የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ።
****************************************
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰራተኞቹ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣ የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ መናር የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ወ/ኪዳን ለአቢሲ ሰራተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ሰራተኞቹ ያቀረቡትን ችግር ለመፍታት ውይይቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
ከሰዓት በኃላ የግንባታ ተቋራጩን ጨምሮ በሚደረግ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡etv


የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መታወቂያ መመሪያ ተሻሻለ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 3/2010 በማሻሻል፣ ብሔር የማይጠቀስበት መታወቂያ ለነዋሪዎች መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የተሻሻለው መመሪያ የከተማውን ነዋሪዎች የመታወቂያ አሰጣጥ ከማንዋል ወደ ዲጂታል የሚያሸጋግርና በአሻራ የተደገፈም ስለሚሆን፣ በሐሰተኛ ሰነድ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦችን መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡

ይህንን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ በክፍለ ከተሞችና በወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን ያካተተ ሥልጠና፣ ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መታወቂያ ብሔርን የሚጠቅስ በመሆኑ፣ ይህም ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶችን የሚያጎላ ስለሆነ በተገኘው አጋጣሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በያዙ ማግሥት ይህንን ጉዳይ በሚመለከት እንደገለጹት፣ የመታወቂያ ጉዳይ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ እየተነሳበት በመሆኑ አሰጣጡን ማስተካከል ይገባል፡፡

በዚህ መሠረት መመርያው የተሻሻለ በመሆኑ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ በሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ለውጥ ያመጣል ተብሏል፡፡

የመጀመሪያው በመታወቂያ ላይ ከብሔር ስያሜ ይልቅ ኢትዮጵያዊ ሲባል፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሰጣጡ ዲጂታል ስለሚሆን ሕገወጦችን መለየት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ በተለይ ሕገወጥ ጥቅም የሚሹ ግለሰቦች፣ በተለያዩ ዘዴዎች መታወቂያ በማውጣት ሲያገኙ የቆዩትን ጥቅም እንደሚያስቀር ታምኗል፡፡

ለአብነት በክልል ከተሞች የግል መኖሪያ ቤት እያላቸው በሕገወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ኮንዶሚኒየም ቤት የተቀራመቱትን ዕርምጃ መውሰድ ያስችላል ተብሏል፡፡

የተሻሻለው መመርያ የኮምፒዩተር አመዘጋገብ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ ሒደት፣ የነዋሪዎች መታወቂያ ይዘትና የመሸኛ ጉዳይን በዝርዝር ይዟል ተብሏል፡፡
#Reporter_Amharic

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...