የግንቦት 7 ልሳን የሆነው ኢሳት (ESAT) በአለቆቹ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቷል

የግንቦት 7 ልሳን የሆነው ኢሳት በአለቆቹ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጃዋርና ቄሮ ላይ ከፍቷል። ሶስት ቀን ሙሉ አጀንዳቸው እሱ ብቻ ነበር። “የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከህወሃት ጋር በድብቅ እየሰሩ ነው፤ ጃዋር ግድያ እያቀነባበረ ነው” እና ሌሎችም ብዙ የፈጠራ ክሶች እያቀረቡበት ነው። “መንግስት እስከመቼ ነው የሚታገሰው?” ብለውም ይጠይቃሉ።


በማህበራዊ ሚዲያም ላይ ግንቦት ሰባትን በመደገፍ የሚታወቁ ግለሰቦች ከፍተኛ ቅስቀሳ ከፍተውበታል። በዚህ ምክንያት ነው የአዲስ አበባው ሰልፍ ላይ ስሙን ጠርተው ሲያወግዙት የነበረው። የሚገርመው ጃዋር ገና ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን እንደመጣ ነው አገሪቱን በዚህ የሽሽግር ወቅት የሚያሰጋት anarchy ነው መንግስት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ሲል የነበረው። ከማንም በላይ ወጣቶች ከተቃውሞ ፖለቲካ ወጥተው ወደ ሀገር-መገንባት ፖለቲካ መግባት አለባቸው ብሎ ሲመክር የነበረው ጃዋር ነው።

አላማቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ጃዋርን ለማራራቅ እና ቢቻልም ባልሰራው ወንጀል በሚዲያ campaign እንዲገፋ ለማድረግ ነው። በአዲስ አበባ የኦሮሞ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የኦነግ አመራሮችን መቀበሉ እና ማንነቱና አርማውን በስፋት ከተማዋ ውስጥ ማየታቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። የጃዋር ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ተፅእኖ ማሳደርም የእግር እሳት ሆኖባቸዋል። አብይ ስልጣን ሲይዝ አስቂኝ የካቢኔት ግምት የፃፈው ኤርሚያስ ለገሰ በተለይ ጨርቁን ሊጥል ነው። መሳይ መኮንንም ትንናት “የአማራ ህዝብ ጸብ ከአምስት ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ጋር ነው አሳውን ለማጥፋት ወሃውን ማድረቅ አለብን” የሚል የዘር እልቂት ማወጁን ረስቶ ዛሬ ሌላን ሰው genocider እያለ ይመፃደቃል።

በጃዋር እና በቄሮ ላይ ያወጁት የስም ማጥፋት ዘመቻ ታስቦበት የተቀነባበረ ሴራ ነው። በግንቦት ሰባት ፊታውራሪነት ኢሳትን ለፕሮፓጋንዳ በመጠቀምና የአዲስ አበባ ወጣትን በመቀስቀስ አዲስ አበባ ውስጥ የኦሮሞ ባህል ማንነት አርማም ይሁን ተሳትፎ ጭራሽ ደግሞ እንዳይታይ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው። ለዚህም ነው ቄሮን በጅምላ ሲፈረጁና ሲሰድቡ የሚወሉት። አንዱ የዚህ አባል እስክንድር ነጋ “ራሳቸውን ፌዴራሊስቶች ብለው የሚጠሩ ፋሺስቶች” እና “አላማ ቢስ አማፂዎች” ብሎ የኦሮሞ ወጣቶችን በጅምላ ሲሰድብ ልክ አይደለህም ያለው የለም።

የአዲስ አበባ ተቃውሞ የተጠራው ቡራዩ ላይ ሰው ስለሞተ የመሰለው ካለ የዋህ ነው። የበፊቱን እንተወውና ባለፉት አምስት ስድስት ወራት ብቻ በጣም ብዙ ሰዎች በብዙ ክልሎች ተገድለዋል። ነገር ግን “አንድ ህዝብ አንድ ኢትዮጵያ” ከሚሉት አስመሳዮች ውስጥ አንድ ሰልፍ የጠራም ይሁን የወጣ ሰው አላየንም። የአዲስ አበባው ሰልፍ የተጠራው ከፍተኛ የኦሮሞ ጥላቻ ባላቸው ግለሰቦችና የግንቦት ሰባት አባላት ኦሮሞ ሊወረን ነው በሚል ስጋት ነው። መፈክራቸውን ብትሰሙ 99 ፐርሰንቱ ከግድያው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። “ኦሮሞው ከንቲባ ወደ መጣበት ይመለስ፤ የኦሮሞ ባህል ማእከል ከአዲስ አበባ ይውጣ፤ የኦሮሞ ባንኮችና ድርጅቶች ይዘጉ፤ ፊንፊኔ የሚባል ስያሜ አለነበረም ወደፊትም አይኖርም ፤ ብሄር የሚባል ነገር የለም የሚል” ጨፍላቂ አስተሳሰብ የተራመደበት ነው።

ሌላኛው የኢሳት አላማ በ constituency ድርቅ በከፍተኛ ሁኔታ የተመታው ግንቦት ሰባት በአማራ ክልል ባዶ ስቴዲየሞችና አዳራሾች እየተንከራተተ እንደሆነ ሰው እንዳያይ distract ማድረግ ነው። ደጋፊ እንደሌለው የተረዳው ግንቦት ሰባትም የፖለቲካ ስልጣን ለማግኘት ያለው ብቸኛ አማራጭ አዲስ አበባ ላይ ያለውን የፖለቲካ አጀንዳ set ማድረግና ማንኛውም የኦሮሞ ጥያቄ በከተማዋ እንዳይስተናገድ ማድረግ ነው ብሎ አስቧል። ለዚህ ነው የቄሮን ስም የማጥፋት ዘመቻና የአዲስ አበባን ወጣት ለግጭት መቀስቀስ የጀመረው። በህወሃት ጀሌዎች የተካሄደውን የቡራዩ ግድያም ወጣቱን ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ደግነቱ backfire አድርጎባቸዋል። ከምን ጊዜውም የበለጠ የኦሮሞ ወጣት እንዲደራጅና መብቱን እንዲጠይቅ እያረጉት ነው። መንግስትም አላማቸውን ተረድቶታል።

ከንቱ ድካም ነው ልፉ ስላቸው2 Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.