የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ በነበረበት ወቅት

ከዚህ በታች የምታዩት፣ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ በነበረበት ወቅት፣ ሥሙ መገርሳ ያደሳ የተባለው የኦሮሚያ ፖሊስ ሠራዊት አባል የሆነው ግለሰብ እንዴትና በማን እንደተገደለ የሚያስረዳ፣ በፖሊስ አባሉ ግድያ ተጠርጥሮ የነበረው ተከሳሽ አብዱልአዚዝ ገዛሊ ለፖሊስ የሰጠው የተከሳሽነት ቃል ነው። ይህ ከፖሊስ መዝገብ የተገኘ ጥብቅ መረጃ ነው። (ይህንን ጥብቅ መረጃ ያቀበሉንን የፖሊስ አባላት ሳናመሰግን አናልፍም። )

የተከሳሹ ቃል እንደሚያስረዳው፣ በወቅቱ በብልጽግና ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የጥበቃ ሥራ እየሠራ ነበር። ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞም ብዙ ግርግር ስለነበር፣ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበረ ከመሆኑ የተነሳም፣ በተጠንቀቅ ላይ እንደነበሩ ያስረዳል። ከዚህም የተነሳ፣ በወቅቱ ጠመንጃውን ጥይት አጉርሶ፣ አቀባብሎ፣ ምላጩን መልሶ በእትኩሮት ሥራውን እየሠራ፣ ሁኔታዎችን እየተከታተለ እንደነበረ፣ አለቃው መጥቶ “ቦታ ቦታ ያዙ እንጂ ” ሲላቸውም ተደናግጦ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ተደነቃቅፎ እያለ ጣቱ ቃታው ላይ አርፎ ምላጩም ተመልሶ፣ ጥይቱ በድንገት እንደባረቀ፣ በዚህም ባልደረባው መገርሳ እንደተመታና በዚህም ምክንያት እንደሞተ ያስረዳል።

የተከሳሹ ቃል በግልጽ እንደሚያስረዳው፣ በወቅቱ የነ ጃዋር አጃቢዎች ምንም ተኩስ እንዳልተኮሱ፣ ትጥቅ ፍቱ ሲባሉም፣ በተባባሪነት መንፈስ እንደ ፈቱ፣ ከእነርሱ ጋር ሌላ የመፋጠጥ ሁኔታ እንዳልነበረ በዝርዝር ያስረዳል።

እንግዲህ ይሄ መዝገብ እንደሚያሳየው፣ የፖሊስ አባሉን “የገደሉት የጃዋር አጃቢዎች ናቸው፣ እነ ጃዋርም ለዚህ ተጠያቂ ናቸው ” የሚለው የብልጥግና ክስ ፈጽሞ መሠረተ ቢስ ነው።

ይሄንን የተከሳሽ ቃል እና ሌሎች ተዛማጅ ያሏቸውን ማስረጃዎች በመያዝ በአራዳ ችሎት በሚደረግ የድመ ክስ ሂደት (preliminary hearing) በማቅረብ በማስረጃነት ለማስያዝና በኋላ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሚያቀርቡት ክስ ዝግጅት መሆኑ ነው።

የክሱ ሂደት ዝግጅት አካል የሆነው ማስረጃ የመፈብረክ ሥራም እየተከናወነ እንደሆነ ታውቋል። ለዚህ የሚሆኑ “ምስክሮች” ተመርጠው፣ 6 ኪሎ ወደ ሽሮ ሜዳ በሚወስደው ጎዳና ላይ በሚገኘው የኦሕዴድ ጽ /ቤት ውስጥ፣ “የምስክርነት ቃላቸውን” እያጠኑ፣ “ልምምድ” እያደረጉ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የፎሬንሲክ (forensic) ምርመራ ውጤት ነው የተባለ መረጃም ቀርቦ፣ ሟቹ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል የተገደለባት ጥይት “የተኳሹ የአብዱልአዚዝ ገዛሊ ጥይት መሆኗን የሚያረጋግጥ መረጃ የለም ” የሚል መረጃ በመዝገቡ ውስጥ እንደተካተተ ፖሊሶቹ በሚስጥር አስረድተዋል።

ሁሉም ሰው አይቶ እንዲፈርድ፣ የተከሳሹን ዝርዝር ቃል ከዚህ መዝገብ መረዳት
ይቻላል።የሚዲያ ተቋማት፣ ይሄንን ጉዳይ በመከታተል እውነቱን ለሕዝብ ይፋ ቢያደርጉት መልካም ነው እላለሁ።

#Abiy_Ahmed_is_a_criminal!
#Abiy_is_the_past

Similar Articles

Comments

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

OMN: ODUU GALGALAA (GURRAANDHALA 20, 2020)

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Abiy Ahmed

Ethnic cleansing continued in Oromia Regional State by Ethiopian government lead by Dr. Abiy Ahmed, Prime Minister of Ethiopia July 10, 2020 The Right Honourable Justin...

New Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in pdf

Book: የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) in PDF Via Aba Orma, September 3, 2019 የተጠለፈ ትግል (The hijacked revolution) Author: Mudhin Siraj Pages: 152 Language: Amharic Year: July 2019 To...

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

BBC Afaan Oromoo: ODUU Owwituu, Amajjii 27, 2020

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data

21 million Chinese died of coronavirus – US intelligence officials intercept data By James Alami (Web Archive) -- A new data intercepted by the United States...