የዘር ማጽዳት ከዱሮ እስካሁን

የዘር ማጽዳት ከዱሮ እስካሁን

ደጋፋ አብዲሳ ቱቾ (ዶ/ር)

Oromo students at universities in Amhara region were crying out for help and rescue days after organized attacks were first unleashed on them. “Political expediency trumps life” has been proven right by Dr. Abiy one more time. For him, pulling Oromo students out of schools in the Amhara region is an admission his “medemer” nonsense is a dismal failure, so he simply chooses inaction as students are murdered every single day.

በጣሊያን ወረራ ጊዜ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ በፈቃድኝነት ከኢትዮጵያ ጋር ተሰልፎ ለመውጋት ከኩባ መጥቶ በ1928 ከራስ ሙሉጌታ ያኔ የመከላከያ ምኒስቴር ጋር ወደ ማይጨው የዘመተ ኮሎኔል አልኽንድሮ ዴል ባዩ በቆቦ ኦሮሞ ላይ የደረሰውን በዓይኑ ያየውን በእስፓኒያ ቕንቕ የጻፈውን በዶክተር ተስፋዬ መኮንን ወደ አማርኛ የተተረገመውን ዋቢ በማድረግ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

የመጽሐፋ ስም ቀይ አንበሳ

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ገጽ 115-116 ላይ በቆቦ ኦሮሞዎች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት በገጽ 115 ላይ ተጽፎአል። ሌሊት ነው። ሁላችንም አልተኛንም። ሆኖም ምሽቱ ሰላምና ጸጥ ያለ ነበር። ቆቦን በምናቕረጥበት ወቅት የጦር አለቃው ደጃዝማች መሸሻ ክብራቸው ተደፍሮ ነበር። ከመንደሩ ነዋሪዎች አንዱ በአደባባይ ከጎደኝኞቻቸው ኣንዱን ገድሎባቸዋል። የሰፈርንበት ቦታ ከቆቦ 3 ማይል ርቀት ላይ ወጣ ብሎ ነው። መሸሻም ቁጭታቸውን ለመወጣት የነኩዋቸውን ሰዎች አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት በልባቸው ተወስነዋል። በጡዋት ድምፅ ሳያሰሙ 5000 ሰዎችን አሰባስበውን ወደ ቆቦ ጉዞ ቀጠሉ። ከተማዋን እንዳልነበረች አድርገዋት ተመለሱ። ያጠቁዋቸውን የደፈሩዋቸውን በሙሉ በጎራዴ ቀነጠሱ። ሹማግሌዎች ልጆች ወንድ ሴት ሳይሉ ገድለዋል። እነኝህ ሊወድቁ የደረሱ ቤቶች በውስጣቸው ከ1200 በላይ ሬሳ ታቅፈው። ቀርተዋል።

ደጃዝማች መሸሻ በጣም ሃይለኛ ሰዉ ናቸው። ጸጉራቸው። ሙሉ በሙሉ ነጭ ሲሆን መልካቸው በጣም አስቀያሚ ነው። ስ በሚያስፈራ መልክም ወፍራም ናቸው። መራመድ። እንኩዋን ያቅታቸዋል። በተጨማሪም እግራቸው። በሥጋ ደዌ በሽታ ተቦዳድሶኣል። በጉዞ ወቅት ባሮቻቸው ተሸክመው በቅሎቻቸው ተሸክመው በቅሎአቸው ላይ አወጥተው እንዳይወድቁ ደግፈዋቸው ይኅዛሉ። መራራና አስጠሊ የሆነውን ህወታቸውን ለመበቀል። ይመስላል ወደር ያልተገኘለት ጨካኝ ናቸው።

አንድ ቀን ጠዋት የደጃዝማች መሸሻ ሰዎች ሰባት ሽፍቶችን ከነህወታቸው ያዘዋቸው። ወደ ደጃዝማች መሸሻ ድንኩዋን ይዘዋቸው አመሩ። እንደ ክብር እንግዳም እኔ ተገኝቼ የሚስጣቸውን ቅጥት። እንድመለክትላቸው ጋበዙኝ ። ሰባቱም ሰዎች ቀስ በቀስ ተቆራረጡ። በመጀመሪያ ጆሮዋቸውን ቀጥሎ እጆቻቸውን ቆየት ብሎ ምላሳቸውን። ቅጣት ፈጻሚዎቹ የእነዚህን ያልታደሉ ጥፋተኞች እያንዳንዱዋን የሰውነት አካል በፍጥነት ሲቆረጡ ማየት በጣም ይዘገንን ነበር። ያለ እግር ያለ እጅ በደም የተለወሰ መሬት ላይ የተቀመጠ ጭንቅላት ወገብና ደረት ብቻ ከዓይናቸው በስተቀር ምንም የሚንቀሳቀስ ክፍል የሌላቸው የተቆራረጡ ገላዎች ኣሳዛኝ ፍጡሮች። ዓኖቻቸውም ቢሆኑ ከዚያ ከፊታቸው ክብ ቦታ በጦር ተቦርቡረው እንዲወጡ ተወሰነ። ዙሪያውን የከበበው ሠራዊትም የመበቀል ምኞቱን ለመወጣት እየጮኸ ድርጊቱ ሲፈጸም ያደንቃል።

የደረሰባቸውን ሰቆቃና ሰቃይ ቆሜ በመታዘቤ የእኔ ስሜት በሙሉ። ደነዘዘ ድርጊቱ እጅግ በጣም መጥፎና የሚያስጠላ ነበር።

በዚሁ መጽሓፍ ገጽ 147-148 ላይ

ኣንድ ቀን ምሽት ወደ ኣርባ የሚጠጉ ጥቁር የቆቦ ጎሳዎች ወደ እኛ ሰፈር ተሳስተው ገቡ። ራስ ሙሉጌታ ወደ አሉበት ቦታ እንዲመጡ አስጠሩዋቸው። በጥሩ አቀባበልና በተለሳለሰ መንገድ ያነጋገራቸው ጀመር። ሁልጊዜ ጠዋት። ጠዋት ብዙ ከፍተኛ ሥነ ሥርዓት እየተደረገ እስረኞቹ እየተሰበሰቡ በዚያች የአለንጋ ግርፍ ይተለተሉ ነበር። ለብዙ ቀናት ቁስላቸው እስክገጥምና እስኪጠግ ድርስ የተዋቸውና እንደገና ሌላው አይነት የቅጣት አይነት ተፈጸባቸው። አፍንጫቸውን እጃቸውን ጆሮኣቸውን ምላሳቸውን ከንፈራቸውን ቀስ እያሉ ተራ በተራ ቆረጡዋቸው። አንዱን የሰውነት ክፍል ከቆረጡ በሀዋላ እንዳይሞቱ ያክሙቸዋል። ሲጠግግ ሌላውን ይቆርጣሉ። የመጨረሻው የተደረገው በመጨረሻው ቀን በአንድ በጋለ ብረት ፊታቸው ላይ። ምልክት። ጠባሳ ማድረግ ነበር። ይህ ደግሞ ከሃዲ ለመሆናቸው መለያ እንዲሆን ነው። እናም። ብዙዎቹን ዲዳ ዓይነ ስውሮች እጀ አልባ አፍንጫ ቆራጣ አስቀያሚ ገጽታ ይዘው አንድ መልዐክት የያዘ ፅሁፍ አሲዘዋቸው ወደ ጣልያኖቹ መስመር መሄጃ መንገድ ላይ እንዲቀመጡ አደረጎቸው። የፅሁፉም መልዕክት እንዲህ ይል ነበር።

<< ከሃዲ ባንዳዎችን ራስ ሙሉጌታ እንዲህ ነው የሚያደርጎቸው።>>

በበኩሌ እንዲህ ያለው ነገር እንዳይፈፅም ተቃውሜአለሁ። ምክንያቱም እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ ቅጣት ብቻ መሆኑ ሳይሆን እንዲህ ላለው ነገር ማረጋገጫ የጣሊያን መንግሥት ካገኘ በኢንተርናሽናል ሊግ ኢጣልያ ምቹ ኣጋጣሚና ተስሚነትን እንዲታገኝ ሊረዳት ስለሚችል ነው።

ራስ ሙሉጌታ ግን አፍጥጠው << ለእኔ ኢንተርናሲዮናልና አንድ የሞተ ጅብ አንድ ናቸው። ሁሉም አገሮች አቢሲኒያን በመቃወም ሊሰለፉ ይችላሉ። እኔ ግን ሁሉንም ላሽነፋቸው ይችላለሁ። ከፈለጉ ሁሉም ፈረንጆች ይምጡ። ልንሽነፍ አንችልም ልንሽነፍ አንችልም ገባህ?

በዚች ቀን ራስ ሙሉጌታ እድሜያቸው በመግፋቱ የነበራቸውን ብስለት በማጣት ማመዛዘን እንዳዳገታቸው ልገነዘብ ችያለሁ።

ከዚች ቀን ጀምሮ እኒህ ኢትዮጵያው አለቃ ጭካኔያቸው በመባባሱ ከቀን ወደ ቀን የበልጠ ሓይለኛ ሆኑ። እስከ 150 እስረኞች በአንድ ምሽት በዘወትር በመሰቃያ መንገዳቸው ብቻ ሳሆን በጥይት ተደብድበው እንዲሞቱ ማድረግ ደርስዋል።

ይህ እንግዴ በኮለነሉ ዕይን ምስክርነት በቆቦ (ወሎ) ኦሮሞ ላይ የተደረገ ግፍ ነው። የቆቦ ኦሮሞች በዚህ ዓይነት ጭፍጨፋ አልቀዋል። አሁን በቆቦ አከባብ የሚኖሩ ማን ናቸው?

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ የገዢ መደቦች በሕዝብ ላይ የፈጸሙት ስባዊ መብት ጥሰት ባለ ብዙ ፈርጅ ይገኛል። ወደ ፊት ተራ በተራ አቀርባለሁ ።

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.