የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው?

– ትላንት የነበሩት፣ ዛሬ ያሉትና ወደፊት የሚኖሩት ፈተናዎች –

ብርሃኑ ሁንዴ, Bitootessa 30, 2018                                     

Ahmed

ክፍል ሰባት

በክፍል ስድስት ፅሁፍ ውስጥ “የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕድድ – OPDO) የኦሮሞ የነፃነት ትግል (ኦነት) ኣጋር ይሆናል ወይንስ እንቅፋት ይሆንበታል?” በሚል ርዕስ ስር አሁን ባለው ሁኔታ ይህ ድርጅት ለኦነት አጋር ከመሆን ፋንታ እንቅፋት እንደሚሆንበት ተገልፆ ነበር። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ አዲሱ ጠ/ሚኒስተር ከዚህ ድርጅት ውስጥ መውጣት አንድ ስር ነቀል ለውጥ እንደሚያመጣ ተደርጎ እየተወሰደ ነው። ይህን የምናየው ጉዳይ ሆኖ፣ ነገር ግን የአንድ ጠ/ሚኒስተር ከኦሮሞ ሕዝብ መውጣት ኦነትን ወደ ተፈለገው ግብ ያደርሳል የምል እምነት የለኝም። ለምን ይህንን ጥርጣሬ እንዳለኝ በዚህኛው ፅሁፍ ውስጥ ለመግለፅ እሞክራለሁ።

የወያኔ መንግስት ጠ/ሚኒስተር ከኦሮሞ ውስጥ ስለመጣ የኦሮሞ ብሔራዊ ጥያቄ መልስ አያገኝም

ወደ ዋናው የዛሬ ፅሁፍ ጉዳይ ከመግባት በፊት፣ እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ ለአንድ የኦሮሞ ልጅ መልካም ምኞት ማስተላለፍ አስፈላጊ ስለሆነ ዶ/ር አብይ አህመድ እንኳን ደስ ኣሎት ማለት እፈልጋለሁ። የሳቸው መመረጥ ለኦሮሞ ሕዝብ ትርፍ ቢያመጣም ባያመጣም፣ በዚህ የነፃነት ትግል ውስጥ ሚና ይኑረውም አይኑረው፣ ድርሻም ያበርክት ኣያበርክት፣ የኦሮሚያ ምድር እንዳፈራችው የኦሮሚያ ልጅ ለሳቸው መልካም ዕድልን መመኘት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ።

ይሁን እንጂ ከዚህ ከጠ/ሚኒስተር ምርጫ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሰዎች ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቶአቸው፣ ኣንዳንድ ከእውነት የራቁ ነገሮችን በሶሻል ሚዲያ ላይ ሲወረውሩ ይታያሉ። አንዳንዶቹ ይህ የሕዝብ ምርጫ ነው ይላሉ። ኣንዳንዶቹ ደግሞ የኦሕድድ ጥንካሬ ነው ይላሉ። እንደኔ አመለካከት ይህ የሚባለው ሁሉ እውነት አይደለም። ኦሕድድን ዛሬ የሚገኝበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደረገውና ለዶ/ር አብይ ምርጫ መንስዔ የሆነው የድርጅቱ ጥንካሬ አይደለም። አዲሱ የኦቦ ለማ መገርሳ አመራር ወደዚህ እንዲወጣ ያደረገውና ለዶ/ር አብይ መመረጥም ዋና ምክንያት የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄና በተለይም ደግሞ የኦሮሞ ቄሮ (Qeerroo) መስዋዕትነት የከፈሉበት ሕዝባዊ ትግል ነው። የኦሮሞ ሕዝባዊ አመፅና ንቅናቄ ባይነሳና እየተጠናከረ ባይመጣ ኖሮ፣ ኦሕድድም እዚያው ድሮ በነበረበት ይቀር ነበር። ስለዚህ ትንሽ ከእውነት የራቀ ነገር ማሰራጨት ስህተት ነው።

እውነት ነው፤ የኦሮሞ ሕዝባዊ ንቅናቄ በፈጠረው ሁኔታ ውስጥ የኦቦ ለማ አመራር ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ የማይካድ ነው። ብዙም ደክመውበታል፤ ለዚህ ደግሞ ሊመሰገኑ ይገባል። ዶ/ር አብይ ብዙ ነገሮች ብጠበቅባቸውም፣ እውነት የሚፍለገውን ለውጥ ያመጣሉ ወይንም ኣያመጡም የሚለውን አሁን በዚህ ደረጃ ላይ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እጅግ በጣም ከባድና የተወሳሰብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገቡና ይህ ነው የማይባል ፈተና እንድሚጠብቃቸው ጥርጥር የለውም። ይህን ፈተና ውስጥ አልፈው ትንሽም ቢሆን ኣንዳንድ ለውጦችን ማምጣት ከቻሉ ይህ ጥሩ ጅምር ይሆናል። ነገር ግን ይህንን የሚጠብቃቸውን ፈተና ማለፍ ካልቻሉና ይህንን የበሰበሰውን የወያኔ ስርዓት ጠጋግነው ለማቆየት የሚሞክሩ ከሆነ፣ የራሳቸውን የሕይወት ታሪክ ከማበላሸትም አልፈው ለሕዝባችን አደገኛ የሆነ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ይህን ሁሉ ወደፊት የምናየው ይሆናል።

ወደ ዋናው የፅሁፉ ጉዳይ ለመመለስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ብሔራዊ መሰረታዊ ጥያቄ (the fundamental Oromo national question) የአገሪቷ ጠ/ሚኒስተር ኦሮሞ ስለሆነ መልስ ሊያገኝ እንደማይችል ለሁሉም ግልፅ መሆን አለበት። ለምን ወይም እንዴት ቢባል፥

አንደኛ፥ ይህ የወያኔ ስርዓት በቦታው እስካለ ድረስ፤ ሕወሃት በዚህ መንግስት ተብዬው ውስጥ ድርሻ እስካለው ድረስ፤ በይበልጥ ደግሞ ቆልፍ የሆኑ የመንግስት ተቋማት በሕወሃት ቡድን እጅ እስካለ ድረስ፤ ምንም ያህል የተለያዩ ለውጦች ቢደረጉም እንኳን የኦሮሞን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ሊመልስ አይችልም። አንዳንድ ጥቃቅን ለውጦችን ለሕዝብ በማሳየት፣ ይኸው ትርፍ እያመጣንላችሁ ነው፤  ቀሪውም ቀስ በቀስ ይመጣል በማለት ኣንድንድ ነገሮችን ቆንጥረው ለሕዝባችን በመስጠት፣ የኦሮሞ መሰረታዊ ጥያቄ ምልስ ሊያግኝ በፍፁም አይችልም።

ሁለተኛ፥ አሁኑኑ መወራት እንደተጀመረው፣ ይኸው ኦሮሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ጠ/ሚኒስተር ኣግኝተዋል እየተባለ ፕሮፓጋንዳ ስለሚደረግ፤ ይህ ደግሞ የሕዝባችንን ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ ስለሚወስድ፤ ለኦሮሞ የነፃነት ትግል እንቅፋት ይሆናል። የሰዎችን ሀሳብ ለያይቶ በጋራ እንዳይታገሉ ያደርጋል። ለዋናው የትግሉ ግብ ትኩረት መስጠትን ትተው ለኣንዳንድ ጥቃቂን ነገሮች እንዲታለሉ የማይሆን ሁኔታን ይፈጥራል። በዚህ በሚፈጠርው ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ስግብግብነትና ለግል ጥቅማ ጥቅሞች መሮጥ ይፈጠራሉ። እነዚህ ደግሞ የትግሉ ፀር ናቸው።

ሦስተኛ፥ ይህ እንደ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውና የወያኔን ስርዓት ለመጣል በገደል አፋፍ ላይ ያደረሰው የሕዝብ ትግል ምናልባትም በጠ/ሚኒስተሩ ሊደረጉ በሚችሉ ኣንዳንድ የፖሊሲ ለውጦች (policy reforms) ለጊዜውም ቢሆን ሊቀዘቅዝ ይችላል። በፍጥነት እየሄደ ያለውን ትግል ፍሬን መያዝ እንደ ማለት ነው። ይህ ደግሞ የነፃነትን መንገድ ያራዝማል።

አራተኛ፥ አንድ የኦሮሞ ልጅ የአገሪቷ ጠ/ሚኒስተር ሆነ ማለት ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ አይመረጥም። አገሪቷን ለመምራት ነው። በመሆኑም የኦሮሞን ልዩ ፍላጎት ከማስቀደም ይልቅ የአገሪቷን ጉዳይ ማስቀደም የግድ ይሆናል። የውጭ መንግስታትና የዓለም ማህበረ ሰቦችም ይህ የተመረጠው ጠ/ሚኒስተር በኣጠቃላይ ለአገሪቷ የሚሰራውን ይደገፋሉ እንጂ በተለየ መልኩ የኦሮሞን ሙሉ ፍላጎት እንዲያሟላ አይረዱም። በዚህ ውስጥ የኦሮሞ የነፃነት ትግል ትኩረት ያጣል ማለት ነው።

አምስተኛ፥ ከዚህ በፊት ሲባል እንደነበረው፣ ይኸው ጠ/ሚኒስተርና የአገሪቷ መሪ ከኦሮሞ ውስጥ ወቷል፣ ኦሮሞ ከዚህ በላይ ምን ይፈልጋል አየተባለ ፕሮፓጋንዳ ስለሚደርግ፣ ትልቁ የኦሮሞ የነፃነት ትግል ዓላማና የኦሮሞ ብሔራዊ ጥያቄ ግንዛቤ ውስጥ እንዳይገባ ያደርጋል። ለትግሉ ተጨማሪ ፈተናን ይፈጥራል።

ስደስተኛ፥ ከኣንዳንድ ንግግሮቻቸው ማስተዋል እንደሚቻለው፣ ዶ/ር አብይ የኢትዮጵያዊነት ሱስ ስላለባቸው፣ ከኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት ይልቅ የአገሪቷን ፍላጎት ማስቀደም የሚፈልጉ ይመስሉኛል። ይህ ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በኦሮሙማ (Oromummaa) ላይ ተፅዕኖ ያመጣል።

እንግዲህ፣ አንድ የኦሮሞ ጠ/ሚኒስተር መመረጥ ማለት ለኦሮሞ የነፃነት ትግል አጋር ሆኖ፣ ለመሰረታዊ ጥያቄው መልስ ከመስጠት ይልቅ፣ ትልቁ የኦሮሞ ብሔራዊ ጥያቄ ትኩረት አጥቶ፣ ሕዝባችን አሁንም በኣንዳንድ ጥቃቅን ለውጦች ተታለው፣  ለትግሉ የመጨረሻ ግብ እንዳይቀጥል አመቺ ያልሆነ ሁኔታን ይፈጥራል እንጂ፣ ከኦሮሞ ጠ/ሚኒስተር የሚገኝ ልዩ ጥቅም እኔ አይታየኝም። ይሁን እንጂ ኦሕድድም ሆነ ዶ/ር አብይ ለኦሮሞ ነፃነት ድርሻ መስጠትና አጋር መሆን ከፈለጉ ካሁን በኋላ ከወያኔ ተፅዕኖ ነፃ በመሆን፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት በዚህ ላይ በቁርጠኝነት መስራት ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ የኦሮሞ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄ መልስ ማግኘት ቀርቶ ይህንን እንደ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን የሚያቀዘቅዝ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ከጠ/ሚኒስተሩ ምርጫ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮችንና የጠላቶቻችን እንቅስቃሴን በተመለከተ በሚቀጥለው ፅሁፍ ሀሳቤን ይዤ እመለሳለሁ።

ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ።

6. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ስድስት
5. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አምስት
4. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አራት
3. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሦስት
2. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል ሁለት
1. የኦሮሞ የነፃነት ትግል ከየት ተነስቶ ወዴት እየሄደ ነው? ክፍል አንድ

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020