The Eritrean army has started to withdraw from parts of Ethiopia specially western Tigray.

The Eritrean army has started to withdraw from parts of Ethiopia Specially western Tigray. The policy of alliance has been changed at once.

Afmeer tv


አፈትልኮ የወጣው ጥብቅ ሚስጥር፦

በታህሳስ መጨረሻ የተካሄደው እና ለሦስት ቀን የቆየው የብልጽግና ስብሰባ በኦሮሞና በአማራ ብሄሮች መካከል ከፍተኛ ቅሬታ አሳድሮ አልፏል፡፡አብዛኛው ተሰብሳቢ ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ይታይ እንደነበር ምንጫችን ለረጆ ሚድያ በተለይ ገልጸዋል፡፡ በስብሰባው መጨረሻ ላይ ጠ/ሚ አብይ ከተናገራቸው አንኳር ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
• ጦርነቱን በፖለቲካ፣ በወታደራዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ተሸንፈናል፤ ድርድር ማድረግ የግድ ነው። ድርድሩ ደግሞ ህገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ይሆናል።
• ትግራይ ውስጥ መግባት የማይታሰብ ነው ምክንያቱም “ህዝባዊ አጀንዳ ስለሆነ”
• የትግራይ ተወላጆች በየጊዜው አዳዲስ ኃይሎችን እያሰለጠኑ ሲሆን በቅርቡም 50,000 አዲስ ምልምሎችን አስመርቀዋል። ከ50-60 ጄኔራሎች አሏቸው፡፡ ወደ 25,000 የሚጠጉት ኃይሎቻቸው የቀድሞ የ ENDF ተዋጊዎች ሲሆኑ በሜካናይዝድ ክፍል ውስጥም ልምድ ያላቸው ናቸው።
• የትግራይ ኃይሎች ከውጪ አዲስ የጦር መሳሪያ እና ድጋፍ በአውሮፕላን እየገባላቸው ነው፡፡ አውሮፕላኑን ደግሞ እንዳይገባ ማድረግ አንችልም፡፡ ለምን ቢባል ወደ ትግራይ እየገባ ያለው አውሮፕላን ደግሞ በኛ ራዳሮች የሚታዩ አይደሉም፡፡
• የትግራይ ኃይሎች ከምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ማግኘታቸውን ቀጥለዋል። እንግሊዝና ፈረንሳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየረዱን ነው ነገር ግን ይህም በሌሎች ላይ ብዙም ተጽእኖ አይኖረውም፡፡
• መቐለ ከተማን ለቀን የወጣነው በወታደራዊ ኃይል ስለተሸነፍን ነው፤ብዙ መሳሪያችንም አጥተናል፡፡ “ተቀጠቅጠን ነው የወጣነው” ስለዚህ “አቅማችንን ማወቅ አለብን”
• አገሪቱ በአስከፊ ሁኔታ ላይ ነች። ኢኮኖሚው ላሽቋል፡፡ በዝህ በደከመ ኢኮኖሚ ጦርነቱን ማስቀጠል አንችልም፡፡
• በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የአካባቢ አስተዳደሮች በ”ሸኔ” ጥላ ስር ወድቀዋል፡፡
• ፋኖዎች የህወሓትን ኃይል ወደ ትግራይ እንዲያፈገፍጉ ያደረግነው እኛ ነን የሚለው ትርኪት ማረም አለባቸው። የተገኘው ድል የጋራ ጥረት ነበር እና አንድ አካል ብቻውን credit ሊወስድ አይችልም። ከዚህ ባለፈም የፋኖ ሃይሎች በአማራ ክልል እንደመሬት ያሉ ነገሮችን እንድሰጣቸው በማስገደድ እያደረሱት ያለውን ጥፋት ገፍተውበታል።
• በቅርቡ ከታሰሩት የትግራይ ተወላጆች እስረኞችን መፍታት እና የንግድ ቤቶችን መክፈት ጀምረናል። ይህ ብዙዎችን እንዳስቆጣ ተረድተናል እና “የትግራይን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ካለብን ይቅርታ እንጠይቃለን”
• አብዛኞቹ የፖለቲካ እስረኞች በቅርቡ ይፈታሉ።

RAJO MEDIA


ጥብቅ መረጃ፦
የኢትዮጵያ መንግስት ከሩስያ ጋር የተፈራረመውን የመሳሪያ ግዥ ለመሰረዝ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ለረጆ ቅርብ የሆኑ ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡ የመሳሪያ ግዥው SU-35 ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ M Series ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች፣ 150mm Howtizers፣ በመቶ ሺዎች AK 47 እና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን ያጠቃለለ እንደነበር ረጆ ሚድያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ለዝህ መሳሪያ ግዥ መንግስት Offshore ባንኮችን እንደተጠቀመ ሁለት የተለያዩ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረት የተወሰኑ መሳሪያዎች ወደ አገር ቤት የገቡ ሲሆን የቀረውን ወደ አገር ለማስገባት መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል፡፡ ስለዝህ መንግስት የገባውን ውል በኢኮኖሚው መዳከም ምክንያት መክፈል ባለመቻሉ ውሉን ለማቋረጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ውሉ በግዜው ካልተቋረጠ በውሉ ምክንያት የገንዘብ ችግሩ እየተባባሰ እንደሚሄድ እነኝህ ምንጮች በተለይ ለረጆ ሚድያ ገልጸዋል፡፡
እንደሚታወቀው በጦርነቱ ሳቢያ መንግስት ካዝናውን ባዶ አስቀርቶታል፡፡ በኢትዮጵያ ታርክ ማንም መንግስት ያላደረገውን የአብይ መንግስት ፈጽሞታል፡፡ ይህም ብሄራዊ ባንክ የተቀመጠውን የወርቅ ክምችት በጥቁር ገበያ በመቸብቸብ ለመሳሪያ ግዥ አውሎታል፡፡በጦርነቱ ሳቢያ የተገባው ዕዳ በሚቀጥሉት ትውልዶች ጫንቃ ላይ የሚያርፍ ይሆናል፡፡ ለዝህም ይመስላል መንግስት ደጋግሞ ጦርነቱን ለማስቀጠል ፍላጎት ቢኖረውም አቅም ማጣቱ ፀሀይ የሞቀው አገር ያወቀው የአደባባይ ሚስጥር መሆኑ እየተገለፀ ያለው፡፡

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.