The Genocide of PM Abiy Ahmed army in Wollega. ያልሰማ ይስማ, የወታደሩ ፀፀት (ከ ወታደር አይነገር ስሜ)

ያልሰማ ይስማ ::  የወታደሩ ፀፀት (ከ ወታደር አይነገር ስሜ) 

Feb 1, 2 018 – Via Gebre Hagos

PM Abiy Ahmed and Lt General Birhanu Jula Gelalcha are responsible for civilian massacre in Wollega. The genocide is still going on.

ጊዜዉ ያለንበት ጥር ወር 2011 አጋማሽ ነበር ፡፡ ለግሌ ጉዳይ ወደ ደምቢ ዶሎ ደርሼ ሲመለስ ጉሊሶ ከሚባለል ከተማ ምሳዬን ለመብላት ወደ አንድ መንገድ ዳር በሚገኝ ሆቴል ጎራ ሲል ዱሮ ከዉጪ ሰምቼ እሚጨነቅበትን ነገር ከምንጩ ለማጣራት ወርቃማ ዕድሌ አገኘሁ ፡፡ ባሁኑ ጊዜ ወደ ወለጋ ዘምተዉ ካሉት የኢህአደግ ወታደሮች አንዱ ጠመንጃዉን በጉልበቱ ላይ ደግፎ ከጓደኞቹ ትንሽ ርቆ ወደ ቤቱ ጎን ዞር ብሎ በሐሳብ ተዉጦ ዝም ብሎ ይቀመጥ ነበር ፡፡ እኔ ለምሳ ሲገባም እንዲሁ ይቀመጥ ስለነበር ሁኔታዉ ሲለተሰማኝ ባካባቢዉ ሲቪል ሆነህ ከኢህአደግ ወታደር ጋር መናገር አስቸጋሪ ቢሆንም እኔ ግን ከጥቂት ጊዜ ቦኋላ አካባቢዉን ስለሚለቅ እየፈራሁም ቢሆን ትንሽ ተጠግቼ ቡና ገዝቼለት አብሬ ቡና እየጠጣሁ ከሃሳቡ ሊገላግል ወሰንኩኝ፡፡

ዉስጤ በፍራቻ ተዉጦ ብዙ ባይስማማበትም እየተንደፋደፍኩ “ወገኔ ቡና ጠጣ” አልኩት ፡፡ ዞር ብሎ አይቶኝ “አመሰግናለሁ ፤ ጠጣሁ” አለኝ ፡፡ ግን በአይኑ ወዲያና ወዲህ እየቃኘ ፊቱን ወደ እኔ አዙሮ በጎርናና ድምፅ ማንነቴን ጠይቆኝ ካጣራ ቦኋላ ጠጋ ብሎኝ በተሻለ መንፈስና ሀዘን በተሞላ ልብ ያናግረኝ ጀመር ፡፡ ሲነግረኝ በትዉልዱ ከደቡብ ሕዝቦች ክልል ሆኖ ከትግራይ ከባድሜ ግንባር አካባቢ ተነስተዉ ኦነግን ለመደምሰስ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዉ የመጣ ኃይል አባል መሆኑን ነገረኝ ፡፡ ለካ ባካባቢዉ ያለዉ ሁኔታ ግራ ገብቶት ከጓደኞቹ ቢርቅም ራሱን መሸሽና ከሕሊና ትዝብት ክስ መገላገለል ተስኖት ከራሱ ጋር ተጣለልቶ ገላጋይ አጥቶ እየተቀመጠ መሆኑንም ነገረኝ ፡፡ ታዲያ እኔም ትንሽ ጠጋ አለልኩና ለምን እንደሆኔ ለማወቅ ጓግቼ እሽ እያልኩ መታደመን ቀጠልኩት ፡፡ እሱም ቀጠለ፡፡ ከትግራይ ሲንነሳ ለቦታ ለዉጥ ወደ ወለጋ ጠረፍ የሚንሄድ ይመስለን ነበር እንጂ ለጦርነት እንደሚንሄድ ከአለቆቻችን በስተቀር ማንም አያዉቅም ነበር ፡፡ እኛ ከመረጃ ርቀን ስላለን መኪና መጥቶ ሲቆም አለቃዉ ሾፌሩን ወዳዘዘዉ ከማቅናት ሌላ ድርሻ የለንም ፡፡ በዚህ መልኩ ሂዴን አማራ ክልልን አቋርጠን ወደ ወለጋ ለመግባት አባይን እንደተሻገርን እንግዳ ነገር አጋጠመን ፡፡ በምዕራብ ጎጃም በቡሬ በኩል አባይን ተሻግሬን ወለጋ እንደገባን አገምሳ በሚባለል ቦታ፡ ቀጥሎም ኪረሙ ላይ ከባድሜ ዉጊያ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ መናገሩም የሚከብድ ዉጊያ ተከፈተብን ፡፡ አንድ ብለን ከሃይላችን ቀንሰን መቅበር ጀመረን ፡፡ አሁንም ቀጠለን ፡፡ ምስራቅ ወለጋን አቋርጠን ዲዴሳ ወንዝን ተሻግረን ወደ ምዕራብ ወለጋ ስንዘለልቅ ከፊታችንም ከኋላችንም እየተንቀሳቀሰ ያለዉ ኃይል የኦነግ የደፈጣ ጥቃት እየበረታ በመምጣቱ አንድ በአንድ እየተመታ እየተንጠባጠበንና እየቀነሰን መጣንና እኛ ራሳችንን ችለን ሲንሄድ የነበርን ሰፊ ኃይል ክፉኛ በመመታታችን አሁን ራሳችንን መቻላችን ቀርቶ ምዕራብ ወለጋ ግምቢ አካባቢ ባለዉ ኃይል ላይ ተደርበን እንድንቆይ ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡

ከአምስት ቀናት ቦኋላ አሁንም ሌላ ኃይል ተጫነና የኦሮሚያና ቤ/ጉሙዝ ብሄረሰቦችን ግጭት ለማብረድ እየሄዱ ናቸዉ ስለተባለ ኦነጎች በሀገር በሽማግሌዎች ተለምነዉ አሳልፎአቸዉ መጥተዉ እኛ ጋ ግምቢ ሲደርሱ አሁንም ለሁለት ቀናት መላ ስፈላለግ ከቆየ ቦኋላ ከግምቢ ተነስተን ታች ባሉት ከተሞች ላይ በከተማ ተገድበዉ በኦነግ ተከበዉ ላሉ ጦራችን ድጋፍ እየሰጠን እስከደምቢ ዶሎ ዘልቀን በጊዳሚ በኩል ገብተን ቤጊ ወረዳ ኮቦር በሚባል ለልዩ ቦታ የሚገኘዉን ትለልቁን የኦነግ ካምፕ እንድንደመስስ ግዳጅ ስለተሰጠን እንደገና ከኋላችን ከመጣዉ ኃይል ጋር ተቀላቅለን ኃላችንን አደራጅተን ወደ ቤጊ እንድናመራ ተደረገ ፡፡ በወለጋ ኦራል የሚባል ወታደር መኪናን ተሳፍሮ መጓዝ የሞትን በር እንደማንኳኳት ስለሚቆጠር እንደወትሮአችን ኦራለን በዝግታ እንዲሄድ አድርጌን እኛ ደግሞ ከግራና ከቀኝ ከበን መንቀሳቀስ ጀመረን ፡፡ ገና ከ260 ኪ.ሜ በላይ ተጉዘን ቤጊ ኮቦር ለመሄድ ከግምቢ ወጥተን ከ20 ኪ.ሜ በላይ ሳንጓዝ በዞኑ ዋና ከተማ ግምቢ አፍንጫ ሥር ላሎ አሳቢ በሚትባል ወረዳ ላይ ከፍተኛ ዉጊያ በኦነግ ተከፈተብን ፡፡ ሁኔታዉን በጣም አዳጋችና መጥፎ የሚያደርገዉ ደግሞ ከዚህ ኦነግ ሁለት ጥይት ሳይተኩስ በአራቱም አቅጣጫ መንገድ ሙሉ በሙሉ ይዘጋ ነበር ፡፡ ኦነግ በተጠቀሰዉ ቦታ ዉጊያዉን ጋብ አድርጎ እኛን ወደ ጫካ አሳልፎ መቀ ነጆ ወደሚባል ቦታ ለቁረጣ ሲያልፍ በመንደር ወደ ጫካ የቀረን እኛ ብቻችን ነበረን ፡፡ መላ ፈጥረን ወደ አንድ ጎን ለማፈግፈግና አካባቢዉን እየቃኘን አቅጣጫ ለመቀየር ወደ ቡና ጫካ ሲንቀርብ አምስት ሰዎች ቡና ይለቅሙ ነበር ፡፡ ጠጋ ብለን ኦነግ ወዴት እንደሸሸ ሲንጠይቃቸዉ አናዉቅም አለን ፡፡ ቢያዩም ባያዩም ከመንግስት በላይ ለድርጅቱ ስለሚቀርቡ ስለኦነግ ሲጠየቁ አላዉቅም ማለት ለወለጋ ህዝብ አመላቸዉ ነበር ፡፡ ሁላቸዉም እንዲህ ሲሉ ከጫካዉ ወደሜዳ እንድናወጣቸዉ ታዘዘን ፡፡ ቡና የሚለቅሙበትን ከቀርከሃ የተሰራ ጉድጓዳ አጣናቸዉን ይዘዉ ከአንዲት አሮጊት ጋር 5 ሆነዉ በቁምነገር የኛን ትዕዛዝ ተቀብለዉ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ሜዳ ካወጣናቸዉ ቦኃላ አንድ የትግራይ ክልል ተወላጂ የሆነዉ አለቃችን “የኦነግ ቀላቢዎች እነሱ ራሳቸዉ ናቸዉ”፡፡ ስለዚህ ከኦነግ ለይተን አናይምና ጭረሱላቸዉ ብሎ ለ 5 የአማራ ብሄር ተወሊጅ ወታደሮች ትዕዛዝ ሰጠ ፡፡ ከሁለም በላይ ልቤን ያቆሰለዉ እናቴን የመሰለችኝ አሮጊቷ ቀሚሷን ጠቅልላ ከመቀናቷ ስር ወትፋ ለስራዋ እንደባተለች የዋህ የኢት/ ዜጋ ለማታዉቀዉ ነገር ከሚትወደዉ ቤቷና ቤተሰቦቹዋ ተለይታ ከ 4 ጅጌዎቹዋ ጋር በኛ በሀገር መከላከያ በተተኮሰባቸዉ ጥይት ሜዳ ላይ ተዘርግፈዉ ቀሩ፡፡

አሁንም አምስቱን ሬሳ ባንድ እርምጃ መሬት ክልል ላይ ጥለን የአካባቢዉ ሁኔታ የህዝብ ቁጣ የተቀላቀለበት በመሆኑ ቶሎ ባለመብረዱ እናንጎ በሚትባል ከተማ አካባቢ ቆይተን ከተወሰነ ጊዜ ቦኋላ አሁንም የተዘጋጉ መንገዶችን እየከፈተን ወደ ደምቢ ዶሎ እንዲናመራ እንደገና ታዘዘን ፡፡ ካለንበት እናንጎ ከሚትባል ከተማ ብዙም ሳንርቅ ወንጆ በሚትባል አካባቢ ከፊታችን እየመጣ ያለዉ ሐይል ከነኦራሉ ስለተመታ ፡፡ መረጃ ደርሶን እኛ በቦታዉ ስንደርስ እንኳንስ ኦነግ ነዋሪዎቹን ባካባቢዉ ማግኘት አልተቻለም ነበር ፡፡ ምክንያቱም ያለፈዉን ጊዜ ታርክ ሰምተዋልና ፡፡ ይሁን እንጂ ቤት ለቤት አሰሳ እያደረግን እያለን እንድ በጠና ታመመችዉን እናቱን ትቶ ለመሸሽ ልቡ ስላልፈቀደ ከእናቱ አልጋ ተደግፎ ቁጭ ብሎ ከህመምተኛ እናቱ ጋር የሚቃስት አንድ ዕድሜዉ ወደ 45 የሚጠጋ ጎልማሳ እቤት ዉስጥ ሲቀመጥ ደርሼበት አይቼ እንዳላዬ ሰዉ በዉጪ በኩል ሁኜ የቤቱን ዙሪያ እያሰስኩ ከቤት ዉስጥ የጥይት ድምፅ ሰምቼ ሲመለስ ቅድም ያየሁት ሰዉዬ ከእኔ በኋላ በመጡ ወታደሮች በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ከእናቱ አልጋ ሥር ወድቆ ተገድሎ አገኘሁት ፡፡

በወታደር ቤት የዚህን ዓይነቱን ነገር ለምን ብሎ መጠየቅ ስለማይቻል ዝም ብለህ ማየት የግድ ይሆናል ፡፡ አሁንም ወደ ተነሳንለት አልደረስነምና ስንሄድ ጉሊሶ በሚትባል ከተማ መግቢያ ላይ ኦነግ ዉጊያ ከፍቶብን አሁንም ብዙ ወታደሮች ተጎድተዉብናል ፡፡ መኪና ትተን በእግራችን ወደሚቀጥለዉ መንደር ሲንገባ ነፍሳችሁን ለማትረፍ ያገኛችሁትን በሙለ አጋድሙ የሚል ትዕዛዝ ተሰጠንና ዛሬም እንደ ከዚህ በፊቱ ሁለ የህዝብ ነኝ ከሚል አለቃ በተሰጠዉ ትዕዛዝ ኦነግ አለበት ተብሎ አንድ ቤት በቦምብ እንዲመታ ታዘዘ ፡፡ ከበን ሲንደርስበት በቤቱ ኦነግ ባይገኝም አንዲት እናትና ሴት ልጇ በቦምቡ ተከትፈዉ አገኘናቸዉ ፡፡ በወዲያ በኩል ወደ መንደሩ የተሰማራዉ ኃይልም አንድ ማሳዉን መስኖ እያጠጣ የነበረዉን ፀጉረ ረጃጅም ወጣት ኦነግ ብሎ እማሳዉ ዉስጥ ጥሎ መጥቷል፡፡ እኔ እስካየሁት ድረስ የወለጋ ሕዝብ በተለይ በዕድሜ የገፉት ሰዎች እንደእንግዳቸዉ ብሉልኝ ጠጡልኝ ከማለት ዉጪ ተንኮል የማያዉቁ የዋህ ሕዝብ መሆኑን ሰምቼዋለሁ፡፡ አሁንም ያዉ ነዉ፡፡ ለካስ ይህንን ሕዝብ ነዉ እንዴ እየገደልን ያለነዉ የሚል ሁሌ ጥያቄ ይጭርብኛል፡፡ ይህንን ሲያዩ በንዴት ከእኛ ወደ ኦነግ የሚቀላቀሉ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ ወታደሮች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡ ዱሮ ዉጊያ ሲከብድ ወታደር በኮምቦይ መንቀሳቀስ ከጥቃት ያተርፋል ይባል ነበር ፡፡ አሁን ያለዉ ሁኔታ ግን ተገላብጦሽ ሆኗል ፡፡ ከ 5-10 የሚሆን የኦነግ ኃይል ከ 10-15 በሚደርሱ መኪኖች በተጫኑ የኛ ወታደሮች ላይ ቦታ ይዘዉ በመተኮስ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት ማድረስ በኦነግ የዉጊያ ቀመር አድስ አይደለም ፡፡ በጣም ተስፋ እያስቆረጠን የመጣዉ ነገር ደግሞ ከትግራይ ከመጡ ወታደሮች አሁን በህይወት ያለት ግማሽ አንሆንም ፡፡ እኛም ህዝቡም ክፉኛ እየተጎዳን ነዉ ፡፡ ኦነግ እኛን እኛ ደግሞ ህዝቡን እየጨፈጨፈን ነዉ ፡፡ ከኦነግ ጋር ሳይሆን ከወለጋ ህዝብ ጋር ጦርነት ገብተናል ማለቱ ይመረጣል ፡፡ ግን ለማን ?

አሁን ባለዉ ሁኔታ ኦነግን ከህዝቡ ህዝቡን ከኦነግ መለየት አመድን በወንፊት ከዱቀት ለመለየት መሞከር ይመስለኛል ፡፡ አሁን እየሰራን ያለነዉ ነገር በትዕዛዝ ስለሰራን ሰዉ ሊጠይቀን አይችልም ቢንል እንኳ ሰዉን በመልኩና ባምሳሉ የፈጠረዉ ፈጣሪ አንድ ቀን ይጠይቀናል ፡፡ ጦርነቱ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በዛ ምድር ላይ ምን እንደሚፈጠር መገመቱ አስቸጋሪ ቢሆንም እኔ በበኩለ ግን በዚህ በተፈጥሮ በታደለች ለም መሬትና የዋህ ህዝብ ላይ ቦምብ ሲዘንብ በዓይኔ ማየት ስለማልፈልግ በግሌ ዉሳኔ ላይ ደርሼዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ምንም የታጠቀ ኃይል ከጎኑ ባልነበረበት ጊዜ እንኳ ግንባሩን ለእስናይፔራችን ሰጥቶ ሁሉንም ባለበት የገታ ወጣት ዛሬ ደግሞ ወደታጠቀዉ የኦነግ ኃይል በገፍ እየተቀላቀለ ስለሆነ መንግስት በእዉነቱ ለህዝብ የሚያስብ ከሆነ ነገሩን ቶሎ ካላበረደ ወደባሴ ጦርነት እያመራን መሆኑ አያጠራጠርም፡፡ ከዚህ ይህንን ግፍ ሲንሰራ ይህ ነገር የተፈፀመዉ ቤተሰቤ ሊይ ቢሆንስ የሚል ጥያቄ ሁሌ ከአእምሮዬ ሲቃጭል ሕሊናዬ ዕረፍት የለዉም ፡፡ የሕሊና ክሱን መቋቋም አልቻልኩ ምም ፡፡ ለጊዜዉ ባካባቢዉ ላይ የታወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስኪያበቃ ለማንኛዉም የቀጠናዉ ወታደር ፈቃድ አይሰጥም ስለተባለ እንጂ አሁንማ በቃኝ ብዬዋለሁ ፡፡ ቡናህን አልጠጣም ያልኩትም ለዚህ ነበር ፡፡ አንዱን እየገደለ ከዘመዱ እጅ መጋበዝ በባህላችን እርም ነዉ፡፡ ሁሌ በኦነግ ሰበብ በንፁሃን ሕዝብ ደም ላይ ከሚረማመድ ወደ ቤተሰቤ ተመልሼ የራሴ ያልኩትን ኑሮ መምራቴ ይበጀኛል በማለት በምሬት ሲነግረኝ በመሃል መኪናዬ እንሂድ ብሎ ጥሩንባዉን ሲነፋ እኔም ቀሪ ኑሮህን እግዚአብሄር ይባርክ ብዬ ተለያየን፡፡

ለካስ ወለጋና ኑሮዉ ይህን ይመስል ነበር ?

2 Comments

  1. it is a sad history what shall we do for this bitter struggle we have to swallow it to pass through such sordid life to win and exist as human being .
    But it is a colonizers work in every peoples history but we have admit
    it as it will pass even if it seems hard that is the history of colonizers never stand at one place it will be changed by strong commitment and continues struggle to next generation even if many betrayed and opportunists are too much so sad and bitter it is but we win .

  2. Why the current government is committed to fight OLF only when there are many forces in other parts of the country which it didnot control. For example why they do not snatch Getachew Assefa from Mekele? it is sad to see OLA paying sacrifice at this time while others are enjoying the relative freedom brought about by the struggle of OLA itself.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.