የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በጠመንጃ ኣፈሙዝ ማፈን ትላንት ኣልተቻለም፡ ዛሬም ኣይቻልም !

(የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ – ሓምሌ 05, 2018ዓም)

Resolutions of the Oromoo Liberation Front National Councilሰሞኑን በኦሮሞ ነጻነት ድምጽና በተለያዩ ሚዲያዎች ስንገልጽ እንደቆየነው በወያኔ መንግስት ታቅዶ በኦነግ እንቅስቃሴና ባጠቃላይ በኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ላይ በኣዲስ መልክ የጦርነት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም በምዕራብ ኦሮሚያ በኩል በመላው ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እንዲሁም በቄሌም ወለጋ ውስጥ “ለምን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንቅስቃሴን ትደግፋላችሁ?” በሚል በኦሮሞ ህዝብ ላይ ኣሰቃቂ እርምጃ ወስደው ትግሉ እንዲገታ ለማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር ሃይል ግዳጅ ወስዶ ከላይ በተጠቀሱት ኣካባቢዎች ውስጥ ስምሪት መጀመሩ ታውቋል።

ይህ ዘመቻ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት(ኣቶ ለማ መገርሳ) ትዕዛዝና እውቅና እንድሁም በጄኔራል ገብሬ ዲላና ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ቀጥተኛ ኣዝማችነት የሚመራ መሆኑም ታውቋል። ጄኔራል ገብሬ ዲላ የትግራይ ብሄር ተወላጅ ሲሆን በምስራቅ ኦሮሚያ በኩል የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይልን በማደራጀትና በማስታጠቅ በኦሮሞ ላይ ሲካሄደ የነበረውንና ኣሁንም በቀጣይነት እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲመራ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ሁሉም እያየና እየሰማ እንዳለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምስራቅ ኦሮሚያ በኩል በሶማሌ ልዩ ሃይል በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በኣዲስ መልክ ተጠናክሮ በመቀጠል እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ (በተለይ በባቢሌና ጭናክሰን ኣካባቢዎች) ህዝቡንና ከብቶቹን በእሳት እስከማጋየት ተደርሷል። በኢትዮጵያ መንግስት፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ይሁን በኦፒዲኦ በኩል እስከ ኣሁን ድረስ ይህንን በህዝባችን ላይ የተከፈተውን ጦርነት መከላከል ይቅርና እስከ ኣሁን ድረስ ይህንን ጉዳይ እንደችግር እንኳ ኣንስተው በመናገር ላይ ኣይደሉም።

የለማ መገርሳ ኣስተዳደርና ኦፒዲኦ በኣንድ በኩል ስለለውጥና ተሃድሶ እያወራና ሕወሃትን የሚኮንኑ መስለው ወደ ኦሮሞ ህዝብ እየቀረቡ በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በግልጽ የዘር-ማጥፋት ዘመቻ ሲያካሄዱ ለነበሩት እንደነጄኔራል ገብሬ ዲላ ሙሉ ስልጣን ሰጥተው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያሰማሩ ነው። ዛሬ በተሃድሶና በለውጥ ስም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትንም ሆነ የፌዴራሉን መንግስት የሚመሩት ግለሰቦች ወደ ስልጣን እንዲመጡ የረዳቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና ወታደራዊ ሃይሉ(የኦሮሞ ነጻነት ስራዊት)፣ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞና የኦሮሞ ልጆች ባጠቃላይ ከምስራቅ-ምዕራብ፣ ሰሜን-ደቡብ በጋራ ለነጻነታቸው ሲሉ የከፈሉት መስዋዕትነት መሆኑ ማንም ሊክደው የማይችል እውነታ ሆኖ ሳለ፡ እነዚህ ሰዎች የኦሮሞ ነጻነት ትግልና ኦነግን ብቻም ሳይሆን ለኦሮሞ ህዝብ ህልውና ከፍተኛ ጠላታዊ ስራ መስራታቸውን መቀጠላቸው በጣም ኣሳዛኝና ኣሳፋሪ ተግባር ነው።

መላው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣባላትና ደጋፊዎች፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስትና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጦር፣ የደህንነት፣ የፖሊስና የኣስተዳደር መዋቅር ውስጥ እንዲሁም በተለያዩ ሙያዊ ስራዎች ላይ የተሰማራችሁና በኦፒዲኦ ድርጅት ውስጥ የምትገኙ የኦሮሞ ብሄርተኞችና ባጠቃላይ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ይህንን እውነታ በመገንዘብ ይህንን ዘመቻ በከፍተኛ ቆራጥነት መጋፈጥ የወቅቱ ኣንገጋቢ ጥያቄና ከፍተኛ የታሪክ ግዴታ ነው። እንደህዝብ ተነጣጥሮ ሲካሄድብን ዛሬን የደረሰውንና ኣሁንም በኣዲስ መልክ በቀጣይነት እየተካሄደብን ያለውን ይህንን ጦርነት ከያለንበት ለወገናችን በመድረስ ኣክሽፈን ነጻነታችንን ከእጃችን ለማስገባት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በወኔና በቆራጥነት መንቀሳቀስ ሌላ ኣማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በኣጽንዖት መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው !
ድል ለኦሮሞ ህዝብ !
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ሓምሌ 05, 2018 ዓ ም

Similar Articles

Comments

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...