ ጎራ ደግሞ ኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ናቸው።

የሁለቱ ክልሎች ብሔራዊ  አስተዳደር ድርጅቶች አዴፓ (ADP) vs ኦዴፓ (ODP)

አዴፓ በአማራ ፍላጎትና ብሔራዊ ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ያለው ድርጅት ሲሆን፣ በዚህ ጉዳይ ላይ አይደራደርም። በመሆኑም ከአብን ጋር እጅና ጏንት ሆነው በጋራ እየሰሩ እንደሆነ ብዙ ማስረጃዎች አሉ።  በተቃራኒው ግን  ኦዴፓ የኦሮሞ ጥያቄ ከተነሳና መልስ ካገኘ አገሪቷ እንድትበታተን ያደርጋል በሚል ፍራቻ ስልጣንም እያለው በሱ አመራር ስር አንድም የኦሮሞ ጥያቄ መልስ አላገኙም። ኦዴፓ እና ኦነግ በጋራ መስራት ቀርቶ አንዱ ሌላውን ለማዳከም እንደሚሰሩ የማይታበል ሀቅ ነው። እንደ አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ ኦዴፓ የኦነግ ክንፍ የሆነውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን (WBOን) ትጥቅ ለማስፈታት እያደረገ ያለው ጥረት ጥሩ ማስረጃ ነው። አዴፓ ግን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አብንን እያስታጠቀ እንደሚገኝ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በሌላ በኩል የአማራ ክልል አስተዳደር የክልሉ ልዩ ፖሊስ እያለ በደንብ እያደራጀና እያስታጠቀ ሲገኝ፣ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ግን የታጠቀውንም ትጥቅ እያስፈታ ወይንም ደግሞ በደንብ እንዳይታጠቁ እያደረገ ነው።

የሁለቱ ክልሎች ብሔራዊ ድርጅቶች አብን vs ኦነግ

ኦነግ በአማራዎች ወይም በኢትዮጵያኒስቶች ጎራ እንደ አገር ገንጣይ ድርጅት ወይም ግንባር ይታይ እንጂ፣ የየትኛውንም ሕዝብ፣ ብሔርና ብሔረ ሰብ መብት ሳይነካ ለብሔሩ (ለኦሮሞ) መብት መከበር የሚታገል ሀቀኛ ድርጅት ነው። በተቃራኒው ግን አብን ለአማራ ብሔር የቆመ ድርጅት ይምሰል እንጂ የትግል ዓላማው በተዘዋዋሪም ቢሆን የዚህን ብሔር የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚሰራ ንቅናቄ እንደሆነ ይህንን የሚያመላክቱ ብዙ ነገሮች ይታያሉ። ኦነግ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ይህ የተፈጥሮ መብታቸው በመሆኑ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረ ሰቦችና ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወስኑ የሚታገል ድርጅት ነው። አብን ግን በሕገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠውን ይህንን መብት የሚቃወምና እንዲያውም የድሮውን ስርዓት ለማስመለስ የሚታገል ንቅናቄ አንደሆነ የሚካድ አይመስለኝም። ኦነግ ለኦሮሞ መብት ከመታገል ውጪ ድንበር ኣልፎ ሌላውን ለመግፋት የሚታገል ግንባር አይደለም። አብን ግን ከአማራ ክልል ድንበርም ዘሎ ሌላውም የኛ ነው እያለ ፕሮፓጋንዳ የሚያደርግ ድርጅት ነው። እንዲያውም የሚገርመው የሸዋ ኦሮሞ በሞሉ Oromized ሆነው ነው እንጂ አማራ ናቸው ይላል። ፊንፊኔ የአማራ መሬት ነው። ስሙም በረራ ነው ይለናል።

ተመሳሳይነታቸው

ተመሳሳይነታቸው ሁሉም ድርጅቶች ለክልሉ ሕዝቦች እንቆማለን በማለት የብሔሮችን ስም መያዛቸው ነው። ኦነግና አብን የየክልሎቻቸው ብሔርተኝነት እንዲያድግ የሚታገሉ ናቸው። ከዚህ የቀረ ምንም የጋራ የሆነ ነገር የላቸውም ቢባል ከእውነት መራቅ ወይንም ነገር ማጋነን አይሆንም።

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...