የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሁለት

የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?
ሁለተኛ ዙር፥ ክፍል ሁለት

ብርሃኑ ሁንዴ, Ebla 18, 2019

jira
በሁለተኛ ዙር ክፍል አንድ ፅሁፍ ውስጥ ለውጥ መጣ እንጂ የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ከግቡ አንዳልደረሰ፤ በዚህ በመጣው ለውጥ ውስጥ የኦሮሞ ጥያቄዎች መልስ አንዳላገኙ፤ እንደዚሁም በክልሎች ላይ ተመስርቶና ተቋቁሞ የሚገኘው የፌዴራል ስርዓት ምን ሊሆን እንደሚችል ጥያቄ አንስቼ፣ ግን ይህንን ጉዳይ በሰፊው እንደምመለስበት መጥቀሴ የሚታወስ ነው። በዚህኛው ክፍል ሁለት ፅሁፍ ውስጥ አሁን ስላለው የፌዴራል ስርዓትና እንዲሁም ስለ ተለያዩ ጉዳዮች ኣንዳንድ ሀሳቦችን አቀርባለሁ።

አሁን ያለው የኢትዮጵያ የፌዴራል ስርዓት ሊፈርስ ይሆን?

በብሔሮችና ብሔረ ሰቦች ክልሎች ላይ ተመስርቶ ያለው የፌዴራል ስርዓት የኦነት ፀር የሆኑት ኃይሎች እንደሚሉት በወያኔዎች የተሰጠን ስጦታ ሳይሆን ኦነት ካስገኛቸው ድሎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ነው። ይህም ስንት የሰው ሕይወት የጠፋበት፤ ደም የፈሰሰበትና የጭቁን ሕዝቦች ልጆች አጥንት የተከሰከሰበት ነው። ዛሬ በካርታ ላይ ሰፍራ በዓለም ደረጃ የምትታወቀው ኦሮሚያ የተረጋገጠችው በዚህ በተከፈለ መስዋዕትነት ውስጥ ነው። የኦነት ፀር የሆኑት በተለይም ደግሞ የድሮውን ስርዓት መመለስ የሚፈልጉ ኃይሎች ይህ የፌዴራል ስርዓት እንዲፈርስ የሚፈልጉበት ዋንኛው ምክንያት ኦሮሚያን በካርታ ላይ ማየት ለነሱ ትልቅ የራስ ምታት ስለሆነባቸው ነው። ለዚህም ነው በቻሉት መንገድ ሁሉ ተጠቅመው የኦነትን ድሎች ማጥፋት የሚፈልጉት። በተለያዩ ድንበሮች ላይ ለተፈጥሩት ግጭቶች እና በዚህም የተነሳ ለሕዝቦች ከቀዬአቸውና ንብረታቸው መፈናቀል መንስዔ የሆነው የፌዴራል ስርዓቱ ነው እያሉ እንደ ማሳመኛ ለማቅረብ የማይሞክሩት ነገር የለም።

ይህ አሁን ያለው የፌዴራሊዚም ስርዓት በውስጡ ዲሞክራሲ ስለሌለና በስራ ላይ ማዋሉ ላይ ችግሮች ስለገጠሙት ነው እንጂ በስርዓት ስራ ላይ ቢውል ስር ሰደው የመጡትን የዚህችን አገር ችግሮች ለመፍታት ለሁሉም የሚበጅ መፍትሄ ነው። በመጡትና ባለፉት የሀበሾች ስርዓቶች ውስጥ የነበሩት ችግሮች የብሔር ጭቆና ስለነበሩ፣ አሁን በብሔሮችና ብሔረ ሰቦች ክልሎች ላይ የተመሰረተው የፌዴራል ስርዓት ለዚህች አገር ችግሮች ጥሩ መፍትሄ ነው ማለት ነው። ይህንን ስርዓት የሚጠሉት ኃይሎች ቁጥራቸው ትንሽ ስላልሆነ፣ ባንድ በኩል በምቻላቸው መንገድ ሁሉ ራሳቸውን እያደራጁና ኃይላቸውን እያጠናከሩ በሌላ በኩል ደግሞ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀምና ፕሮፓጋንዳ ባማድረግ ሕዝቦችን ለማሳመን ያማያደርጉት ጥረት የለም። ከብሔርና ብሔረ ሰቦች ውስጥ ደግሞ ለነሱ የሚሰራላቸውን በቀላሉ ማግኘት ስለምችሉ፣ ይህ በይበልጥ ሞራላቸውን ያጠናክራል። ድሮም ቢሆን ጨቋኝ ስርዓትን በሕዝቦች ላይ መጫን የቻሉት በራሳቸው ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ የምተባበሩአቸው ከሃዲዎችን ማግኘት በመቻላቸው ነው።

ይህንን አሁን ያለውን የፌዴራል ስርዓት አፍርሰው በምትኩ ለራሳቸው የሚሆነውን ለመተካት ዝግጅት ካጠናቀቁ ቆይተዋል። እነሱ የምመኟት ኢትዮጵያም ምን እንደምትመስል ካርታ አዘጋጅተዋል። ይህ ደግሞ በድብቅ ሳይሆን፣ በየማሕበራዊ ድህረ ገፆች ላይ በይፋ የሚታይ ነው። የነዚህን የፀረ ኦነት ኃይሎችን አካሄድ መናቅና መተው አደጋ ሊያመጣ ስለሚችል፣ የብሔርና ብሔረሰቦች ኃይሎች እንዲሁም ይህንን አሁን ያለውን የፌዴራል ስርዓት የሚደግፉት ኃይሎች ኃይላቸውን አጠናክረውና በልጠው መገኘት የግድ ይላል። እንደ ራሴ አመለካከት የኦዴፓን አቋም በግልፅ ባላውቅም፣ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ይህንን የፌዴራል ስርዓት እንደምደግፉ ነው የማምነው። ስለሆነም የኦሮሞ ድርጅቶች ተዋህደው አንድ መሆን ብቸግራቸው እንኳን በመተባባር ወይም ህብረት (alliance) በመፍጠር ኃይላቸውን አጠናክረው ለሚመጣው ሁሉ መዘጋጀት፤  የኦሮሞን ጎራ (Oromo Camp) ኃይል ማጠናከር አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝም ነው።

ባሁኑ ወቅት ያሉት የኦሮሞ ድርጅቶች ኃይል ምን ያህል አስተማማኝ ነው?

እንደሚታወቀው ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ሌላ የቀሩትና የሚታወቁት የኦሮሞ ድርጅቶች እንደ ኦነግ (ABO SG)፣ የተባበረ ኦነግ (ABO Tokkoome)፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የኦሮሚያ ነፃነት ግንባር (AWO) በፊት አንድ ኦነግ የነበሩና በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ ናቸው። ቢመርም እውነታን መዋጥ የግድ ስለሚሆን፣ እነዚህ ድርጅቶች ውጭ አገር እያሉ ሲፋተጉና ስተቻቹ የቆዩ በመሆናቸው ወደ አገር ቤትም ከተመለሱ በኋላ ይነስ ይብዛ እንጂ ከዚህ ከከፋፋይ ድርጊት የተቆጠቡ አይመስሉም። ማስተዋል እንደሚቻለው ከኦነግ (ABO SG) የቀሩት ሌሎች ድርጅቶች ወደ አገር ከተመለሱ በኋላ በኦዴፓ ጉያ ስር ተሸሽገው ቁጭ ያሉ ይመስላሉ። የሚገርመው ግን እነዚህ ድርጅቶች ወይ ከኦዴፓ ጋር አልተወሃዱም ወይንም ደግሞ ራሳቸውን ችለው ነፃ ሆነው መንቅሳቀስና ሕዝብንም አያደራጁ ጉልበታቸውን ማጠናከር አለመቻላቸው ነው። ቁጭ ብለው ምን እንደሚጠብቁ አይገባኝም። ለሚመጣው የአገሪቷ ምርጫ ራሳቸውን እያዘጋጁ ነው እንዳይባል ባሁኑ ጊዜ ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አመቺ አይመስልም።

እዚህ ላይ አንባቢዎች እንዲገነዘቡ የምፈልገው፣ ABO SG ብዬ እዚህ ያቀርብኩት ከተቀሩት ድርጅቶች ለመለየት ያህል ነው እንጂ ይህ የድርጅቱ ሕጋዊ ስም አይደለም። ይህ ABO SG ተብሎ የሚጠራው በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ግንዱ ኦነግ ሲሆን መዋቅርና ወታደራዊ ቅርንጫፍ ያለው ነው። SG የሚቆመው በኦሮምኛ Shanee Gumii ለሚለው ሲሆን ይህ ደግሞ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማለት ነው እንጂ የድርጅቱ ስም አይደለም። ሰራዊቱን ወደ ካምፕ የመመልስ ስራ ከመደረጉ ወዲህ ሁኔታዎች ተቀየሩ እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (WBO) የABO SG አካል ነው። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ድርጅት ወደ አንድ ቡድን አሳንሰው ሸኔ ብለው ሲጠሩ ይሰማል ወይም ይታያል። ABO SG ወደ አገር ቤት ከተመለሰ ወዲህ ወደ ዳር የተገፋና ጫናም እየተደረገበት ያለ ይመስላል። እንደፈለገ በደንብ እየተንቀሳቀሰ ያለ አይመስልም። በተላያዩ ምክንያቶች ከፌዴራልም ሆነ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጫና የተደረገበትና የተለያዩ ተንኮሎችም እየተሰሩበት ያሉም ይመስላል። የደርጅቱ ቢሮዎች እንደተፈለጉ በየቦታው መከፈት የቻሉም አይመስልም። ኣባላቱም በደንብ መንቅሳቀስ እንዳልቻሉ ይነገራል።

ኦፌኮንም ካየን እንደዚያ ሕዝብን ስቀሰቅስና ሲያንቀሳቅስ moblize ሲያደርግ የነበረ ድርጅት የቀዘቀዘ ሁኔታ ውስጥ ያለ ይመስላል። በነሱም ላይ ጫና አለ ብዬ ነው የማስበው። ያለምክንያት እንደዚህ ፀጥ አላሉም። ባጠቃላይ ምን እየሰሩ እንደሆነና ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው የቀሩት ሌሎች ድርጅቶችም በኦዴፓ ጉያ ስር ገብተው የሆነ ነገር የጠበቁ እንደሆነ ይመስላል እንጂ የነሱም እንቅስቃሴ አይታይም። ኦዴፓ ውስጥም የተለያዩ ችግሮች ተፈጥረው፣ በድርጅቱ ውስጥ መከፋፍል እንዳለም ይነገራል። ይህ አሁን የተጀመረውን የለውጥ ሽግግር ለማሻገር በሚፈልጉና ይህንን በሚቃወሙ መካከል በቡድን መካፋፋል እንደሚታይ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።

ባጠቃላይ ባሁኑ ወቅት የኦሮሞ ድርጅቶች ያሉበት ሁኔታ ተስፋ የሚሰጥ አይመስለም። የኦሮሞ ጎራ (Oromo Camp) ካልጠነከረና አስተማማኝ ኃይል ካለተፈጠረ፣ አደጋ ውስጥ መግባት የማይቀር ይሆናል። ጠላቶቻችን ግን አሁን በተፈጠረላቸው ጥሩ ሁኔታና አጋጠሚ በመጠቀም ራሳቸውን እያደራጁና ኃይላቸውን እያጠናከሩ ይገኛሉ። በፕሮፓጋንዳቸው የአገሪቷን ሕዝቦች ለማሳመንና ከነሱ ድጋፍ ለማግኘት የማይሞክሩት ነገር የለም። እነዚህ ፀረ ኦነትና ፀረ ጭቁን ሕዝቦች የሆኑት ኃይሎች በአገሪቷ ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ብዙ ሚዲያዎች ስላላቸው፣ በዚህ በኩል ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደርጉ ያሉ ይመስላል። ከሚጠቀሙባቸው የፕሮፓጋንዳ ስልቶች ውስጥ አንዱ በኦሮሞ ድርጅቶች መካከል አለመግባባትና ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ማድረግና በዚህ የተነሳ የኦሮሞ ጎራ እንዲዳከም ሌት ተቀን እየሰሩ ናቸው። የኦነት ፀር የሆኑ ኃይሎችን በሚመለክት በሚቀጥለው ፅሁፍ ውስጥ በሰፊው እመለስበታለሁ።

ተመልሰን እስከምንገናኝ በደህና ቆዩ

 

2 Comments

 1. Ethiopian Airlines is unable to operate as it should due to lack of enough space at the Addis Ababa Bole International Airport. The Addis Ababa Master Plan should expand Addis Ababa if Ethiopian Airlines is expected to be of any value at all.

  Ethiopian Airlines which PM Abiy-ot was talking about selling to Emirates’s private tycoon investors is on a verge of bankruptcy, even the Private investors are quickly pulling back the offers they extended to buy Ethiopian Airlines.

  Both Ethiopian Airlines and Lion Air managements had unofficially admitted that the accidents of Boeing 737 MAX planes were caused by pilots errors and both Airlines have requested to hold negotiations with Boeing in finding out the most cost effective ways to resolve the issue surrounding Boeing 737 Max planes accidents.

  Ethiopian Airlines flight 302 pilots were young , with Ahmed Mohammed, aged 25 born in 1994 and Yared Getachew, aged 29 born in 1990, these are the two pilots that are blamed for not following procedures completely resulting in the horrible accident of flight 302.

  Boeing CEO said the 737 MAX planes had no defects since the planes security systems were designed perfectly, according to Boeing CEO it was pilots error that caused the EAL flight number 302 to fail out of the sky.

  Many analysts said in a failed country like Ethiopia , airplane safety procedures are often neglected since, in failed countries human lives are not as valuable as other countries. So if this is true Ethiopian Airlines is expected to pay full compensations to the EAL flight number 302 crash victims families and also is expected to pay other fees including insurance penalities that might arise from the EAL flight 302’s trajedy , it might cost Ethiopian Airlines up to tens of billions of dollars USD, not including the loss it might encounter due to loosing it’s long standing safety reputation.

  https://m.youtube.com/watch?v=IxhKtCktyjk

  https://www.reuters.com/article/us-ethiopia-airplane-pilots/youngest-captain-loving-son-ethiopian-pilots-honored-in-death-idUSKCN1R11LV

  https://www.cnn.com/2019/04/29/investing/boeing-annual-meeting/index.html

 2. Things are being done too fast, most are unable to catch up with daily events to update themselves to make a plan of action. By 2021 GERD is expected to produce 750 MEGA WATTS electricity and by 2023 GERD will produce all of the 6.4 GIGA WATTS elevtricity. With constant uninturuppted electricity many great treatment centers can open to help the displaced in today’s Ethiopia recover, eventhough Ethiopian people are not nice to each other with over 4 millions iinternally displaced people in Ethiopia displaced by their own very close neighbors, being able to have your own residence in a sanctuary city of New York as Gigi does written in the link below , with no nagging defaming roommates/neighbors is a blessing.

  The life Mr. Gebrekristos Desta who lived in New York until his very last breath in the 1960’s is a dream for almost all single persons of Ethiopia.
  New York is still a dream destination for SF habeshas that want to live away from the back stabing ill willed evil habesha frinemies that bother attack any chance they got regularly.

  After 50+ years later Artist Gebrekristos Desta’s death, locking his door , dieing peacefully at his home is considered to be a dream come true for the vast majority of Ethiopians.That is why I say Let Gigi live the lifestyle that most Ethiopians only long for to have one day.

  To Gigi
  Live your life the way you choose to, DONOT let anyone tell you, that your small room is not enough for you. Atleast you donot have to go room to room every minute checking if burglars are in, like those people living in mansions do. Many will follow you, move out of SF to NY soon too. SF bay area habesha is mostly too scandalous that are always in competition amongst each other ,one good example, that happened to many just this past Easter Fasika day was the ones with big residences who stayed in this country long invited people for Easter lunch to their homes .when the invited guests went take a bite of the fasika food right away those that invited them turn around and tell their families that the guests are an uninvited guest busters starved begger they fed. That is why I say You are better off where you are.

  Texas is another place filled with people who left SF bay area just like you did.

  Sincerely, Almaz

  https://www.zehabesha.com/amharic/archives/95020

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.