In Memory of Ethsat – የእሳት ማህደረ ትውስታ

In Memory of Ethsat – የእሳት ማህደረ ትውስታ

By Tullu Ayira, Waxabajjii 7, 2019

ESAT

አንተ ብቻ አዋቂ አንተ ብቻ ተንታኝ
አንተ ብቻ ሀብታም ሌላው ድኃ ለማኝ

ኦሮሞን ከጌዴኦ ለማፋጃጀት
ለፖሎቲካህ ስትል ለመለያየት
በቁስሎቻቸዉ እንጨት መሰካት
ተመልሶ ፈጀህ የለኮስከዉ እሳት።

አረ እንዴት አስመሳይ አቤት ወላዋይ
ወዲህ ወዲያ እያለ ሁሌም አዉደልዳይ
የአብን ጫማ ሳሚ ይታመናል ወይ?

የእሳት ጋዜጠኛ የአብን ዉስጥ አርበኛ
የርይዖት ተላላኪ የዚያ ሽብርተኛ

የእሳት ምድጃ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ
የምትቀቅልዉ ሁሉ ጥሬ ምግብ ብቻ
ከምረህ ከምረህ በዉሸት ስልቻ።

እንዲበስል ብለህ መርዝ አርከፍክፈህ
እሳት ነደደና መልሶ ፈጀህ።

አንተ ብቻ ሀቀኛ ሌላዉ ዉሸተኛ
ወይ እሳት ወይ እሳት ወይ እሳት ነዉረኛ
ባመጣሀው ዳኛ ሁነህ እስረኛ
ውሸቶችህን ታቅፈህ ከመቃብር ተኛ።

የእሳት ፅንፋኞች እንዴት ሞኞች ናቸዉ
ኦሮሞን ለማጥፋት መከጃጀላቸዉ
አቤት ትዕብታቸዉ አቤት እብሪታቸዉ
በሰኮንድ ስጠፉ ለካስ ቀፎ ናቸው::

Press Freedom የእሳት Oromo People ESAT Ethsat Dawit

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.